ሳይርቅ በቅርቡ፣ሳይደርቅ በርጥቡ! ይሻላል።

«ከአፋር ክልል መንግስትና ከአፋር ህዝብ ጎን መሰለፍ፣ መስዋእትነት መክፈልና፣ ወረራውን መቀልበስ ለነገ የሚባሉ ጉዳዬች አይደሉም። ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም አፋጣኝ ድጋፎችን ማቅረብ የሁላችንም ድርሻ ነው።
ሳይርቅ በቅርቡ፣
ሳይደርቅ በርጥቡ! ይሻላል።»

For And Along The Afar People!

Yesuf Ibrahim

ወራሪው ኃይል ዳግም ጥፋት ለመፈፀም በአዲስ መልክ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል። በአንድ በኩል በእብሪት ለከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ሀብት ግብዓት እያደረገ በጎን “የረሀብና ችግር” ሲቃ ሲያሰማ ይውላል።

በሰላማዊ ከባቢ ውስጥ እስትንፋስ አይኖረኝም ብሎ ስለሚያምን ሽብርና ጦርነትን ግንባር ቀደም ምርጫዎቹ ያደረገ ሀይል ነው፣ ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ ተጨማሪ ጥፋቶችን እየፈፀመ ይገኛል!

በአሁኑ ሰዓት በአፋር በኩል አዲስና መጠነሰፊ ጦርነት ከፍቷል። የአፋርን ህዝብ እየጨፈጨፈና ሀብት እያወደመ ቀጥሏል። ሰሞኑን የአፋር ሀይሎች ጥቃት እንደከፈቱበት አስመስሎ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ ቆይቷል።

የይስሙላ ተበዳይነት ቅሬታውን ለአፋር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አቅርቦም ነበር። ጉዳዩን የመረመሩት የአፋር የሀይማኖት አባቶች የቀረበውን ስሞታ ሀሰትና መሰረተ ቢስ፣ ወረራውን ለመደበቅ ታስቦ በክፉ ልቦና የቀረበ መሆኑን በመግለፅ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በሂደት አጠናክሮ የገፋበት ጦርነት ሊደበቅ በማይችልበት ደረጃ ላይ ሲሆንበት በአማራ ላይ ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ አንድ ጊዜ “ከአፋር ጋር ሂሳብ ለማወራረድ”፣ ሌላ ጊዜ “ከአፋር ልዩ ሀይል፣ የፀጥታ ሀይሎችና የፖለቲካ ልሂቃን ጋር ሂሳብ ለማወራረድ” የሚሉ ቃሎችን ሲያስተጋባ ተሰምቷል።

በቅርቡ የወራሪው ሀይል ከፍተኛ አመራሮችና ጥብቅ ባለሟሎች መካከል በነበረ የመልዕክት ልውውጥ ወቅት (በትግርኛ ቋንቋ) ጦርነቱን የከፈቱት በአፋር ህዝብ ላይ ሂሳብ ለማወራረድ የታሰበ ስለመሆኑ አረጋግጧል።
የማስረጃውን መውጣት ሲገነዘቡ “ጦርነቱ ከአፋር ህዝብ ጋር ሂሳብ ለማወራረድ አይደለም!” የሚል የአደባባይ ድስኩር ይዘው ብቅ ብለዋል።

ዋናውን የጥቃት አላማ በግልፅ አሳውቀውና እየፈፀሙ ባለበት አግባብ በተቃራኒው ለማስረዳት የመዳከራቸው ሚስጥር ሊደበቅ አይችልም።

ለማንኛውም በአፋር ላይና በኩል የተከፈተውን የወረራ ጦርነት ሁላችንም ትኩረት ልንሰጠውና በፍጥነት ተረባርበን ልንመክተው ይገባል። የወረራውን አንድምታ፣ በህይወትና ንብረት ላይ እያስከተለ ያለውን ጥፋት ባግባቡ ማወቅ፣ ማሳወቅና ማጋለጥ ያስፈልጋል።

ከአፋር ክልል መንግስትና ከአፋር ህዝብ ጎን መሰለፍ፣ መስዋእትነት መክፈልና፣ ወረራውን መቀልበስ ለነገ የሚባሉ ጉዳዬች አይደሉም። ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም አፋጣኝ ድጋፎችን ማቅረብ የሁላችንም ድርሻ ነው።
ሳይርቅ በቅርቡ፣
ሳይደርቅ በርጥቡ! ይሻላል።

Primary goal of the Tigrean invading forces is to dismember Ethiopia. The Amhara and Afar territories are naturally proximate Ethiopian parcels. Now, the invading forces have launched their brutal attacks on the Afar People.
Noticing the rest of nonspeaking Ethiopia is verily discomforting.

ADVOCACY AND FIGHTING FOR AND ALONG THE AFAR NOW!

Related posts:

Leave a Reply