ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ልታደርግ ነው

በኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ [dietary guideline] ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በኋላ ይፋ እንደሚሆን በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የምግብ ስርዓት እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክተሩ ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ ለቢቢሲ ገለጹ።

ሃላፊው ለሶስት ዓመታት ሲዘጋጅ የቆየው የጤናማ አመጋገብ መመሪያ ወደ መጠናቀቁ መደረሱን ገልጸው በጤና ሚኒስቴር እና በሌሎች ሚኒንስቴር መስሪያ ቤቶች የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ማስረሻ የመመሪያውን አስፈላጊነት ሲገልጹ “ህብረተሰቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንድን ነው መብላት ያለብኝ? በሚል ብዙ ሰው ይጠይቃል የተማረም ያልተማረም ሰው ስለዚህ ይህንን በዘላቂነት ለመመለስ” የተዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።

መመሪያው ለማዘጋጀት ‘ሰፊ ጥናት’ እንደተደረገበትም ገልጸዋል። እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች የተዘጋጀ ሲሆን ምን አይነት ምግቦች እና አመጋገቦች ለጤናማ ህይወት እንደሚረዳ የሚያመላክት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም በሀገሪቱ ዙሪያ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ሲሉ አክለዋል።

ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ ምንድን ነው?

እንደ ዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ትርጓሜ ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ በሀገራት ውስጥ ጤናማ የአመጋገብ እና የኑሮ ዘይቤም ለመገንባት የሚወጡ ናቸው።

በውስጣቸውም ከስነ ምግብ አኳያ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን እና አመጋገቦችን በተለያዩ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎቻቸው በምክረ ሃሳብ መልክ የሚያቀርቡበት ነው። በተጨማሪም እርሻና የምግብ ዝግጅትን በተመለከተ የሚያትት ነው።

በሌላ በኩል ጤናን ለማጎልበት እና አሳሳቢ በሽታዎችን ለመከላከል የሚረዱ ንጥረ ነገርን ያዘሉ ምግቦች የአመጋገብ ዘይቤዎች ላይ ምክር ሃሳብ ይሰጣሉ።

እንደ ድርጅቱ መረጃ በዓለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አላቸው።

በአፍሪካ ሰባት ሀገራት ይህ መመሪያ ያላቸው ሲሆን ከሌሎች አህጉራት አንጻር ዝቅተኛው ነው። በአህጉሪቱ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሲሼልስ፣ ናይጄሪያ፣ ቤኒን፣ ናሚቢያና ሴራሊዮን የአመጋገብ መመሪያ አላቸው።

ከሁለት ወር በታች በሆነ ጊዜ የጤናማ አመጋገብ መመሪያን ይፋ ለማድረግ ያቀደችው ኢትዮጵያ 8ኛዋ የአፍሪካ ሀገር እንደምትሆን ይጠበቃል።

ቢቢሲ አማርኛ ላይ ዋናውን ዜና ይመልከቱ

Related posts:

"በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ319 የእዳታ እህል የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መቀሌ ደርሰዋል" OCHAMay 21, 2022
“የአዲስ አበባ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው” ኮሙኒኬሽን ቢሮMay 21, 2022
«የግል የትምህርት ተቋማት የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚታደልባቸው እየሆኑ መጥተዋል»May 20, 2022
መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻልና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ተከታታይ እርምጃ አንደሚወስድ ተገለጸMay 18, 2022
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት መኖር እና የሚያስከትለው ውጤትMay 17, 2022
በመኪና አደጋ አራት የጤና ባለሙያዎችን ህይወት አለፈMay 15, 2022
የሞት ቅጣት የሚያሰጋቸው ጀማል እና ሀሰንMay 15, 2022
"ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት ●●●May 14, 2022
የአቅመ ደካሞችን ጣሪያ መድፈንም ያስወግዛል?May 9, 2022
በኦሮሚያ ቦረና ዞን - ገበሬዎች ራሳቸው ሞፈር እየጎተቱ እያረሱ ነውMay 3, 2022
ከደሴ ከተማ ቤተ-እምነቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ህብረት የተሰጠ መግለጫApril 29, 2022
«በትግራይ መንግሥት እርዳታ በትክክል ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ይቆጣጠራል»April 16, 2022

Leave a Reply