ዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ተጠናቀቀ

በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ያስገነባው የዳያሊሲስ ማዕከል ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ሰላሳ የዳያሊሲስ ማሽኖች የሚኖሩት ማዕከሉ የህፃናት ማቆያ ክፍል፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣የቀዶ ጥገና ክፍል፣የሀኪሞች ክፍል፣የታማሚዎች ክፍል፣ለይቶ ማቆያ ክፍል እንዳለው ተጠቁሟል፡፡እንዲሁም ሀኪሞች ታካሚዎቻቸውን በቅርበት የሚከታተሉበት ነርስ ስቴሽን ያለው ሲሆን ደረጃውን የጠበቀ የመፀዳጃ ቤት እንዲሟሉለት ተደርጓል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ለ ሰላሳ ታካሚዎች አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለውና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ይህ ማዕከል አሁን ላይ የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡በቀጣይም ማሽኖቹ ተገጥመው ወደሙሉ አገልግሎት ሲገባ ለኩላሊት ታካሚዎች ከፍተኛ እፎይታን ከመስጠቱም ባለፈ የከተማችንን የህክምና ቱሪዝም መዳረሻነት ጉዞ ያፋጥናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ፅ/ቤት የተገኘ መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ አመልክቷል።
Related posts:
"ግጭት አድራቂ የሰላምና እርቅ መድረኮች…"
አዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ጥብቅ የስነምግባር ቁጥጥር ይጀመራል
በባለቤታቸው የጥምባሆ ጭስ ካንሰር - "አልወቅሰውም"
30 የኩላሊት እጥበት ማሽኖችን - ትልቅ እፎይታ
“እኛ ምንም የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የወዳጃቸውን የአደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ
በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 28 ሺህ ዜጎች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ
ይህ በኢትዮጵያ ለማህበራዊም ሆን ለዩቲዩብ ዜናነት አይበቃም፤ እንኳን ደስ አላችሁ!!
በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል