ከሶማሌ ክልል በተጨማሪ ኦሮሚያ ክልል የሚሰማው የድርቅ ዜና ከባድ ነው። ያለ ምንም ማጋነን ሶስት ዞኖች ድርቅ መቷቸዋል። እስካሁን ከደረሰው በላይ ድጋፍ ካልደረሰ በቀጣይ ጉዳቱ እንደሚከፋ ከየአቅጣጫው ጩኸት እየተሰማ ነው። ይህ በዝናብ እጥረት ምክንያት በየአስር ዓመቱ የሚከሰተው፣ አንዳንዴም በየሰባት ዓመቱ የሚታየው ድርቅ ሰፊ ጥፋት ቢያደስም በዘላቂነት እንዲቀረፍ የሰራ መንግስት የለም።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክብቶች አልቀውብናል። ዝናቡ ቀጥ ስላለ አረንጓዴ ነገር የለም። በሰማይና በምድር መካከል ሃሩር ከሚቅበዘበዘው በቀር ለህይወት ማስቀተያ የሚሆን ነገር ነጥፏል። ከብቱ ውሃ ጥምና ረሃብ፣ ከሙቀቱ ጋር አንድነት ቀጥ አድርጎታል። የሚጠቡትም ቆዳ ሆኖባቸዋል። ህጻናት ከስለዋል። የነጠፈውን የናቶቻቸውን ጡት እንደመጫኛ ይጎትታሉ። ምን የለም። በቅርብ ረቀት አማራጭ የለምና ሁሉም ተስፋቸው ተድፍቷል። ተስፋቸው ደርቋል። አውሮፓና አሜሪካ ሆነው ሴራ ለሚረጩ ተቀታሪዎች እኒህ ሰዎችና እንሳሳቶች ምናቸውም አይደሉም። ቢሆኑማ “እስኪ ይህን ጊዜ እንለፈው” ባሉ ነበር።

በውሃ ማጎልበት፣ በምግብ ለስራና በተለያዩ የማቋቋሚያ ተግባራት ስም ከውጭ ከሚገባው ዕርዳታና ብድር ላይ የሚዘርፉ መሪዎች፣ ከደሃ ጉሮሮ ዘርፈው ገንዘብ ወደ ውጭ አገር የሚያሸሹ ማፊያዎች ሲመሯት የኖረችው ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ከከበባት የሴራ ፍትጊያ በተጨማሪ ድርቁ ክፉ ጠባሳ እንዳያስቀር በስጋት የሚጮሁ በርክተዋል።

ምክንያቱ ቁልጭ ብሎ በማይነገር አድማ ዓለም እጁን ከኢትዮጵያ እንዲሰበስብ ተደርጎ በአንድ ፊት የህልውና ጦርነት፣ በሌላ በኩል ይኸው የሴራ ነውጥ ያፈናቀላቸውን ሲያስታምምና ወደ ቀያቸው ሲመልስ የከረመው መንግስትም ዓለም አደባባይ “እርዱን” እያለ እየጮኸ ነው። መንግስት እየጮኸ ባለበት ወቅት አማራ ክልልን ዱቄት ያደረገው ትህነግ ዳግም አፋርን ወሮ ከ300 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሕዝብ አውላላ ሜዳ ላይ ፈሷል። እናት ዱር እየወለደች ነው። እርጥብ አራስ በበረሃ ያለ በቂ ውሃና እናት ጡት እየተሰቃየ ነው። ሌላም ሌላም ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመ ነው። “ለምን?” ይህን የሚያደርገው ትህነግም ሆነ ደጋፊዎቹ ምላሽ የላቸውም።

ይህ ሁሉ ሳያንስ ሸኔ የሚባለው አላማውና አሳቡ ምን እንደሆነ የማይታውቀ ቅጥረኛ ቡድን ሕዝብ ይጨፈጭፋል። ንብረት ያወድማል። ጌታው ትህነግ እንዳለው ይዘርፋል።

በስመ አማራ ተቆርቋሪነት አውሮፓ ቁጭ ብለው ሴራ እያመረቱ የሚከፈላቸው ክልሉን እዚህ ግባ በማይባል ደባ እየደበደቡት ነው። አመድ አድርጎ የወጣው ጠላት ለዳግም ሂሳብ ማወራረድ እየተሟሟቀ መሆኑንን እየገለጸ አንድ እንዲሆን ከመስበክ ይልቅ ክልሉን ለማተራመስ በቡዳ መንፈስ ይሟሟታሉ። “ጊዜው አሁን ነው” በሚል አረቄ የሚያንቃርሩ ወስላቶችን ለማራ ህዝብ አማራጭ አድርገው እያቀረቡ በህዝቡ ላይ ልጋጋቸውን ይተፋሉ። እኒህ ጥቂት ተከፋዮች ለዚህ ውለታቸው አማራ ያዋጣላቸዋል። ሃፍረት።

አገሩን እያፈረሱለት ሃብት የሚሰበሰብላቸው እነዚህ አፍረተ ቢሶች አንድ ላይ ያገኙትን ሁሉ በማግበስበስ አገሪቱን ለማጦዣ ይጠቀሙበታል። አማትበው የሚጀመሩ “እሪያ ሃይማኖተኞች” መርዝ ይረጫሉ። ትናት በንጹሃን ደም ሲነገዱና ሲቀልዱ የነበሩ ሁሉንም እያጣመሙ እርግማን ያወረዳሉ። በሄዱባትና በረገጡበት ክህደትን ሲለማመዱና በሁለት ሳንጃ ሲበሉ የኖሩ የጥፋት ነዶ ከትህነግ ሚዲያዎችና አቀንቃኞች ጋር ሆነው ይወዘውዛሉ። ሳይለይ ያገኘውን የሚያፍስላቸው አብሮ ይጮሃል። ደግነቱ ጥቂቶች ናቸው እንጂ ቢሳካላቸው ይህን አገሪቷ በጠፋች ነበር።

ምዕራብ ጉጂ ዞን አደጋ ሥጋትና ልማት ተነሽዎች ማቋቋም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዘሪሁን እንደገለጹት፤ ዞኑ በድርቅና ጸጥታ ችግር በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎችና ባለሀብቶች የተሰበሰበ 300 ኩንታል እህል በስተቀር በመንግሥት የተደረገ የምግብ ድጋፍ የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት 188 ሺህ 606 ዜጎች ለምግብ ተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡ በውሃና መኖ እጥረት 20 ሺህ 278 እንስሳት ሲሞቱ ከ60 ሺህ 311 በላይ በአስጊ ደረጃ ላይ ደርሰው በሰው ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

የፈረሰ ሳይጠገን፣ የተመታ ስነልቦና ሳይደነድን፣ የተወጉ ወገኖች ሳያገግሙ፣ የተበተኑ ቤታቸው ሳይገቡ፣ ድርቅ ታክሎበት ወገኖቻችን የሚላስ የሚቀመስ አጥተው የውሃ ያለህ ሲሉ ጦርነት፣ ጭፍጨፋ፣ ሴራ፣ መከፋፈል፣ ማባላት፣ ሜዳ ካልውሰድኩ ብሎ አገር መናጥ፣ ሁሉ ለኔ፣ ስልጣን ብቻ፣ … ጊዜ የማይመርጡ በህዝብ ስቃይ፣ በህጻናት የጠኔ ድምጽ የሚያሽካኩ እርኩሶች፤ ሰባኪውም ተሰባኪውም የነጠፉባት አገር።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክብቶች አልቀውብናል። ዝናቡ ቀጥ ስላለ አረንጓዴ ነገር የለም። በሰማይና በምድር መካከል ሃሩር ከሚቅበዘበዘው በቀር ለህይወት ማስቀተያ የሚሆን ነገር ነጥፏል። ከብቱ ውሃ ጥምና ረሃብ፣ ከሙቀቱ ጋር አንድነት ቀጥ አድርጎታል። የሚጠቡትም ቆዳ ሆኖባቸዋል። ህጻናት ከስለዋል። የነጠፈውን የናቶቻቸውን ጡት እንደመጫኛ ይጎትታሉ። ምን የለም። በቅርብ ረቀት አማራጭ የለምና ሁሉም ተስፋቸው ተድፍቷል። ተስፋቸው ደርቋል። አውሮፓና አሜሪካ ሆነው ሴራ ለሚረጩ ተቀታሪዎች እኒህ ሰዎችና እንሳሳቶች ምናቸውም አይደሉም። ቢሆኑማ “እስኪ ይህን ጊዜ እንለፈው” ባሉ ነበር።

የኦሮሚያ የጣር ጩኽት ከስር ያንብቡ ሸኔ ይጨፈጭፋል፣ ረሃብም …

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ፤ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች በቂ ድጋፍ በአግባቡ እየደረሰ ባለመሆኑ መንግሥትና የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ ምዕራብ ጉጂ ፤ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች የድርቁን ሁኔታንና የድጋፍ አሰጣጥ ክፍተቶችን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሶስቱ ዞኖች ድርቅ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችና እንስሳት ለምግብና ውሃ እጥረት ተጋልጠዋል፡፡

መንግሥት የችግሩን አሳሳቢነት የሚመጥን ድጋፍ ለምዕራብ ጉጂ፤ ለምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች ተግባራዊ አለማድረጉ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን የዘርፉ አመራሮች ገልጸዋል፡፡

ምዕራብ ጉጂ ዞን አደጋ ሥጋትና ልማት ተነሽዎች ማቋቋም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዘሪሁን እንደገለጹት፤ ዞኑ በድርቅና ጸጥታ ችግር በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲዎችና ባለሀብቶች የተሰበሰበ 300 ኩንታል እህል በስተቀር በመንግሥት የተደረገ የምግብ ድጋፍ የለም፡፡ በአሁኑ ወቅት 188 ሺህ 606 ዜጎች ለምግብ ተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡ በውሃና መኖ እጥረት 20 ሺህ 278 እንስሳት ሲሞቱ ከ60 ሺህ 311 በላይ በአስጊ ደረጃ ላይ ደርሰው በሰው ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

ዞኑ ዜጎችን ለመታደግ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለድጋፍ እጁን የዘረጋ ቢሆንም በቂ ድጋፍ ማግኘት አልቻለም ብለዋል፡፡ በኑሮ ውድነት ምክንያት ሰው ሰውን ለማስጠጋት አስቸጋሪ ነው ያሉት ኃላፊው፤ ተመጣጣኝ ምግብ እጥረት ታክሎበት ሕጻናትና አዛውንቶች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን ጠቁመዋል።

ምዕራብ ሀረርጌ ዞን አደጋ ስጋትና ልማት ተነሺዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አሊፊያ ቶፊቅ ዞኑ ከጥር ወር ጀምሮ ለ563 ሺህ 766 ዜጎች ከመንግሥት የምግብ ድጋፍ ጥያቄ መቅረቡን ጠቅሰው እስካሁን ድረስ በቂ ድጋፍ እንዳላገኙ ገልጸዋል፡፡

ዜጎች ለዜጎች አደረጃጀት ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ 590 እህል ከተሰበሰበ እህል መልሶ ከመጠቀም ዉጪ ሌላ ድጋፍ አለመደረጉን ተናግረዋል፡፡ የእንስሳት መኖ እጥረት ለመቋቋም የተደረገው ድጋፍ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ቤል በላይ ከሚያስፈልገው እንስሳት መኖ 14 ሺህ ቤል ብቻ ድጋፊ መደረጉን ጠቅሰው፤ የውሃ ችግር ለመፍተት 11 ቦቴ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ ችግሩን መቅረፍ አላስቻሉም፡፡ ቡርቃ ዲምቱ ከፍተኛ የውሃ እጥረት መኖሩን አያይዘው ገልጸዋል፡፡ መንግሥት የምግብና የመኖ ድጋፍ እንዲያደርስላቸው ጠይቀዋል፡፡

ምስራቅ ሀረርጌ ዞን አደጋ ስጋትና ልማት ተነሽዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ኑሬ መሐመድ 67 በመቶ የሚሆነው ምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ ቆላማ አየር ንብረት ያለውና በተደጋጋሚ ለድርቅ ተጋላጭ ነው፡፡ በዝናብ እጥረት ምክንያት ምርትና ውሃ እጥረት በዞኑ እየሰፋ ነው፡፡ በድርቁ ምክንያት 268 ሺህ ዜጎች ለተረጂነት ተጋልጠዋል፡፡

በአራት ወረዳዎች ችግሩ የከፋ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ የእንስሳት ሕይወት ለማዳን ዞኑ ከደጋማ አካባቢዎች የእንስሳት መኖ በማፈላለግ ችግሩን ለመፍታት እየሞከረ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ 59 ከብቶች የሞቱ ሲሆን 14 ሺየሚሆኑት በአስጊ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡

ኦሮሚያ አደጋ ሥጋትና ልማት ተነሽዎች ኮሚሽን ኮሚሸነር ሙስጠፋ ከድር በበኩላቸዉ፤ ለሰው ህይወት የሚያሰጋ የምግብ እጥረት የለም፡፡ እስከአሁን ድረስ በተደረገው ርብርብ በአጠቃላይ በኦሮሚያ ውስጥ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ለሚገኙ ተረጂዎች 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል እህል እንዲሠራጭ ተደርጓል፡፡

ለአደጋው ተጋላጭ ከሆኑ ዞኖች መንግሥት የእህል ስርጭት ያላደረሰበት ዞን የለም ብለዋል፡፡ በገንዘብ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰው፤ እህል በመጋዘን ውስጥ በማጠራቀም አንዳንድ ቦታዎች ክፍተቶች ከታዩባቸው ዞኖች ቦረና ዞንን እንደምሳሌ ጠቅሰዋል፡፡

በስርጭቱ ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶች ለማጣራት ኮሚሽኑ ኮሚቴ አዋቅሮ በሌሎችም ዞኖች ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል፡፡ ከመቶ አስር እጅ እንስሳት ቁጥር ለማዳን መንግሥት ከ500 ሺህ በላይ ቤል የእንስሳት ምግብ መሰራጨቱን ገልጸው፤ ሕብረተሰቡ ከችግሩ እስከሚላቀቅ ድረስ ሁሉም አካላት ከኮሚሽኑ ጎን በመቆም የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ገመቹ ከድር

አዲስ ዘመን የካቲት 10/2014 ዓ.ም

Leave a Reply