አፋር ጄኖሳይድ እየተፈጸመ ነው፤ መንግስት የት ነው? እነዚህ ልጆች ምን አደረጉ?

በዳግም ወረራው አፋር ታምሷል። የመጣውን ወራሪ ሃይል እየደመሰሱ እንደሆነ ቢያስታውቁም ጦርነቱ በሌሎች ግንባሮች እየሰፋ ነው። ” መንገድ እናስከፍታለን?” በሚልና በቀይ ባህር አፋር የሚሳበበው ጦርነት ዝርፊያና ንጹሃንን በከባድ መሳሪያ እየጨረሰ መሆኑንን የሚመለታቸው አካላት ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል። መንግስት የት ነው? ምን እየሰራ ነው? መከላከያና አየር ሃይል ድፍን አጻፋዊ እርምጃ የማይወስዱበት ምክንያትም ግልጽ አልሆነም።

Image
በዚህ ሁሉ አቅጣጫ ነው ጦርነት የተከፈተው

ከሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ሲፈናቀል፣ ህጻናት ሲቃጠሉና ሲጨፈጨፉ፣ አዛውንቶች በየቦታው ሲወድቁ ዝምታው ከምን የመነጨ እንደሆነ መንግስት ማስታወቅ አለበት። በርግጥ ትህነግ ሰራዊቱን እንዲበትን፣ ትጥቁን እንዲፈታና ለኤርትራ በህግ የተፈቀድውን ስፍራ አስረክቦ ሰላም እንዲያወርድ የቀርበለትን ቅድመ ሁኔታ ላለመቀበልና አቅም እንዳለው ለማሳየት በአፋር ንጹሃን ላይ እሳት እንደለኮሰ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ እየገለጹ ነው። ይህ ቅድመ ሁኔታ የማይዋጥለት ከሆነ በሚገባው ቋንቋ፣ በክፋቱ ልክ፣ በጭካኔው መጠን፣ ባነደደው ሚዛን ዋጋው ከሰማይና ከምድር ሊከፈለው ግድ ነው።

የትህነግ ውጊያ አስገራሚ፣ አስጨናቂና ለውሳኔ አዳጋች እንደሆነ ይታወቃል። ኢትዮጵያ ቀለብ ትልካለች። ትራንስፖርት ታደርሳለች። ነዳጅ ትልካለች። መድሃኒትና ገንዘብ … የማትለከው የለም። የዚሁ ውጋት የሆነ ድርጅት ሃብት የሆኑ ተቋማት በመላው አገሪቱ ይነግዳሉ። ያተርፋሉ። ዶላር ያጥባሉ። ድጋፍ ያደርጋሉ። ይህ ሁሉ እየሆነ ለትህነግ ትንሽ ከጎደለበት የተባበሩት መንግስታት ሳይቀር ይሰበሰባል። ሚዲያው ሁሉ ይጮሃል። ትራፊ የሚጣልለት ስመ ኢትዮጵያዊ በብሄር ስም ይለፈልፋል። በዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ከትህነግ ጋር የሚደረገው ትንቅንቅ የዋዛ አልሆነም። እጅግ አሰቸጋሪና ውስብስብ ሆኗል።

ውስብስብ መሆኑን በመረዳት ሕዝብ ታግሷል። አሁን ግን ከትዕግስት በላይ በመሆኑ የዋሃን በትህነግ እባብነት መጠን ለማሰብ እየተገደዱ ነው። መንግስት ይህ ካልገባው ሊገባው እንደሚገባ የሚያስጠንቀቁም አሉ። የአፋር ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ የሚያልቅበት ምክንያት የለም። መንግስት ባስቸኳይ ክተት ይበል። የሚከፈለው ሁሉ ተከፍሎ ይህን ውጋት የሆነ ድርጅት ከህዝብ ለይቶ በሰራው ግፍ ልክ መክፈል ያስፈልጋል። ሰላም የማይወድና ንጹሃንን ቀዬቸው ድረስ እየመጣ የሚዘርፍበት፣ የሚገልበት፣ ንበረታቸውንና መጠቀሚያቸውን የሚያወድመበት ጉልበቱ መድቀቅ አለበት። ይህን ማድረግ የማይቻል ከሆነም ሽንፈትን አምኖ የሚፈልገውን ማድረግ ግድ ነው።

Image
የአፋር ምስኪኖች ላይ እየተፈጸመ ያለውና ዓለም ዝም ያለው ጭፍጨፋ ይህ ነው። ተራው የአፋር ነው። ሂሳ የሚወራረደው አፋር ላይ ነው

የትግራይ ምስኪን ሕዝብም ሆነ ሌሎች የአገሪቱ ነዋሪዎች አንድ መፍትሄ ይሻሉ። መንግስት ይህን መፍትሄ ማበጀት ግዴታህ ነው። ይህ ኢትዮያን አልፋታ ብሎ መርዝና ሴራውን የሚረጭ ድርጅት እስከመቼ ንጹሃንን እየጨረሰ ይኖራል። በአማራ ክልል የፈጸመው ግፋና ዝርፊያ፣ ውድመትና ብልግና ገና አሻራው ሳይጠግ ለዳግም ጥፋት ሲነሳ ዝም ማለት በምንም ሂሳብ አሳማኝ ምክንያት ሊቀርበለት አይችልም። ለማንኛውም የጀርመን ድምጽ ይህን ዘግቧል።

