“ከኛ ጋር ታስረው የነበሩ እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም“

ከኛ ጋር ታስረው የነበሩ እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ እነ አብዲ መሀመድ ኡመር ተቃውሞ አሰሙ። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተገኝተው ተቃውሞ ያሰሙት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት እነ አብዲ መሀመድ ኡመርን ጨምሮ 17 ተከሳሾች ናቸው።

ተከሳሾቹ በ2010 በሱማሌ ክልል በጂጂጋ ከተማና በተለያዩ ዞኖች በተፈጠረ የዕርስ በዕርስ ግጭት ጋር ተያይዞ በጥር ወር ከ2011 ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወሳል።

… ዚህ በኋላ ፍርድ ቤት አንቀርብም እኛ ከእስር ከተፈቱ ግለሰቦች የተለየ ምንም ወንጀል አልፈጸምንም፣ ስለዚህ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ታስረን ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

አብዲ መሀመድ ኡመር

ተከሳሾቹ ወንጀሉን አለመፈጸማቸውን ገልጸው የሰጡትን የዕምነት ክህደት ቃል ተከትሎ ዓቃቢህግ ምስክር ማሰማት የጀመረ ሲሆን አጠቃላይ ከ46 በላይ ምስክሮችን አቅርቦ በችሎት አሰምቶ ነበር።

ችሎቱ ለሶስተኛ ዙር ቀሪ ምስክር ለመስማት በያዘው ቀጠሮ ዛሬ የተሰየመ ሲሆን፣ ችሎቱ ሥራውን እንደጀመረ ተከሳሾቹ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት መቅረብ የለብንም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።

አብዲ መሀመድ እጃቸውን በማንሳት ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት አንቀርብም እኛ ከእስር ከተፈቱ ግለሰቦች የተለየ ምንም ወንጀል አልፈጸምንም፣ ስለዚህ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ታስረን ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

በተጨማሪም አብዲ ከአማራ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከትግራይ እና ከሌሎችም ከተፈጸመው ወንጀል የኛ በምን ይለያል ግድያ በተፈጸመበት ሁኔታ ሌሎች ሳይጠየቁ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ጉዳይ የለም። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ እኛ ፍርድ ቤት አንቀርብም ፍርድ ቤቱ የራሱን ውሳኔ ይስጥበት ሲሉ ከእስር አቤቱታ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ሌሎችም ተከሳሾች ከሌሎች ተነጥለን መታሰራችን አግባብ አደለም ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

ከሳሽ ዓቃቢህግ በበኩሉ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ይስጥበትና ክርክሩ ይቀጥል ሲል ችሎቱን መጠየቁን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች። ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ ከእስር የተፈቱ እስረኞችን ክስ ያቋረጠው ፍትህ ሚኒስቴር መሆኑን ገልጿል።

አስተያየታቸዎውን ለፍትህ ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚችሉ የገለጸው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ መርምሮ ተገቢውን ትዛዝ ለመስጠት ለፊታችን ሀሙስ የካቲት 3ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ታውቋል።

(አዲስ ማለዳ)

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
"መስከረም አበራ የአማራ ክልልን ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራች ነው" ሲል ፖሊስ ገለፀMay 23, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
የጉምሩክ የታክስ ኢንተለጀንስ ባለሙያ ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተያዘMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022

Leave a Reply