ፕሮፌሠር ካሣሁን ብርሐኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካ ሳይንስና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ትምሕርት ክፍል መምሕርና ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሠር ካሣሁን ብርሃኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባደረባቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማረፋቸውን ኢፕድ ከዩኒቨርሲቲው ባገኘው መረጃ አረጋግጧል፡፡

ፕሮፌሠር ካሣሁን ላለፉት 36 ዓመታት በዩኒቨርስቲው ውስጥ በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የሀላፊት ዕርከኖች ላይ ከማገልገላቸው በተጨማሪ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማበርከት ይታወቁ ነበር፡፡

የፕሮፌሠር ካሣሁን የቀብር ስነ ስርዓት ነገ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሠዓት በየካ ሚካኤል ቤተ ክስርሰቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም ኢፕድ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

You may also like...

Leave a Reply