አብይ አሕመድ 60 ከመቶ ከኤሌክትሪክ ጋር የማይተዋወቁ ዜጎች ቅድሚያ መሆናቸውን አመለከቱ

” ያለኤሌክትሪክ ሃይል የትኛውም አገር ድህነትን አላሸነፈም። አካታች እድገትን አላረጋገጠም። የዜጎቹን ኑሮ አላረጋጋም። ዘላቂ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የአካባቢ ልማት ስኬቶችን አላስመዘገበም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ሁልጊዜም የአባይ ውሃ በምክንያታዊነት እና በፍትሃዊነት ጥቅም ላይ ለማዋል የተነሳችበትን መሰረታዊ ምክንያት አስታውቁ።60 ከመቶ ከኤሌክትሪክ ጋር የማይተዋወቁ ዜጎች ቅድሚያ መሆናቸውን አመለከቱ።

“የህዳሴ ግድብ የትብብር እንጂ የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም” በሚል መሪ ሃሳብ ጽህፋቸውን ያሰራጩት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የፍሰት አለመመጣጠን ለማስቀረትና ወንዙም አመቱን ሙሉ ተመሳሳይ የውሃ ፍሰትና ያልተቆራረጠ የሃይል ምርት እንዲኖረው ግድቡ በቂ ውሃ መያዝ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የምትገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትብብር እንጂ የግጭት መንስኤ ሊሆን እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ። ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማምረቻና በኢንዱስትሪዎች ላይ የተመሰረተ ዘመናዊ ኢኮኖሚ የመገንባት ውጥን ይዛ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሚስፋፉት የመሰረተልማት አውታሮች ውስጥ ለዜጎች የሚዳረሱት ጥራት ያላቸው የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ ንጹህና ከብለት የጸዳ አካባቢ እንዲፈጠር በትጋት በመስራት የተፈጥሮ ሃብቶች እንዳይጎዱና ስነምህዳሮች እንዳይዛቡ በማድረግ የከባቢ አየር መበከል የሚያስከትላቸው ተጋላጭነቶች እንዲቀንሱ እየሰራች መሆኑን አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ የልማት ህልሞች እውን የሚሆኑት ንጹህ የሃይል አቅርቦት አማራጮች ተግባራዊ ሲደረጉ መሆኑን ያሰመሩበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ተፈጥሮ በለገሳት የውሃና የመልክአምድር ስጦታዎቿ ተጠቅማ ህልሟን እውን ለማድረግ ጥረት እያደረገች እንደሆነ ገልጸዋል።
አብዝታ ልትጠቀምባቸው ከምትችላቸው መስኮች መካከል የታዳሽ ሃይል ዘርፉ ቀዳሚው ቢሆንም ከ53 በመቶ አሊያም ከ60 ሚሊየን በላይ የሆኑት ኢትዮጵያውያን ከኤሌክሪክ ሃይል ጋር አይተዋወቁም ብለዋል።
ያለኤሌክትሪክ ሃይል የትኛውም አገር ድህነትን አላሸነፈም አካታች እድገትን አላረጋገጠም የዜጎቹን ኑሮ አላረጋጋም እንዲሁም ዘላቂ የኢኮኖሚ የማህበራዊና የአካባቢ ልማት ስኬቶችን አላስመዘገበም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ ሁልጊዜም የአባይ ውሃ በምክንያታዊነት እና በፍትሃዊነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያላት ፍላጎት ጽኑ መሆኑን ገልጸዋል።
በሁሉም ኢትዮጵያውያን ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ እየተገነባ ያለው የህዳሴ ግድቡም ይሄንን የኢትዮጵያን የመተባበር መርህ አጉልቶ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ከግብጽና ሱዳን ባሻገር ለምስራቅ አፍሪካ አገራትም ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
ግድቡ ሲጠናቀቅ 15 ሺህ 700 ጊጋዋት የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭና 90 በመቶ የሚሆነው ሃይል የሚመረተው የኢትዮጵያን የክረምት ወቅት መሰረት በማድረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ይሄንን የፍሰት አለመመጣጠን ለማስቀረትና ወንዙም አመቱን ሙሉ ተመሳሳይ የውሃ ፍሰትና ያልተቆራረጠ የሃይል ምርት እንዲኖረው ግድቡ በቂ ውሃ መያዝ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።
ግድቡ ለታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት የሚኖረው ጠቀሜታ እንዳልተነገረለትና ሱዳንን በየአመቱ ከሚያጋጥማት የጎርፍ አደጋና በበጋ ከሚፈጠረው የውሃ እጥረት ስጋት ነጻ እንደሚያደርጋት አብራርተው የግድቡ መጠናቀቅ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ከኢትዮጵያ ጋር ለተሳሰሩት ሱዳንና ሌሎች ሃገራት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

ከአስዋን ግድብ የሚተነውን የውሃ ሃብት በመቀነስ በአጠቃቀምና በአያያዘ ረገድ ግድቡ ለግብጽም የሚሆን ትሩፋት እንደሚኖረው አስረድተው፤ በመላው አለምና በአባይ ወንዝ ቀጣና ታዳሽ ሃይል በማምረትና በካይ ንጥረ ነገሮችን በመቀነስ ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካትና ለአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እውን መሆን ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው አስገንዝበዋል።

አፍራሽ አስተሳሰቦችን ወደ ጎን በማለት ገንቢ እሳቤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት ሰላምን ለመገንባት አንዱ ሌላውን ሳይጎዳ ተያይዞ ለመልማት የአባይ ወንዝ እንደ አጠቃላይና የህዳሴ ግድብ በተለየ የሚያስተሳስሩ መሆናቸውን በመገንዘብ ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በጋራ መንቀሳቀስ አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply