አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ተሰጠ

ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል።

በዚህ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ተሰቶባቸው የነበሩት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይገኙበታል። ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መጥሪያ እንዲያደርስ የታዘዘው የፌደራል ፖሊስ በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በኩል አፈላልጌ ላገኛቸው አልቻልኩም ሲል መልስ ሰቶ ነበር።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የሮማን ፉውንድሽን እንደሚሰሩና በመንግስ ፖሊስ እጀባ እየተደረገላቸው እንደሚቀሳቀሱ ጠቅሰው ይህ በሆነበት ሁኔታ ፖሊስ ላገኛቸው አልቻልኩም በማለት የሰጠው ምላሽ  አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ በድጋሚ ትዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፖሊስ አቶ ሀይለማርያምን ደሳለኝን ካሉበት አፈላልጎ አስሮ እንዲያቀርባቸው ትዛዝ ሰቷል።

ምንጭ፦ T.me/ethio_mereja

Leave a Reply