የተመድ ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሃመድ ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሀፊ አሚና መሃመድ ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ።

ምክትል ዋና ጸሀፊዋ ኮምቦልቻ ከተማ ሲገቡ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበርን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተቀብለዋቸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር አህመድ የሱፍ እንደገለጹት በምክትል ጸህፊዋ የተመራው ልዑክ በጦርነቱ የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ይመለከታል።

ልኡኩ አሸባሪው ህወሀት በከፈተው ጦርነት ቤተሰቦቻቸውን ያጡ፣ አካላቸው የጎደለና የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማትን እንደሚመለከት ተናግረዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ስለደረሰው ሁለንተናዊ ውድመትና ጥቃትም ለልዑክ ቡድኑ ገለጻ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

ምክትል ዋና ጸሀፊዋና የልዑካቸው በዞኑ በሚኖራቸው በቆይታ ከአመራሩና ባለድርሻ አካላት ጋርም ውይይት ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼ (ኢዜአ)

Leave a Reply