የኢትዮጵያ መንግስት በቤኒሻንጉል እስር ቤት የነበሩ ሃያ አምስት የሱዳን ዜግነት ያላቸው እስረኞችን መፍታቱ ተሰማ። ውሳኔው ከወር በፊት የሁለቱ ሀገራት አካሂደውት በነበረው የጋራ ድንበር ጉባኤ ስምምነት መሰረት መሆኑን ተመልክቷል። ቀጣይ ስምምነት የተደረሰባቸው የጸጥታና ከንግድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንደሚተገበሩ ተገልጿል።
የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ በድንገት በኢትዮጵያ ያካሄዱትን ጉብኝትን ተከተሎ ቀደም ሲል በተደረሰው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያንን ከእስር መልቀቋ ቢገለጽም ስለ እስረኞቹ ማንነትና ሃላፊነት የተብራራ ነገር የለም። ይህ እስከታተመ ድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም አልተሰማም።
ከወር በፊት በሱዳን የብሉናይልና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሃላፊዎችና የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ባሉበት የሰላምና የደህንነት ጉባኤ መደረጉ ይታወሳል። በዚሁ መድረክ በተደረገ ስምምነት መሰረት አገራቱ በቀጣይ ማንኛውንም የጸጥታና የህንግድ ጉዳዮችን ደረጃ በደረጃ ተግብራዊ እንደሚያደርጉ ነው ፈጥኖ ደረሽ መግለጫን ጠቅሶ ሚድል ኢስት 24 ከካይሮ የዘገበው።
ሚድል ኢስት 24 የተሰኘ ድረ ገጽ የሱዳንን ራፒድ ሳፖርት ፎርስ የተሰኘ ( ፈጥኖ ደራሽ) መግለጫ ጠቅሶ እንዳለው የብሉ ናይል ክልል ሁለቱ አካላት ስምምነት የደረሱባቸውን ማናቸውንም ጉዳዮች፣ በተለይም ከጸጥታ ጋር የተያያዙ የድንበርና የንግድ ጉዳዮች ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አመልክቷል።
The governor of the Blue Nile region affirmed that the efforts of the two parties will continue to implement everything that was agreed upon, especially in the security fields related to borders and trade issues”.
የጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎን ድንገተኛና ያልታሰበ የኢትዮጵያ ጉብኝትን ተከተሎ ኢትዮጵያ 25 ሱዳናዊያንን መልቀቋ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተበላሸው ግንኙነት ሊሻሻል እንደሚችል ማሳያ ተደርጎ ተውሰዷል። ማናቸውም ኢትዮጵያ ላይ የተደቀኑ ፈተናዎች የሚጠነሰሱትና ሚጠመቁት ሱዳን ውስጥ እንደሆነ መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ነበር። በተለያዩ ወቅቶች ብረት አንስተው በውጊያ የተሳተፉ እንደነበሩም ይታወሳል።
ሕዝባዊ የተቃውሞ ማዕበል እየናጣት ያለችው ሱዳን አመጹ ከተነሳ ጀምሮ ከሰባ በላይ ዜጎቿ ተገድለዋል። በርካቶች ታስረዋል። ቀውሱና አለመረጋጋቱ እየሰፋ የሄደባት ሱዳን ለዚህ ይመስላል ፊቷን ወደ ሰላም ለማዞርና ” ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የመሬት ይገባኛል ጥያቄና ሌሎች ጉዳዮች በዲፕፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ አግባብ ብቻ ይፈታሉ። ከዚህ ውጭ ማንም ዓይነት ሌላ አማራጭ የለም” ሲሉ የላዕላይ ምክር ቤቱ መሪ ሌተናል ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን መናገራቸው ተሰምቷል።
በሌላ የሱዳን ዜና የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተናል ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን አዲስ ካቢኔ አቋቁመዋል። በዚሁ መሰረት በተበተነው ካቢኔ ምትክ ለአስራ አምስት አዳዲስ ሚኒስትሮች ሹመት ሰጠዋል። የመንግስቱ ልሳን የሆነው ሱና ይህንኑ ሹመት ይፋ አድርጓል።
በአብደል ፋታህ የሚመራው አንጋች ሃይል በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ የሚመራውን ሲቪል አስተዳደር ከፈነቀለ በኋላ ካቢኔ ሲቋቋም አዲስ ካቢኔ ማቋቋሙ የሱዳንን ሕዝብ ተቃውሞ የሚገታ ስለመሆኑ እስካሁን ፍንጭ አልታየም። ሕዝብ ወታደራዊ አገዛዝ በቃ በሚል ተቃውሞውን እንደቀጠለ መሆኑ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመክታሉ። እስርና የሃይል እርምጃ እንዲቆም ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማለት ያህል እየጠየቁ ነው።
“የግብፁ ፕሬዚዳንት ሲሲ ከካይሮ ወደ ካርቱም ሲበር ፣ የካርቱም ተወካይ ጋደሎ ወደ አዲስ አበባ በሯል። ነገሮች የተቀረዩ ይመስላሉ። ሱዳን ከዚህ ቡሀላ የግብፅን አሸማጋይነት አልቀበልም ብላለች። ኢትዮጵያ ወደቤቷ ተመልሳለች” ሲል ዘጠኝ ሚሊዮን ተከታይ ያለው አል አለሚ ሱዳን በፊት ለፊት ገፁ መዘገቡን በተደጋጋሚ የአረብኛ ጽሁፎችን ወደ አማርኛ እየመለሰ መረጃ የሚያጋራው ሱሌማን አብደላ በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሯል።