አለምን ያንጫጫው ፎቶ!

በሀገረ ሊባኖስ፣ ቤይሩት ከተማ በሚገኝ አንድ ሰፈር ውስጥ ነው። በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የአስር ዓመት ሶሪያዊ ልጅ ሑሴን ይባላል። ሑሴን ቆሻሻ ከሚጠራቀምባቸው ገንዳዎች እየሄደ ሰዎች ተጠቅመውባቸው የጠሏቸውን የፕላስቲክ ኮዳዎች በመሰብሰብ በትንንሽ ሳንቲም የመሸጥ ልማድ
አለው። ባለፈው ሰኞ ቀን ይህንኑ ሊፈጽም ሄዶ ሳለ ግን በገንዳው ውስጥ መጽሐፍ ያገኛል። እርሱም ኮዳዎችን
መፈለጉን ትቶ መጽሐፉን እያገላበጠ ማየትና መፈተሽ ጀመረ።

ሶሪያዊው ልጅ ይህንን ሲያደርግ “ሮድሪግ ማግሐሚዝ” የሚባል ኢንጂነር በዛው መንገድ ላይ ሲያልፍ አየው። በሁኔታው ስለተገረመ ቀርቦ ወደ ሁሴን በመምጣት ሑሴንን ፎቶግራፍ አነሳው።
“መጽሐፉ ለትልቅ ሰው የተዘጋጀ መጽሐፍ ቢሆንም ሁሴን ልክ ቤቱን መጽሐፉ ውስጥ ያለ ይመስል እያገላበጠ መጽሐፉን እያየው ነበር።

ኢንጂነር ሮድሪግ ሶሪያዊው ህፃን ሑሴን መጽሐፉን የሚያነብበትን ተመስጦ ሲያስረዳ “በመጽሐፉ ውስጥ ለእርሱ የተዘጋጀለትን ልዩ ቦታ የሚፈልግ ነበር የሚመስለው” በማለት ነው የገለጸው። ለግማሽ ሰዓት ያህልም ሌሎች ችግሮቹን ሁሉ ረስቶ መጽሐፉን በተመስጦ ማየቱን ይቀጥላል።

ሁሴን ጠዋት ጠዋት(ልክ እንደ ፈረቃ) ትምህርቱን ቦርጅ ሃሞድ አካባቢ እስከ ስድስት ይማራል። ከሰዓት ከገንዳ የተራረፈ ነገር በመለቃቀም በሽተኛ አባቱንና አራት እህቶቹን ያግዛል።

ኢንጂነሩ ቀረብ ብሎ አብሮት ሰልፊ ፎቶ ለመነሳት ሲጠይቀው መጀመሪያበጥርጣሬ አይቶት ይስማማና አብሮት ፎቶ ይነሳል።

ሊባኖሳዊው ኢንጂነር የሶሪያዊውን ልጅ ፎቶ በካሜራው ቀርጾት በዚያው ዝም አላለም። በቲውተር፣ በፌስቡክ እና በሌሎች የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ በመለጠፍ ለጓደኞቹ አጋርቷል።

ፎቶው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከዐረቡ ዓለም እና ከምዕራባዊያን ሚዲያዎች እና የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በመድረስ መነጋገሪያ ሆኗል።

ማግሐሜዝ በጎ አድራጎት ማህበራትን በማነጋገር ለ ሁሴን ትምህርቱ ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርግ የተሻለ አኗኗር ለቤት ኪራይ እና መሰረታዊ ነገሮችን የሚሟሉበት ሁኔታ ለመፍጠር እየጣረ ነው።

ሶሻል ሚዲያ በትክክል ከተጠቀሙበት ብዙ አዎንታዊ ለውጦችን ሊያመጣ የሚችል ትልቅ መሳሪያ ነው። ስለዚህ እናስብበት።

(ምንጮች፣ የአህላም ሙስተጋነሚ ፌስቡክ ገጽ፣ አል-ጀዚራ፣ አል-ዐረቢያ

Via Woldia Times

Leave a Reply