“የፌደራል መንግስት ፈርሷል። የትህነግ ወራሪ ሃይል አዲስ አበባ ዙሪያ ከቧል። ራሳችሁን አድኑ። የውጭ ተቋማትና ዲፕሎማቶች አገር ለቃችሁ ውጡ። የመንግስት ባልስልጣናትም ቪዛ ተመቻችቶላችኋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ወደ አረብ ኢምሬትስ ሊበሩ ነው … ” አሜሪካ መራሹ የፕሮፓጋንዳ ሃይል በተከታታይ፣ በዕቅድ፣ በመናበብ፣ በመቀባበል ሲያውጁት የነበረው የሞት አዋጅ ነበር።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግስት እንዲህ ያለው ተግባርና እንቅስቃሴ እንዳለ መረጃ እንዳለው በማስታውቀ ቅድመ ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር፣ ከማሳሰቢያው በሁዋል ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ግን ክልሉ አፈንጋጮችን የሚታገስበትም ሆነ ማንንም የሚያባብልበት አቅምና ትእግስት እንደሌለው አመልክተዋል። የክልሉ መንግስት ይህ ከመሆኑ በፊት ለመጨረሻ ግዜ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ጀሌው ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ኮሚሽነሩ ይፋ አድርገዋል። ከሴራው ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበትን ማናቸውንም አካላት በህግ ለመጠየቅም እንቅስቃሴ መጀምሩንና በቁጥጥር ስር የዋሉ አካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

“ከማን ጋር ነው ድርድሩ? መንግስት ሞቷል” የሚለውና ከክህደት ቢላዋ ተርፎ አገሩን የታደገውን የአገር መከላከያ ዳግም በትኖ ለማኝ ለማድረግ ” የብልጽግና ወታደሮች እጃችሁን ለትግራይ ነጻ አውጪ ስጡ። የሚያድናችሁ ምድራዊ ሃይል የለም። ጊዜ አታባክኑ። የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊት እርምጃ ሳይወስድባችሁ … ” ይህ ደግሞ ከዋና አሜሪካ መራሹ ፕሮፓጋንዳ ስር የሚርመጠመጠው የከሃጂዎች ስብስብ ጩኸት ነበር።

በክህደት የታረደው፣ የደርግ ተብሎ ለልመና የተዳረገው፣ አሁን ደግሞ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ እንዲሉ “የብልጽግና የአብይ ሰራዊት” የሚል ታቤላ የተለጠፈለት የኢትዮጵያ መመኪያ የአገር መከላከያ ሰራዊት ራሱን ዳግም አደራጅቶ፣ በሃይል ገዝፎ፣ በትጥቅ ዘምኖ፣ ከፋኖ፣ ከሚሊሻ፣ከ ልዩ ሃይልና ከአፋር አናብስት ጋር ተጋምዶ ከአየር ድጋፍ ተደርጎለት ” መግባት እንደመውጣት አይቀልም” በሚል መርህ በሁለት ሳምንት ነገሮች ተገለበጡ።

ሃፍረትን ከቶ የማታውቀው አሜሪካ በወኪሏ አማካይነት ” 1991 ላይ የተቸነከሩ” ስትል የትህነግ መሪዎችን አገር በቀለ ስም አጸኑ። ሕዝብ የማይወዳቸውና የማይቀበላቸው እንደሆነ ቢነገራቸው የማይገባቸው እንደሆኑ በአደባባይ አስታውቀው ዘለፏቸው። ሱሉሱ ሲዞር እነሱም ዞሩ። ያቺ ፈርሳለች የተባለች አገር ዲያስፖራ ልጆቿ ጋለቡባት። የአፍሪካ ህዝብረት ስብሰባ ተካሄደባት። በአደባባይ በውሃ ዳንስ በግልጽ አዳራሽ፣ ዓለም በቀጥታ እያየ የዓለም “ታላላቅ” የሚባል እንግዶችና የአፍሪካ መሪዎች ተምነሸነሹባት። ይህ ዓይናቸውን ብቻ ሳይሆን ህሊናቸውን ያቆሰለባቸው ሃይሎች ግን አዲስ እቅዳቸውን ለማሳካት በሴራና በክፋት መርመጥመጣቸውን ቀጥለዋል።

ፊደራል መንግስት ላይ የተከፈተውና ኢትዮጵያ ላይ የተጠመደው የብተና ሟርት ሕዝብ አንድ ሆኖ ሲያከስመው ቀጣዩ ዕቅድ ክልሎችን ከተቻለ በሎቢ፣ ካልተቻለም ተቀጥያ በመፈለፈል ከማዕከላዊ መንግስቱ እንዲያፈነግጡ ማድረግ፣ ለዚሁም ከፍተኛ በጀት መመደቡን ጥቅሰን ከወር በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

ትህነግ 300 ሺህ የትግራይ ልጆች የት እንደደረሱ እንደማያውቅ በወጣት ሊጉ አማካይነት ሲያስታውቅ፣ ቀደም ሲል ከዛው ከትግራይ ተቃዋሚ መሆኑንን የሚናገር፣ ነገር ግን ከትህነግ ጋር የአጀንዳ ልዩነት የሌለው ድርጅት መሪ ሰባት መቶ ሺህ ወጣቶች መገደላቸውን በራሳቸው ኔትዎርክ በተደረገ ንግግር ማስታወቁ አይዘነጋም።

የዚሁ ክልሎች ላይ እሳት የመለኮሱ ተግባር በኦሮሚያ በስፋት እንዲከናወን ሰፊ በጀት መለቀቁን ከነበጀት ዝውውሩ የስለላ መዋቅሩ አግኝቶት በታሰበው ደረጃ ሳይሰፋ መቆጣጠር የተቻለ መሆኑንን በውስጥ የሚሰሙ መረጃዎች ያመልክታሉ። በተመሳሳይ የሶማሌ ክልልን በማተራመስ፣ የአፋር ነጻ አውጪ በሚል ትህነግ ያደራጀው ሃይል ጦርነት እንዲከፍትና የአብዲ ኢሌ መዋቅር በሶማሌ ክልል ባለስልጣናትን በመጀንጀንና መዋቅር በመስበር ከቻለ መንግስት እንዲገለብጥ፣ ካልቻለም የተወሰነኑ አካባቢዎችን እንዲቆጣጠር ዕቅድ መኖሩም ታውቆ ነበር።

ከአካባቢው የሚተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሶማሌ ክልል መሪዎች ላይ መፈንቅለ አመጽ ለማካሄድ ገንዘብ የወሰዱ፣ አብረው የመከሩ፣ ያሴሩና የተባበሩት ቀድሞ ይታወቁ ነበር። ለዚህም ይመስላል ሁከት ለመፍጠር ያሰቡት ክፍሎች በተከፈላቸው መጠን ሂሳብ ሊያወራርዱ ሲዘጋጁ ጀግጅጋና አካባቢው የፌደራል ልዩ ሃይል፣ ቀይ ለባሽ ተወርዋሪዎች፣ እንዲሁም መከላከያ እንደሁኔታው እርምጃ ለመውሰድ ጣቱን በቃታ አድርጎ መመሪያ ይጠብቅ ነበር።

ቅርብ የሆኑ እንዳስታወቁን ሁሉም ነገር በጥንቃቄ ያለቀው ልክ በአንድ በታጠረ ግቢ ውስጥ በዝግ እንደተደረገ ግጥሚያ ነው። ዋናዎቹ አተራማሾች በመረጃ ተበልጠው ለትርምሱ እንዲጠቅም ተደርጎ በተሰራ መረብ ውስጥ እንዲገቡ ተደርጎ ሸምቆቆው ጠብቆባቸዋል። ቀሪው ውሪም ተለቅሟል። በዚህ መልኩ ያለቀውን ጉዳይ አዲስ ስታንዳርድ “መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ” ሲል አጉኖታል።

ሁሉም ካለቀ በሁዋላ ነው የሶማሌ ክልል ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስ ያስታወቀው። በሶማሌ መንግስት ስራው ለሰኮንድ እንዳልተስተጓጎለ። የሚገልጹ እንዳሉት ዓላማው ከአፋር ጀመሮ እስከ ሶማሌ ክልል ያለውን ኮሪዶር የማተራመስ ዕቅድ የኖረ የትህነግ ሁለተኛ ደረጃ አሳብ እንደሆነ አመልክተዋል። ለውጡ ይፋ እንደሆነ ቅድሚያ ሶማሌ ክልል ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን የተካሄደውም በዚሁ መነሻ እንደሆነ አስታውሰዋል።

አጸደ የምትመራው አዲስ ስታንዳርድ ያሰራጨችውን ዜና ተከትሎ ትላንት አመሻሹን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጅግጅጋ ከተማ ውስጥ ረብሻ፣ አለመረረጋጋትና መንግስታዊ የኃላፊነት ቦታዎችን በኃይል ለመያዝ የተደረገ ሙከራ እንዳለ ተደርጎ ተናፍሷል። ይህን መረጃ ክልሉ “ፍፁም ሀሰትና ከእውነት ራቀ” ሲል አንኳሶታል። በአሁኑ ወቅት ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ መላው የሶማሌ ክልል እንደ ወትሮው ሁሉ በሰላም እና መረጋጋት እንቅስቃሴዎች እየተከናወነ መሆኑም ገልጿል።

ክልሉን የማተራመስ ሙከራ እንደነበር ያላስተባበለው ክልሉ ፀረ ለውጥ የሆኑ፣ በሙስና እንዲሁም በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ለውጥ አደናቃፊ አካላት ጋር በድብቅ ግንኙነት ሲያደርጉ ተደርሶባቸው ከመንግስት መዋቅር የወጡ ሀይሎች ሰላም ለማደፍረስ ያደረጉት ሙከራ ከሰላም ወዳዱ የክልሉ ህዝብ ጋር በመተባበር መክሸፉን አመልክቷል። ክልሉ ከውጭ አካላት ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላት ባያብራራም ከቀሞ መሪ አብዲ ኢሌ መዋቅር ተጎሮ የቀረው፣ ከፍተኛ ሃብት ይዞ ኮብልሎ ቱርክና ኬንያ የተቀመጠውና ትህነግ ዳግም ያደራጀው ሃይል እንደሆነ ይታወቃል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን የክልሉን ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደማይታገስና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቁን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ሲያስታውቅ ምን ያህል በቁጥትር ስር እንደዋሉ ይፋ አላደረገም። ሸገር ታይም የጠቀሳቸው የሶማሌ ክልል የልዩ ሃይል አዛዥ ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ መረጃ ሰጥተዋል።

ከቀናት በፊት ርእሰ መስተዳድሩ የሌላ ብሄር ውግንና አለው፣ አሃዳዊ ነው እንዲሁም ካቢኔያቸው ለድርቁ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም በሚል ሽፋን ክልሉን ለመበጥበጥ እና በዋናነትም ጅግጅጋ ከተማ ላይ ረብሻ ለማስነሳት የታቀደ ቢሆንም በዚህ ቅስቀሳ የተሰማሩ እና ለአላማቸውም ማሳኪያ ገንዘብ በሚስጥር ሲያከፋፍሉ የነበሩ 10 የሚሆኑ የቀድሞ አመራሮች ከፍርድ ቤት የማሰሪያ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው በይፋ አመልክተዋል። የሚፈለጉት ጥቂቶቹ እየታደኑ ሲሆን አብዛኞቹ ከላይ በተገለጸው መሰረት ፍለጋ ድረስ እንኳን አላስቸገሩም።

