እስራኤል ከኢትዮጵያ ጎን መሆኗን አወጀች፣ በበርሃሌ አርሚ አምስት ተመታ

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ(ሄመቲ) ወደ ኢትዮጵያ ከመምብረራቸው በፊት በአውሮፕላን ማረፊያ ከእስራኤል የስለላ ሰዎች ጋር መምከራቸውን የሱዳን መንግስት አያውቅም ነበር። ንግግራቸው ካለቀ በሁዋላ ነው ገና “ይገኛናሉ” ሲል የሱዳን የመንግስት መገናኛ የዘገበው። ዛሬ ደግሞ እስራኤል ለኢትዮጵያ አስፈላጊውን ሁሉ እንደምታደርግ የፕሬዝዳንቱ የውጭ ግንኙነት አማካሪ ዚቪ ቫፕኒ በይፋ መናገራቸው ተሰምቷል። ይህ ዜና የትህነግን ስንብት የሚያመላክት፣ ከሄሜቲ ጉብኝት ጋር ንክኪ ያለው እንደሆነ ነገሩን የሚከታተሉ ጠቁመዋል። በበርሃሌ ትህነግ የሚተማመንበት አርሚ አምስት መመታቱና መከላከያ ጥብቅ እርምጃ መውሰዱ ተሰማ።

እስራኤል እንደ ወዳጅ አገር የምትፈልገው የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት ነው” ሲሉ የእስራኤል ፕሬዝዳንት የውጭ ግንኙነት አማካሪ ዚቪ ቫፕኒ ማስታወቃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። የጠቀሰውም እስራኤል ያለውን ኤምባሲ ጠቅሶ ነው። የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያን “አስፈላጊ በሆነ መንገድ ይደግፋል” ማለታቸውም ተዘግቧል።

በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የውጭ ግንኙነት አማካሪ ዚቪ ቫፕኒ በሁለትዮሽና በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል። አምባሳደር ረታ አለሙ ለፕሬዝዳንቱ የውጭ ግንኙነት አማካሪ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ማብራሪያ መስጠታቸውን ኢዜአ በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የእስራኤል ፕሬዝዳንት የውጭ ግንኙነት አማካካሪ ዚቪ ቫፕኒ “እስራኤል እንደወዳጅ አገር የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋት እንደምትፈልግና የኢትዮጵያ መንግስት አቋም ትረዳለች” ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሄደበት መንገድ የሚደገፍ መሆኑን ጠቅሰው፣የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያን “አስፈላጊ በሆነ መንገድ” እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄኔራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ(ሄመቲ) ከእስራኤል የደህንነት ሃይሎች ጋር ከተገናኙ በሁዋላ እስራኤል ይህን ማለቷ ጉዳዩ ተያያዥ እንደሆነ ተመልክቷል። ሄሜት የሚመሩት የፈጥኖ ደረሽ ሃይል ከትህነግ ጋር ግንኙነት የነበረውና ቀደም ሲል ይህ ግንኙነት በአቶ ስብሃት በኩል እንደነበር የሚያውቁ በቅርቡ ታላላቅ ዜናዎች እንደሚሰሙ አስታውቀዋል።

በርሃሌ ግንባር ትህነግ አስረከቦ የሸሸው ነው በሚል የአፋር አክቲቪስቶች ያሰራጩት

ይህ ያሳሰበው ትህነግ በዳግም ወረራ በአፋር በኩል የመከላከያና የአፋር ልዩ ሃይል በሌሉበት፣ የሰላም ንግግርና በሚስጢር እየተካሄደ፣ ለሰላም የሚበጅ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ በአባላና በበራህሌ ወረራ የፈጸመው የአርሚ-5 ሃይል ምሽጎች ተሰብረው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉና ከመመታት የተረፈ ሃይል መበተኑ ተገልጿል።

በዚህ ግምባር የተቆጣው የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት በቁጭትና በንዴት ጠላት መሽጎባቸው የነበረውን አከባቢዎች በጨበጣ ሳይቀር እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማድረግ የግልና የቡድን መሳሪያዎችን መማረኩ ተሰምቷል። መጠኑ ባይገለጽም የአገር መከላከያ ሃይል እርምጃ መውሰድ እንደጀመረ ታውቋል። በቆቦ በኩልም የውጊያ አቅጣጫውን ለማስፋት ሙከራ በመኖሩ መከላከያ ሙሉ ሃይሉን እንዲጠቀም ሊታዘዝ እንደሚችል እየተነገረ ነው። የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይል ከመንግስት ጋር እየመከረ እንደሆነ ታውቋል።

በምግበይ የሚመራው አርሚ-5 ትህነግ አለኝ የሚለው ሃይል ከሰማይ ላይ አየር ሃይል ልቡን እንዳጠፋው፣ የአፋር ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አካባቢውን ስለሚያውቁ የተበተነውን እያሳደዱና አንጠባጥቦ የሄደውን እየሰበሰቡ መሆኑን እማኞች ገልጸዋል። የአፋር ሰራዊት ወሳኝ የተባሉ ከፍተኛ ቦታዎችን ከጠላት መረከቡ ታውቋል።

በአብኣላና በመጋሌ ግምባር ውጊያው ቀጥሏል። በሁለቱ ግምባሮች የአፋር የምድር ድሮኖች ከሰማዩ ድሮን ጋር ተዳምረው ከመከላከያ ጋር ወደፊት እንደሚገፉና የትህነግን ሃይል እንደሚያመቱ ከስፋርው መረጃ የሚያገኙ የዳጉ አባላት አስታውቀዋል።

በከባድ መሳሪያ ሕዝብ አሸብሮ እንዲፈናቀሉ ያደረጋቸው ወግኖች በበረሃ ለከፍተኛ የውሃ ጥም መቸገራቸውን በዳጉ መረጃ እየተገለጸ ስለሆነ “እባካችሁን ውሃ አድርሱ” ሲሉ ዶክተር ኮንቴ በቲውተር ጋጻቸው አመልክተዋል።

ይህቺ ሕጻን በአባላ የትህነግ ወራሪ ሃይል ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ በደረሰ ቃጠሎ የተጎዳች እንደሆነች ገልጸው የአፋር አክቲቪስቶች ያሰራጩት ምስል ነው። በዚ መልኩ ነው ትህነግ ” መላክም ጎረቤት እንፈልጋለን” የሚለው

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply