”አካታች ብሔራዊ ምክክር በማካሄድ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተግባብተን መቋጫ ማብጀት ይኖሩብናል ”

አቶ ብናልፍ አንዷለም የሰላም ሚኒስቴር ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር “አካታች ብሔራዊ ምክክሩን ከማሳካት አንፃር የምሁራን ሚና ” በሚል ርዕስ ከዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር ውይይት ተካሄደ ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም አካታች ብሔራዊ ምክክር ማካሄድ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የቆየ ምኞት እና ተነሳሽነት አለ ብለዋል ።

ለዘመናት ይዘናቸው የመጣናቸውን ችግሮች መፍታት የምንችለው አካታች ብሔራዊ ምክክር በማካሄድ በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ስንችል ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህን ተግባር መፈፀም የዚህ ትውልድ ዋና ሃሊፊነት ነው ብለዋል ።

አሁን በመግባባት እና በመወያየት ላይ ያተኮረ አዲስ የፖለቲካ ባህል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ብናልፍ ያለፈው ነገር አልፏል የኛ የዛሬ ስራ ነገን በማስተካከል በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተግባባተን መቋጫ ማብጀት ነው ብለዋል ።

አቶ ብናልፍ አክለውም ውይይት እና መግባባት መፍጠር ስራው ከባድ መሆኑን ገልፀው ለውጤታማነቱ በትዕግስት መወያየት እና መግባባት እንሚያስፈልግ ገልፀዋል ።

አካታች ብሔራዊ ምክክሩን ከማሳካት አንፃር የምሁራን ሚና በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዶ/ር ባዩልኝ ዘመድአገኘሁ ናቸው ።

ዶ/ር ባዩልኝ በጥናት ፅሁፋቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ችግሮችን በጥናት በመለየት፣ሃሳብ በማምንጨት እና በማመከር የምክክር ሂደቱን የማገዝ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል ።

ጦርነትና ግጭቶች ።፣ጫፍ የረገጡ አመለካከቶች እና የመሰረተ ልማት ችግሮች የብሔራዊ ምክክር ፈተናዎች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ዶ/ር ባዩልኝ ገልፀዋል ። በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የማጠቃለያ ሃሳብ ተሰጥቶበታል ።

Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር 

Related posts:

Leave a Reply