ለማ መገርሳ አዲስ አበባ ተመለሱ፤ ከድርጅታቸው ጋር መቀጠል ይፈልጋሉ

የቀድሞው የድህንነት ሹምና የኦሮሚያ ክልል መሪ የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸው ታውቋል። አቶ ለማ በአሜሪካ ሚኖሴታ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ከሚሰሩት ባለቤታቸው ጋር አብረው ይኖሩ እንደነበር ባልደረቦቻቸው መናገራቸው ይታወሳል። እሳቸውም በአንድ አጋታሚ እረፍት ላይ እዛ መሆናቸውን አስታውቀው ነበር።

በአመለካከት፣ በተለይም “ብልጽግና የተመሰረተበት ጊዜ አግባብ አይደለም” የሚል አቋም መያዛቸው ለልዩነቱ ዋና ምክንያት እንደሆነ ለቪኦኤ ሲያስታውቁ ” ተሰሚነት አጣሁ ” በሚል ስሜታቸውንም መግለጻቸው አይዘነጋም።

እሳቸው የልዩነቱ መነሻ ይህ ነው ይበሉ እንጂ በውቀቱ በድምጽ እንዳልተቃወሙ ተገልጾ ነበር። ከዛ ይልቅ የኦሮሚያ ብልጽግናን ያለ ስራ አስፈሳሚው ምክክር በማሟሟት አንድ ወጥ የኦሮሚያ ፓርቲ ለመመስረት ጀነ ጃዋር ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ዋናው የልዩነቱ መነሻ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ።

አቶ ለማ “እኔና አብይ አሕመድን የሚለየን ሞት ነው” በሚል “አጋፔ” የተሰኘውን የፍቅር ጫፍ በአደባባይ ሲያጸኑ የተደረገላቸው አድናቆት ብዙም ሳይቆይ በቪኦኤ መገፋታቸውንና ሰሚ ማጣታቸውን መናገራቸው በወቅቱ አብዣኞችን ሲያስገርም፣ ለፖለቲካው ቅርብ የሆኑትን ” እዚህ ድረስ ነው እንዴ የሚያስቡት” የሚል ጥያቄ አስነስቶባቸው ነበር። በውቅቱ አቶ ፈቃዱ ” ለአብላጫ ድምጽ መገዛት የአፕርቲ አሰራር ነው። ጓዳችንን ዛሬም ነገም እናከብራለን። እንወያያለን” የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ኢትዮጵያ ቆንስላ ቢሮዎቿንና ኤምዳሲዎቿን በመቀነስ የኦንላይን አገልግሎትና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አሰራር እንደምትከተል መገለጹን ተከትሎ የሜኖሶታ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በመዘጋቱ ይሁን በሌላ በውል ባልታወቀ ምክንያት አቶ ለማ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

በኦሮሚያ ስልጡን የፖለቲካ እይታ መያዝ እንደሚያስፈልግ ያመኑ የማስታረቅ ስራ በጀመሩበት፣ እንደ አገርም ሁሉን አካታች ውይይት የሚጀመርበት ሂደት እየተጣደፈ ባለበትና የነ ጃዋር መሐመድን መፈታት ተከትሎ የአቶ ለማ አዲስ አበባ መመለስ መነጋገሪያ ሆኗል። ዝግጅት ክፍላችን ባደረገው ማጣራት አቶ ለማ ተቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከድርጅታቸው አመራሮች ጋር ይገናኛሉ።

አቶ ለማ አሜሪካን አገር ተቋቋመ በተባለ ንቅናቄ ውስጥ እንዳሉበት ሲነገር ” የለሁበትም፣ ተዘጋጀ የተባለውንም ሰነድ አላየሁም። የሚወራው ሁሉ ወሬ ነው” በማለት መናገራቸው፣ የምያውቋቸው አቶ ለማ ዲሲ የመጡት ለቅሶ ሊደርሱ እንጂ ከማንም የፖለቲካ ዘመቻ ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው መግለጻቸው አይዘነጋም።

See also  ኦፌኮ ብሔራዊ ውይይቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪና ሸኔ እንዲካተቱበት ጠየቀ

አቶ ለማ ራሳቸውን ከፖለቲካ አቅበው የፒኤችዲ ዲግሪያቸውን ለማያዝ ይተጉ እንደነበርና ያንኑ ማሳካታቸውን ተከትሎ፣ አቶ ለማ ድርጅታቸውን እንደማይጠሉና በየትኛውም ጊዜ ችግራቸውን በውይይት ሊፈቱ እንደሚችሉ በቅርብ የሚያውቋቸው በልበ ሙሉነት ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል። አቶ ለማ ትህነግን ባስወገደው ትግል ውስጥ ቀዳሚ ሚና ከነራቸው መካከል አንዱ መሆናቸው ሲገለጽ እንደነብር ይታወሳል። አቶ ለማ በትውልድ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከተወለዱባት ሆሮ ጉድሩ መሆናቸውም ግላዊ ፋይላቸው ይናገራል።

ዜናውን አስመልክቶ እሳቸውም ሆኑ ማንኛውም ወገን በይፋ ያስታወቁት ምንም ዓይነት መረጃ የለም።

Leave a Reply