በባኮ ቲቤ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ ሾቦካ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ሁለት ከባድ ተሽከርካሪዎች እርስ በርስ በፈጠሩት ግጭት የተከሰተ ነው።

በተከሰተው አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ÷ግጭቱን ተከትሎ በተፈጠረው የእሳት ቃጠሎም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ርብርብ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ እና የትራንስፖር አገልግሎት መቀጠሉም ተገልጿል፡፡ via OMN

Leave a Reply