“የኢትዮጵያ ጦር የበረበራ ወደብን ሊከረብ ይችላል”

  • ከሁለቱ መሪዎች ውይይት ቀጥሎ የወጡ መረጃዎች ምን ይላሉ


የኢትዮጵያ ጦር የበረበራ ወደብን ሊከረብ ይችላል። ከዚህም ከፍ ብሎ በኦማን የባህር ዳርቻ ላይ ዝቅ ብሎ ለሶቆጥራና በሱማሊያ የባህር ክልል ውስጥ መልሶ ሊሰፍር ይችላል። ይህ ዜና የተዘገበው የሞሳድ ቅልቡ ጆርዳን ታየምስ ጋዜጣ ላይ ብቻ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ ትልቅ የመረጃ ምንጭና የኢንተለጀንስ መረጃዎችን ማግኘት የሚችል ጋዜጣ ላይ ነው። ምናልባት በሚል ርዕስ የተጀመረው ይህ ዜና የሌሎችን ትኩረት ላለመሳብ ፍልጎም ሊሆን ይችላል።
.
የተባበሩት አረብ ኤምሪትስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዶላር እረሀብ ቸገረኝ ካላት መልሶ እንዲያገግም ባንኩን አለኝ የሚላት አጋሩ ናት። የጠሚ አብይ አሕመድ እና የዛይድ ልጅ መሀመድ ያላቸው የጋራ ጎደኝነት አስቸጋሪ ነው ይላል ይህ ጋዜጣ። ዱባይ የኢትዮጵያ መተንፈሻ የመሆን እድል ያገኘችው እና በኢትዮጵያውያን የላቀ ክብር የተሰጠችው በአብይ አሕመድ ዘመን ነው በሌሎች መንግስታትን ዘመን ይህ ወዳጅነት አልነበረም።

በሰሜኑ ክፍል ካለው ጦርነት ጋር ስሟ የሚነሳው ሚጥጥየዋ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ የክፍ ቀን ወዳጅ አገር መሆኗን ከምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ተወካይ ፊልትማን ጋር የነበረው ክርክር ላይ መሆኑን ጋዜጣው በስሱ ዳደስስ አድርጎታል። ሰፋ ብሎ ሊገባበት ያልቻለው እነዚህ መረጃዎች በኢንተለጀንስ የመረጃ ቋቶች ላይ ብቻ ስላሉ ነው።

የሆነው ሆኖ አረብ ኤምሬትስ ከመቸውም ጊዜ በላይ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ ብላ መከራከር ከጀመረች ቆየት ብላለች። የግብፅን ትችት ወደኋላ ብላ ለኢትዮጵያ የታመነችበት ሚስጥር ባይገባንም፣ ከኢትዮጵያ ምን እንደፈለገች ግን አልታወቅም ። ምናልባት ግን የዱባይ ህዝብ መሰረታዊ የግብር ፍጆታ ከኢትዮጵያ ጥቋቁር ማሳዎች የሚሸፈን ሊሆን ይችላል። ወደፊት ያለ ቅርብ ነው።
1 ሚሊየን ዜጋ ያላት ሚጥጥየዋ ግን ሀብታሟ ዱባይ ዜጎቿ መሰረታዊ የግብርና ፍጆታቸውን ሙሉ በመሉ ከኢትዮጵያና ከቱርክ መሬቶች ብቻ ሊያደርጉ ይችላሉ። ወደፊት የዛይድ ልጅ ትራክተሮች የማንን ክልል መሬት እንደሚያርሱ የጆቢራ ገደሉ እብድ ይወቀው። ምናልባት ሁመራ ወይም ምስራቅ ጎጃም፣ ወይስ ወለጋ ወይስ አዋሽ ወይስ ጋምቤላ ወይስ ጎዴ ወይስ መተከል . ብቻ ግን ማረሳቸው አይቀሬ ነው።
.
የኢትዮጵያ ጦር (መከላከያ ስራዊቱ የወርሃዊ ደመዝ ክፍያ ሊጨምር ይችላል)
ይህ መንግስት ያስቀመጠው የወደፊት እቅድ ቢሆምን፣ የኢትዮጵያ አጋሯ ኤምሪትስ
ግን ይሄንን ተቋም ለማገዝ ከመንግሥት ጋር ተስማምተዋል። በነገራችን ላይ የግብፅ ጦር ደመወዝ በሳኡዲና በአሜሪካ መንግስት የሚሸፈን መሆኑን ስንቶቻችን ነን የምናቀው፣ የሱዳን ጦር አሁንም ድረስ በሳኡዲ መንግስት ነው ደመወዝ የሚሸፈንለት። የኢትዮጵያ ጦርስ ማን ሊረዳው ይሆን ? በርግጥ የኢትዮጵያ መንግስት የሌሎች ጥገኛ የመሆን ፍላጎት የለውም፣ የሚለው ይህ ዘጋባ፣ ነገር ግን በወዳጅ አገሮች ሰቶ መቀበል ባህል መልሶ መደጋገፉን እንደመርህ ያየዋል።
.
በሌሎች አይን በወታደራዊ አቅሟ በንቄት የምትታየው ኤምሬትስ፣ በግብፅ ጦር የሚተማመነውን የገልፉን አገራት መርህ ጥሳ በጥቋቁረቾ የአድዋ ልጆች ላይ ፊቷን አዙራለች። ከእንግዲህ ቡኋላ የግብፅ ጦር ለአረቡ አለም ምናቸውም ላይሆን ይችላል። ለዛም ነው የኢትዮጵያ ጦር የዱባይ ጦር የሰፈረበትን የበርበራን ወደብ ሊረከብ ይችላል የተባለው። የአሜሪካ ጦር በቅርቡ የሰፈረበት የኦማንና የሱማሌ የየመን ሶቆጥራ ወደብ አካባቢ መልሶ የኢትዮጵያ ጦር ሊሰፈር ይችላል። በወታደራዊ አቅሟ ትንሽ ቁጥር ያላት አረብ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ያላት መተማመን በቀላሉ ሊታይ አይገባም። ጥቁቁረች የኢትዮጵያ ወታደሮች ትጥቅና አቅም ወረሀዊ ክፍያ ከዚህ ቡኋላ ሊጨምር ይችላል የሚለው ዘገባ ከዚህ የመነጨ ነው።
.
በመጨረሻም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርብ ቀን ኤምሬትስን
ይጎበኛሉ። እዚህ ላይም ሌላ ድል አለ። ከላይ ወደታች በወረደው ፁሁፌ ላይ ሙሉ ትኩረት የሚሰጠው ስለ ቀይባህር ፖለቲካ ጉዳይ ነው። ተቀናቃኞቻችን እነ ኬኒያ ግን ይሄንን እንቅስቃሴ ከነ አሜሪካ ጋር ሆነው አይመክሩበትም አንልም። ቢሆንም እስራኤል አለች ። የእስራኤል አጋር ሀብታሟ ዱባይ ምን አይነት ሚና መጫዎት እንዳለበት ታስብበት።
.
ስለ ቀይ ባህር ፍጥጫ በሌላ እርዕስ እመለሳለሁ። በዙ መረጃና የማስረጃ ምንጭ ያለበት ለኛ የሚጠቅሙ ነገሮች የሚበዙበት ጉዳይ ነው።

See also  "አሸባሪው ሃይል ህጻናትና አዛውንቶችን በጅምላ ጨፍጭፏል"አፋር

Suleman Abdela

Leave a Reply