ኦቻ – በሽራሮ አቅጣጫ፣በወልቃይት ፀገዴ፣በምዕራብ ሁመራ ውጊያ መኖሩን ሰማሁ አለ”በተጠቀሱት ቦታዎች ትንኮሳ ቆሞ አያቅም”

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኦቻ ከየአቅጣጫው እንደሰማና “ሊተነበይ የማይችል” ሲል የጦርነቱን ሁኔታ አመልክቶ ባወጣው ሪፖርት በደቡብ ምዕራብ ሽራሮ ከተማ፣ በወልቃይት ፀገዴና በምዕራብ ዞን ሁመራ ውጊያ እንዳለ ገልጿል። በተለያዩ አቅጣጫዎች ትንኮሳ እንዳልቆመና አልፎ አልፎም የሱዳንን ኮሪዶር ለማስከፈት ተደጋጋሚ የማጥቃት ሙከራ ቢደረግም ሊሳካ እንዳልቻለ የአማራ ክልል፣ የአካባቢዎቹ አስተዳደሮች፣ እንዲሁም የመከላከያ ባለስልጣኖችን የሚጠቅሲ ” የተለመደ ነው” ሲሉ ሚዛናዊ እንዳልሆነ ለሚወቀሰው የኦቻ ሪፖርት ብዙም እንደማይገረሙ ያነጋገርናቸው አመልክተዋል።

“በትግራይ ውጊያ አለ” ያለውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ኦቻን ጠቅሶ ቢቢሲ በደቡባዊ በሽራሮ ከተማ ጦርነት መኖሩን ሲያስታውቅ፣ ተዋጊዎቹ እነማን እንደሆኑ አልገለጸም። ወሰኑ ከኤርትራ ጋር ቢሆንም ሪፓርቱም ሆነ ቢቢሲ ኤርትራን አላነሱም።

በሌላ በኩል ውጊያ አለ በሚል ኦቻ የገለጸው ወልቃይት ጠገዴና ሁመራ ነው። “ምዕራብ ትግራይ” ሲል ትህነግ ጠቅልሎ የሚገልጸው ከአማራ ክልል በሃይል ተውስዶ የቆየውንና አሁን “በላቤቶቹ ተቆጣጥረውታል” የሚባለውን የውልቃይት ጠገዴ ሰፊ ለም መሬት አካባቢ ነው። ይህ “ምዕራብ ትግራይ” ተብሎ ላለፉት 27 ዓመታት የተሰየመው አካባቢ የማንነትና የባለቤትነት ጥያቄ ሲቀርበበት የኖረ ነው። በወቅቱ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ትህነግን ወክለው ይዘውት በነበረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወነበራቸው ጉዳይ በተደጋጋሚ ቢቀርብላቸውም ምላሽ ሳያገኝ፣ ጥያቄውን ያቀረቡ የሕዝብ ወኪሎች እንዲታሰሩ እየተደረገ እስከ ለውጡ መቆየቱ ይታወሳል።

የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በደቡብ ምዕራብ ሽራሮ ከተማ፣ በወልቃይት ፀገዴ፣ በምዕራብ ዞን ሁመራ አቅጣጫና፣በአፋር ክልልም መጋሌ፣ ኢሬብቲ፣ በራህሌ፣ ዳሎልና አብዓላ፣ በሰሜን ጎንደር በዋግ ኸምራ እንዲሁም በሰሜን ወሎ ዞኖች ውጊያ እንዳለ በትናትናው ዕለት ባወጣው ማስታወሻው እዳስታወቀ የዘገበው ቢቢሲ ከአፋር ክልል ውጪ በሌሎች አውደ ውጊያዎች የደርሰውን ጉዳት በስፋት በሪፖርቱ ስለመካተቱ ያለው ነገር የለም።

በወልቃይትና ሁመራ አቅጣጫ ከሃያ ጊዜ በላይ የማጥቃት ሙከራ ተደርጎ መምከኑና ሁሉም ነዋሪ በሚባል ደረጃ ታጥቆ በንቃት የሚጠብቀው አካባቢ እንደሆነ ከትናንት በስቲያ አማራ ማስ ሚዲያ ያነጋገራቸው ሲያስታውቁ ተሰምቷል። እነዚህ ወገኖች ትህኮሳና ዳግም ወረራ ለመፈጸም የሚደረገው ሙከራ የተለመደ ግን የማይሳካ እንደሆነ ሲናገሩም ተድምጧል። ኦቻ ስፍራዎቹን ጠቅሶ እንደ አዲስ ውጊያ ተቀሰቀሰ ከማለት ውጪ ሌላ ያለው ነገር የለም።

ሪፖርቱ ጦርነቱን ተከትሎ ዜጎች ለአደጋ መጋለጣቸውን አስታውቋል። ሰብዓዊ እርዳታን ለማድረስም እንቅፋት እንደገጠመውም አመልክቷል። በአፋር በተከሰተው ጦርነት ባልፈው ሳምንት ብቻ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ኦቻ አመልክቷል። ክልሉ ከሁለት ቀን በፊት ይፋ እንዳደረገው በትህነግ ዳግም ወረራ የተፈናቀሉት ነጹሃን ከ200 ሺህ በላይ ናቸው። ኦቻ “በአስር ሺህ” ሲል የገለጸውን ሪፖርት ምንጭ አጠራጣሪ እንደሆነ ቢትውተር ገጻቸው ወቅሰው የገለጹ አሉ።

በትግራይ ክልል በሰመራ- አብዓላ-መቀለ ኮሪደር እንዲሁም በአፋር እና በአማራ ክልሎች ለተጎዱ አካባቢዎች እርዳታ ማቅረብ አለመቻሉን ኦቻ ሲያስታውቅ፣ ለወትሮው ሲያደርግ እንደነበረው ችግሩን የፈጠረውን አካል ለይቶ አልወቀሰም።

በሪፖርቱ በትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የተደረጉ ውጊያዎችን ተከትሎ ከአፋርና አማራ ክልሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ ተፈናቃዮች ወደ ውቅሮ፣ አፅቢና፣ አጉላዕ ወረዳዎች መድረሳቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደርም እንዲሁ የተፈናቀሉ እንዳሉ ኦቻ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል። ለተፈናቃዮችም ምግብ፣ የድንገተኛ አደጋ መጠለያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች፣ ውሃ እና የንፅህና መጠበቂያዎች እና የህክምና አገልግሎት ማቅረብ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁሟል።

ሪፖርቱ በትግራይ ከፍተኛ የሆነ የርዳታ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ቁጥር ጠቅሶ አመልክቷል። የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደተዘጉ መሆናቸንና ቤንዚን ችግር እንዳለም ተቁሟል። እርዳታ እህክና ነዳጅ ጭነው የቆሙ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ጠቅሷል። የአልሚ ምግብ ክምችቱም ሆነ የእህል መጋዘኑ መመናመኑን አሁን በቁጥር ጠቅሶ ስጋቱን አኑሯል።

ትግራይን አስመልክቶ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ማንበብ ከወደዱ ኦቻ ላይ ያንብቡ

You may also like...

Leave a Reply