«ለሽብር ሊውል የታሰበ ዶላር ከመቅፅፈት በኤርትራ የባህር ሀይሎች ተወርሶ ብሩ አስመራ ገብቷል»

የሦስተኛው ሙሊት ዝግጅት~ የግብፁ ናይል online ዘገባ

በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ላይ ችግርም ረሀብም ጦርነትም፣ ማዕቀብም ተከስተዋል። ይህ የሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ረሀብ ጦርነት ማዕቀብ ያልደፈረው ኢኮኖሚ እንዳለ ሆኖ ለሦስተኛ ሙሊት እየተዘጋጅ ነው። ቢሊዮን ዶላር የወጣበት የግብፅ መንግስት እቅድ መና ቀርቷል። ምን እያለ እንደሆነ ግልፅ ነው። ግብፅ በሦስት አመት ውስጥ ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ አውጥታለች። ከቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ጀርባ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር አለበት። ይሄ ለሌላ ትንታኔን ይጠይቃል እመለስበታለሁ።

”ዶክተር አረፋት ዋሽ” የሚባል አንድ ሙህር ያለውን ነው የማስነብባችሁ። የግብፅ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዴት እንደከሰረ አልጠቀስም። ደቡብ ሱዳን ላይ መና የቀረበትን ጉዳይ በሌላ ትንታኔ እመለስበታለሁ። እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነቶች የራሳቸው ሚና አላቸው።

የኬኒያው የስለላ ድርጅት በባህር ዳርቻ ላይ ስብሰባ ተቀምጦ በኤርትራ የባህር ዘበኞች ለምን በጥይት እንደተሳተ ሌላ ያልተሰሙ መረጃዎች ናቸው። በዚህ ዙሪያ ግን ረገጥ አድርገን መፃፍ አለብን። የግብፅ መንግስት ሙዝና ቲማቲም ይዞ እየዞረ የሰራው ድራማ ራቁቱን ያስቀረው የኢትዮጵያ ጥንካሬ ነው ወይስ የቀድሞው የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ቤኒያሚን ኔታኒያሁ፣ አልታወቀም። በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር፣ ከሱዳን ተነስቶ ግብፅ ከከገባ ቡኋላ፣ እንደገና በግብፅ የባህር ድንበር አካባቢ የኬኒያ ደህንነቶች ተቀብለው ወደ ኢትዩጵያ አስገብተው ለሽብር ሊውል የታሰበ ዶላር ከመቅፅፈት በኤርትራ የባህር ሀይሎች ተወርሶ ብሩ አስመራ ገብቷል። እዚህ ላይ ግን የእስራኤሉ ሞሳድ የሰራው ድራማ አለ ወይም የእስራኤል መንግስት ለኢትዮጵያ የተወው አንድ ውለታ አለ። መልሱን ለማወቅ ማንንም አንጠይቅም። ይህ ስራም ይህ መረጃም የኢንተለጀንስ ጉዳይ ነውና። ዘገባው የዘጆርዳን ታየምሰ ነው።
.
የግብፁ ናይል ኦንላይን እንግዳ ወደናገረው ዘገባ እንሸጋገር። ርዕሱ ከላይ አለ። ማዕቀብ ጦርነት ረሀብ ግጭት ያልበገረው የህዳሴ ግድብ ለሦስተኛ ሙሊት እየተቆነጃጀነ ነው። ይገርማሉ ይላል ዶክተር
አረፋት በብስጭት ያልበላውን ጉንጩን እያከከ። ይሄንን ሁሉ መከራ ተሸክመው ለሦስተኛ ሙሊት ይዘጋጃሉ። በአንፃሩ እኛ ከነሱ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ሰላማዊ ዲፕሎማሲያዊ ሀይል ያለን የውሃ መብታችንን ለማስጠበቅ የነሱን ያህል አልሰራንም። ጉዳዩ የአላማ ነው። እነሱ የሚኖርለትም የሚቆሙለትም የሚሞቱለትም አላማ ዓላቸው። እኛ ግን ያለ አለማ ነበር የምንከራከራቸው። ዶክተር አረፋት ሲጠይቅ እንዲህ ይላል በሁሉም መስክ እንዲህ ሆነን ልንቀር ነው ወይ ? ቢሊዮን ዶላሩ፣ ያሁሉ የመሪዎቻችን ድክመት የህዝባችን ምኞት የት ገብቶ ሊቀር ነው ?። ሱዳንን ከኛ ለማሰለፍ ጥረን ተሳካ ስንል የቀጠናውን መከራ የተሸከመች ሱዳን ሆና በየቀኑ በሚሊዮን ዶላር እያከሰረችን ነው። ለዚህ ጥያቄ ማነው መልስ የሚሰጠው ይላል ዶክተር አረፋት !
.
ከላይ በነካ ነካ እንደነገርኳችሁ ግብፅ በየ አመቱ በቢሊዮን ዶላር የምትከስረው የግድቡን ሙሊትና የኢትዮጵያ ሰላም ለማበላሸት ነው። የዘንድሮው ደሞ ለየት ያለ ነው። ብሩ አስመራ ገብቶ መቅረቱ አጠያያቂ ነው።

See also  የሰልፊ ፓለቲካ - በላይ ባይሳ

በዚሁ ዙሪያ
ሞሳድ የበላው ነጭ ድመት የሚለውን
ትንታኔ በቀጣይ እመለስበታለሁ።

Via – Suleman Abdela

Leave a Reply