አረብ ኤምሬትስ ኢትዮጵያን ላይ የጣለችውን የጉዞ እገዳን ልታነሳ ነው

የተባበሩት አረብ ኤምሬት ኢትዮጵያ ላይ ጥላው የነበረውን የጉዞ እገዳ ልታነሳ መሆኑ ተሰማ። ተቋርጦ የነበረው የጉዞ ዕገዳ የፊታችን ቅዳሜ እንደሚነሳ ሮይተርስ ያወራው።

በቅርቡ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ትራንዚትን ጨምሮ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ የከለከለቻቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ደቡብ አፍሪካን፣ ኬንያን፣ ናይጄርያን እና ሌሎች ስምንት የአፍሪካ ሀገራትን ተጓዦችን እንደነበር ይታወሳል።

ሀገሪቷ ባለፉት አስራ አራት ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ አስራ ሁለት የአፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው የነበሩ ተጓዦች ወደ ሀገሬ መግባት አይችሉም ብላ እገዳ የጣለችው በአዲሱ የኮቪድ 19 ህዋስ ኦሚክሮን ሳቢያ ነበር። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ዕግዱ የሚነሳላቸው ሀገራት ታንዛንያ፣ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ቦትስዋና፣ ኢስዋቲኒ፣ ሌሶቶ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ እና ዚምባብዌ መሆናቸውን ዜናው አመልክቷል።

ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬት ጉዞ የሚያደርግ ተጓዥ ከመሳፈሩ ከ48 ሰዓታት በፊት ቀደም ብሎ ከኮቪድ ነፃ መሆኑን የማረጋገጥ ሰነድ መያዝ አለባቸው ተብሏል። በጉዟቸው መዳረሻ የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጠውን ማስረጃ ማሳየት ግድ መሆኑንን የሮይተርስ ዜና ያስረዳል።

Leave a Reply