ሸኔን የተቀላቀሉ ወጣቶች እጅ እንዲሰጡና የክልሉን የኢኮኖሚ አብዮት እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበላቸው

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሳያውቁ አሸባሪውን የሸኔ ቡድን ለተቀላቀሉ የኦሮሞ ወጣቶች እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረበ፡፡ የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አሸባሪ ቡድኑ ሊያሳካ የሚፈልገው የፖለቲካ ዓላማ ኖሮት የማያውቅና ህዝባዊ መሠረት የሌለውም መሆኑን አስታውቋል። 

የሽብር ቡድኑ የኦሮሞ ህዝብ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዘርፍ ላይ ይህ ነው የሚባል አስተዋጽዖ ያላበረከተ ድርጅት መሆኑንም ነው ያመለከተው። መግለጫው፥ ቡድኑ የኦሮሞን ህዝብ ማንነትና ክብር አዋርዷልም ነው ያለው። ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ በፀረ ጭቆና ትግሉ ትልቅ መስዋዕትነት ከፍሎ ወደ ሚገባው ክብር ሲወጣ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ግን ተቃውሟል ያለው መግለጫው፣ ይባስ ብሎም ይህ አሸባሪ ቡድን የኦሮሞን ህዝብ እየገደለና እያዋረደ እንደሚገኝ አስታውቋል። 

የክልሉ መንግስት ዘመኑን የሚዋጅ፣ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ባሕል እውን በማድረግ ሠላም የመረጡትን አሸባሪ ኃይሎች ለመመለስ ጥረት አድርጓል ብሏል።አሸባሪ ቡድኑ ለሀገር ሲባል የተደረገውን ልመናና ተማጽኖ ከመቀበል ይልቅ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ክህደትና ውርደት መፈፀሙን ነው ያነሳው፡፡ 

የሸኔ ዓላማ ኦሮሞን ማዋረድ እንደሆነ በርካታ ወጣቶች ተረድተው በተለያየ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ ከጥፋት ተመልሰዋል ብሏል መግለጫው፡፡ የተቀሩትም የሸኔ አመራሮች ከአሸባሪው የህውሓት ቡድን ጋር መሰለፋቸውን ሲያዩ እና አባ ገዳዎች የሠላም ጥሪ ሲያቀርቡ በሥራቸው በመፀፀት እጃቸውን ለመንግስት እየሰጡ መሆኑም ተመልክቷል። 

ቢሆንም ግን አሁንም ቁጥራቸው በርካታ የሆነ ቡድኑን የተቀላቀሉ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች አላስፈላጊ መስዋትነት እየከፈሉ ነውም ብሏል መግለጫው፡፡ በስህተት አሸባሪውን የሸኔ ቡድን ለተቀላቀሉ የኦሮሞ ወጣቶች ተግባራቸው የተሳሳተ እና የኦሮሞን ህዝብ የሚያዋርድ እንደሆነ በመረዳት በወጣትነት እድሜያቸው እንዳይቀልዱ ጠይቋል። የነገን ጠንካራ መሠረት መገንባት የምንችለው በወጣትነት ዘመናችን ትክክለኛውን አስተሳሰብ ስንከተልም ነው ብሏል።

“ወጣቶች የሚገባቸው ትርጉም የለሽ መስዋዕትነት መክፈል ሳይሆን የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት አካል በመሆን ከክልሉ ጋር መበልፀግ ነው” ያለው መግለጫው፣ “ወጣቶች ባለን አቅምና እውቀት ከተጠቀምን የኦሮሞን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን መቀየር እንችላለን” ብሏል።የህዝቡ ሰላምና ብልፅግና እውን እንዲሆን ሰላማዊ ጥሪውን እንዲቀበሉና ወደ ልማት እንዲገቡ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ተሳስተው ሸኔን ለተቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply