የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት አጽድቋል።

ምክርቤቱ ለውሳኔ የቀረቡለትን 11 ኮሚሽነሮች ሹመት ያለምንም ተቃውሞ በ5 ድምጸ ተአቅቦ ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህ መሰረትም ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሲሾሙ ወ/ሮ ሂሩት ገብረሥላሴ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው ተሿሚዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

 1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
 2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ
 3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
 4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ
 5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን
 6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ
 7. አቶ ዘገየ አስፋው
 8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም
 9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
 10. አቶ ሙሉጌታ አጎ
 11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ ናቸው።

ፕ/ር መሰፍን አርአያ ወልደተንሳይ ማናቸው⁉️

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት አጽድቋል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ይተዋወቁ።

👉 በሕክምና የዶክተሬት ዲግሪ ( MD), ከፓቭሎቭ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ

👉 በሳይኮቴራፒ ፍልስፍና የፒኤች ዲ ዲግሪ (PhD), ከኦማያ
ዩኒቨርሲቲ፣ ሰዊድን

👉 ስፔሻላይዝድ ድፕሎማ፤ በሳይኮሎጂካል ሜድስን እና ሳይካትሪ፣
ግሮኒጎኝ ዩኒቨርስቲ ኔዘርላንድስ፣

👉 በኤፒዲሞሎጂና ባዮስታትስቲክስ ሰርተፍኬት፤ ጆን ሆፕኪንስ
ዩኒቨርስቲየሥራ ልምድ

👉 ለ6 ዓመታት በአዲግራት በደሴ አና በአማኑኤል ሆስፒታሎች
ሜዲካል ኦፊሰርና ዳይሬክተር፣

👉 ለ10 ዓመታት በአማኑኤል ሆስፒታል ሳይካትሪስት

👉 ለ 6 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሮቮስት

👉 ለ6 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይካትሪ ዲፓርትመንት
ዲን፣

👉 ለ12 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው
የዲፓርመንት ሃላፊ እና ልክቸረር ሆነው ካገለገሉ በኋላ ሙሉ
የፕፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል ፡ ፡

👉 ለ 11 ዓመታት የፌደራል ሆስፒታሎች አመራር ቦርድ አባል

👉 በአሁን ወቅት ከሙያዊ አገልግሎት በተጨማሪ በኢፌዴሪ
የማንነትና የአስተዳር ወሰን ኮሚሽን አባል ሆነው ያገለግላሉ፤

/ ሂሩት ገብረስላሴ ኦዳ ማን ናቸው ?

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ ተሹመዋል።

• በህግ ሜትሪዝ ምሩቅ ሰርቦን ዩኒቨርሲቲ (ፈረንሳይ)

• ለ2 ዓመት በህግ እና ፍትህ ሚኒስቴር የህግ ተንታኝ ባለሞያ

• ለ2 ዓመት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የአፍሪካ ህብረት የህግ ጥናት ኦፊሰር

• ለ2 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ሌክቸረር

• ለ8 ዓመት በግል የንግድ ድርጅት ከፍተኛ የህግ አማካሪ

• ለ4 ዓመት በዓለም አቀፍ የንግድ አማካሪ በመሆን ለUN ፣ World Bank) ፣ OAU የጥናት እና የማማከር ስራ

• ለ6 ዓመታት የአፍሪካ የሴቶች የሰላምና ልማት ኮሚቴ ከፍተኛ ኦፊሰር

• ለ3 ዓመት በኦክስፋም አህጉራዊ የሰላም ግንባታ እና የግጭት አመራር አማካሪ

• 14 ዓመት በተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የሰሩ፣ ለምዕራብ አፍሪካ እና ሳህል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ምክትል ወኪል ሆነው እያገለገሉ ያሉ

ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት

በአብዱረዛቅ መሐመድ. (ኢ.ፕ.ድ)

Leave a Reply