የአሸባሪው ህወሃት ወራሪዎች የአፋር ወረዳዎችን የተቆጣጠሩበት ሚስጥር!

ወራሪው ጁንታ የደርግን አገዛዝ ለመገርሰስ ለ17 አመታት ከአፋር ጋር አብሮ ታግሏል በመሆኑም የአፋር ህዝብን የዉጊያ ስልትና ጀግንነት በሚገባ ተረድቷል። ወራሪው የትኛውንም የአፋርን መንደር ለመያዝ ከአፋር ጋር በክላሽና በብሬን ተዋግቶ እንደማይዝ በሚገባ ያውቃል። ለምሳሌ-አንድ ምሽግ ውስጥ 100 የአፋር ተዋጊ ካለ ጠላት ያንን ምሽግ ለመቆጣጠር ምሽጉ ውስጥ ያለው 100 ተዋጊ በሙሉ ማለቅ አለበት። የአሁኑ ወጣት የአፋርን ይሄን ባህሪይ አያውቁም ግን የወራሪው ጁንታ መሪዎች ጠንቅቀው ያውቃሉ።

እናም ወደ አፋር ለሚያመጧቸው ሃይላቸው አፋርን በዉጊያ አትችሉም መጀመሪያ ሞክሩ ግን እልህ ውስጥ አትግቡ አፋር ወይ እናንተን ይጨርሳል ወይ እራሱ ያልቃል እንጂ አያፈገፍም ከምሽጉ ፈቀቅ አይልም በማለት ለሃይሎቻቸው ቀድመው ይናገራሉ፡ በአፋር ግምባሮች የተያዙ ምርኮኞች ይሄን ምክር እንደተመከሩ አረጋግጠዋል። ወራሪው ሃይል ይሄን ስለሚያውቅ አሁን የተቆጣጠሩት አከባቢዎች የያዘው በድብቅና በድንገት ጥቃት በመክፈት እንዲሁም ከርቀት መድፍ በመተኮስ በመበተን እንጂ በእግረኛ ሃይል በዉጊያ አሸንፎ በፍፁም አንድ መንደር አልያዘም ይዞም አያውቁም።የአፋር ህዝባዊ ሃይል ደግሞ ሁሌ በራሱ የውጊያ ስልት በጠላት የተያዙባቸውን አከባቢዎችን እስከ መድፎቻቸው ይቆጣጠራሉ ።በዚህ ምክንያት ወራሪው ሃይል በጭካኔና በጥላቻ ከተሞች ላይ መድፍ በመተኮስ የአፋርን ንፁህን በመጨፍጨፍ ያላቸውን ጥላቻ ከመግለፅ ባለፈ የአፋርን ሞራል ለመጉዳትም ጭምር ነው ግፍ የሚፈፅመው።

በታሪክም የአፋር ህዝብ ድንበር የሚኖሩ ህዝብ በመሆኑ በተለያዩ ዘመናት የውጭና የውስጥ ወራሪዎች በተለያዩ ግዜያት ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱበት የመጣ በመሆኑ የአፋር ህዝብ ሁሌም ለጠላት ዝግጁ የሆነ ጠላት በአንዱ አቅጣጫ ከመጣ ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ ራሱን ያስከብራል። የሚገርመው አንድ የአፋር ወጣት እድሜ 14 ከሞላው ጥይት ይገዙለታል ይሄ ደግሞ የአፋር ቋሚ ባህል ነው። ግን ኢትዮጵያን ማንበርከክ አይቻልም ብሎታል ጀግናው የአፋር ህዝብ።

Ahmed Habib Al-zarkawi

Leave a Reply