ሰሞኑን የትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ በአዲስ መልክ ባገረሸው ጦርነት ከአፋር አምስት ወረዳዎች 200 ሺህ ሰዎች ገደማ መፈናቀላቸውን ክልሉ አስታወቀ። የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደተናገሩት በተቀሰቀሰው በከባድ ጦር መሣሪያ የታገዘ ጦርነት በርካቶች በየመንገዱ ወድቀዋል። የተወሰኑትንም ወደ ህክምና ማድረስ ተችሏል። ባለስልጣናትና የዓይን እማኞች እንደሚሉት የሕወሓት ኃይሎች ወረራ ፈጽመዋል ባሉት የአፋር ዞን 2 ወረዳዎች ከፍተኛ ውድመትና ቀውስም ተከስቷል። በበረሃሌ በኩል የአፋር ተዋጊዎች የሕወሓት ኃይልን ተከላክለው በብርቱ ጉዳት እንዳደረሱበትም ተናግረዋል። 

መምህር መሐመድ ኑር ዑስማን በአፋር ዞን ሁለት ኢሬብቲ ከተማ ትምህርት ቤት በርዕሰ መምህርነት ያገለግላሉ። መምህሩ እንደሚሉት በዓብዓላ የከባድ ጦር መሣሪያ ተኩስ በትግራይ በኩል መከፈቱን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ እሪብቲ ከተማ ተፈናቅለዋል።ትምህርት ቤት ከተዘጋም ሁለት ወር ገደማ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ አሁን ደግሞ እሪብቲን ጨምሮ በአራት የአፋር ወረዳዎች ጦርነቱ በመስፋቱ መኖሪያ ከተማቸውን ለቀው ወደ አፍዴራ አቅራቢያ መሰደዳቸውን በመግለጽ ስላከባቢው አሁናዊ ሁኔታ አስተያየታቸውን አጋርተውናል፡፡ 

እንደ የአፋር ክልል ባለስልጣናት ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ 40 ኪ.ሜ. ገደማ በቅርብ ርቀት ላይ እንደምትገኝ በሚነገረው የአፋር ክልል ዞን 2 አብዓላ ከተማ የከባድ መሳሪያ ድብደባ መፈጸም የጀመረው የፌዴራል መንግስት ሰራዊቱ ወደ ትግራይ ከሚያደርገው ግስጋሴ ታቅቦ ባለበት እንዲቆይ ውሳኔ ባሳለፈበት ማግስት ነው። በአፋር ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ መሃመድ አህመድ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም. እሁድ ሌሊት በትግራይ ኃሎች ተከፍቷል ባሉት ድንገተኛ ጥቃት ደግሞ ጦርነቱ በአፋር ዞን ሁለት ወደ አራት ወረዳዎች ሰፍቷል፡፡ 

የአገር መከላከያ ሰራዊት በስፍራው እንዳልነበረና የአፋር ክልል ሃይሎች የመከላከል ስራ እየሰሩ ነው የሚሉት አቶ መሃመድ አህመድ ጦርነቱ እየተደረገበት የሚገኘው ይህ መንገድ መዳረሻው የጂቡቲ እና ሰመራ አካፋይ ወደ ሆነው ሰርዶ እንደሚወስድ ነግረውናል። እንደ ባለስልጣኑ ገለጻ በአዲስ መልክ ጦርነት በተከፈተባቸው የአፋር ከተሞች ውድመትና ዝርፊያም ተፈጽሟል፡፡ 
የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን በበኩላቸው ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት አሁን ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ባሉት እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው ጦርነት 200 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል። 

ጦርነት በሚካሄድበት ስፍራ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ማድረስ እንዳልተቻለ የገለጹት አቶ መሃመድ ሁሴን አከባቢው ላይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ በከባድ መሳሪያ የተጠቁ ሰላማዊ ዜጎችን በተወሰነ መልኩ ወደ ህክምና ማእከላት መውሰድ መቻሉንም ገልጸዋል። ወደ ትግራይ የሚወሰደውን የእርዳታ ቁሳቁስ ለማጓጓዝ ብቸኛ መንገድ የሆነው ጦርነቱ የተስፋፋበት የአብዓላ ሰመራ ኮሪደር የተዘጋው በህወሓት ጸብ አጫርነት እንደሆነ በመንግስት በኩል ሲነሳ፤ ህወሓት በፊናው ተፈጽሞብኛል ያለውን ከበባ በመስበር የርዳታ ቁሳቁሶችን ማስገባ መንገድ ፍላጋ ላይ እንደሆነ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡ 

ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ

Leave a Reply