ተደራጅተው የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አሰታወቀ


ተደራጅተው የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አሰታወቀ።

የግለሰቦችን መኖሪያ ቤት በሌሊት በመስበር ስርቆት ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል 23 የተለያየ መጠን ያላቸው ቴሌቭዥኖችን ማስመለሱን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጸዋል።

ጥር 11 ቀን 2014 ዓ.ም ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ሁለት ቴሌቪዥኖችን ሰርቀው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1 አ/አ 29071 ላዳ ታክሲ ሲያጓጉዙ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪዎች በወንጀል መከለካል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደም የሰራቋቸውን የተለያየ መጠን ያላቸውን 23 ፍላት እስክሪን ቴሌቭዥኖች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አጠና ተራ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በ1ኛው ተጠርጣሪ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው ማግኘቱን መምሪያው አሳውቋል፡፡

በተለያዬ ጊዜ ቴሌቪዥን የተሰረቀባቸው ግለሰቦች ሆኑ ተቋማት አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በግንባር በመቅረብ ንብረታቸውን መውሰድ እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጸዋል።

የስርቆት ወንጀል የሚፈፀመው ጨለማን ተገን በማድረግ ስለሆነ ህብረተሰቡ ተገቢው ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢዲስ አበባ ፖሊስ አሳስበዋል።

(ኢ ፕ ድ)

You may also like...

Leave a Reply