ከቀናት በፊት የክልሉ መንግስት እንዲህ ያለው ተግባርና እንቅስቃሴ እንዳለ መረጃ እንዳለው በማስታውቀ ቅድመ ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር፣ ከማሳሰቢያው በሁዋል ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ግን ክልሉ አፈንጋጮችን የሚታገስበትም ሆነ ማንንም የሚያባብልበት አቅምና ትእግስት እንደሌለው አመልክተዋል። የክልሉ መንግስት ይህ ከመሆኑ በፊት ለመጨረሻ ግዜ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ተከትሎ ጀሌው ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ኮሚሽነሩ ይፋ አድርገዋል። ከሴራው ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበትን ማናቸውንም አካላት በህግ ለመጠየቅም እንቅስቃሴ መጀምሩንና በቁጥጥር ስር የዋሉ አካላት መኖራቸውን አስታውቀዋል።

“ሁከት እና ውዥንብር ለመፍጠር የሚያልሙ አካለት አንቅስቃሴያቸውም ሆነ እኩይ ተግባራቸው ከክልሉ መንግስት እና የፀጥታ መዋቅር በላይ አይደለም” ያሉት ኮሚሽነሩ ተገቢውን እርምጃ እና ህግ የማስከበር ስራ በማያዳግም መልኩ እንደሚተገበር አመልክተዋል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ የክልሉ ሹም እንደነገሩን የልዩ ሃይል፣ የቀይ ላባሽ ኮማንዶዎች ፍጥነትና መከላከያ በቅጽበት ተናበው ያሳዩት ዝግጅት ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። አንዳቸውም ወደ እርምጃ እንዳልገቡ ነገር ግን ሲፈለግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለመገመት ቀልል እንደሆነ አመልክተዋል።

ከክልሉ ያኮረፉና ቀደም ሲል የአብዲ ኢሌ መረብ ስር የነበሩ ኬንያ ሚዲያ ከፍተው እንቅስቃሴ መጀመራቸው የሚታወስ ነው። አሁን ላይ ቻይና በጀመረችው የምስራቅ አፍሪቃን የሰላም ቀጠና የማድረግ እንቅስቃሴ፣ ለዚህም ለቀጠናው ከመደበችው ልዩ ልዑክ ጋር በተያያዘ ይፋ እንዳደረገችው የቀጠናው አገራት አንዱ በሌላው ላይ አፍራሽ ድርጊቶችን እንዳያከናውኑ፣ ድጋፍ እንዳይሰጡ፣ ይልቁኑም ተጋግዘው እንዲመክቷቸው ተሰራለች። የዚህ አካል የሆነው የቅድመ ስምምነት ስብሰባ በኬንያ መካሄዱን ተከትሎና ቀደም ሲሉ ሁለቱ አገራት ባላቸው ስምምነት መሰረት ኬናያ ምድሯ ላይ ሆነው ኢትዮጵያን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ጀርባ እንደምትሰጥ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

One thought on “ከፌደራል ወደ ክልል የተከለሰው ሴራ – ሶማሌ ክልል እርምጃ ወሰደ”
  1. […] ከክልሉ ያኮረፉና ቀደም ሲል የአብዲ ኢሌ መረብ ስር የነበሩ ኬንያ ሚዲያ ከፍተው እንቅስቃሴ መጀመራቸው የሚታወስ ነው። አሁን ላይ ቻይና በጀመረችው የምስራቅ አፍሪቃን የሰላም ቀጠና የማድረግ እንቅስቃሴ፣ ለዚህም ለቀጠናው ከመደበችው ልዩ ልዑክ ጋር በተያያዘ ይፋ እንዳደረገችው የቀጠናው አገራት አንዱ በሌላው ላይ አፍራሽ ድርጊቶችን እንዳያከናውኑ፣ ድጋፍ እንዳይሰጡ፣ ይልቁኑም ተጋግዘው እንዲመክቷቸው ትሰራለች። የዚህ አካል የሆነው የቅድመ ስምምነት ስብሰባ በኬንያ መካሄዱን ተከትሎና ቀደም ሲሉ ሁለቱ አገራት ባላቸው ስምምነት መሰረት ኬንያ ምድሯ ላይ ሆነው ኢትዮጵያን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ጀርባ እንደምትሰጥ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል። (ኢትዮ 12) […]

Leave a Reply