የአጊቱ ጉደታ ገዳይ 20 ዓመት ተፈረደበት

አጊቱ እጅግ ውጤታማ የተባለች፣ የፍየል ወተትና የወተት ውጤቶችን በማምረት የተሳካላት የዲያስፖራ ምሳሌ ሴት ነበረች። የመሞቷ ዜና በትጋቷ የሚያውቋትን የጣሊያን ዜጎች፣ የአስተዳደር አካላት እንዲሁም ወገኖቿንና የምርትዋ ተጠቃሚዎቿ ድንገተኛ ሞቷን የምይታመንና በቀላሉ የማይረሳ ስሜት ፈጥሮባቸው እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል።

May be an image of 1 person, food and indoor

በጣሊያን፣ የትሬንቶ ፍርድ ቤት ትላንት (የካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም) በዋለው ችሎት ኢትዮጵያዊቷን ስራ ፈጣሪ አጊቱ ጉደታን አሰቃቂ ጥቃት በማድረስ ለህልፈተ ህይወት የዳረገው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ሱሌማን አዳምስ ላይ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዷል።

አጊቱ በትሬንትኖ ሊጠፉ የተቃረቡ የፍየል ዝርያዎችን ከመጥፋት በመታደግና ፍየል እርባታ፣ በአካባቢ እንክብካቤ፣ በወተትና ወተት ተዋፅኦ ምርት በጣም ውጤታማ የነበረች እና በጣሊያን ህዝብና መንግሰት እንዲሁም በዳያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ በውጤታማነቷ ሞዴል የነበረች ትጉህ ሴት ነበረች።

ለዚህ ፍትህ መገኘት የአካባቢው የመንግስት ኃላፊዎችና ነዋሪዎች እንዲሁም የትሬንቲኖ የኢትዮጵያ ዳያስፓራ ኮሚኒቲ በጣሊያን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ጋር በመስራት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ኤምባሲው መግለጹን የቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

Leave a Reply