ሌተናንት ጀነራል አስራት ዴኒሮ የደቡብ ሱዳን የሰላም ተቆጣጣሪ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ!

በኢትዮጵያ የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ የነበሩት ሌተናንት ጀነራል አስራት ዴኒሮ የደቡብ ሱዳንን ሰላም አስከባሪ አዛዥ ተደርገው ተሹመዋል።የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምድር ኃይል ዋና አዛዥ እና የመተከል ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ የነብሩት ጀነራል አስራት ዴኒሮ ይህ ሹመት የተሰጣቸው በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሲሆን በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ማስፈን እና የሽግግር ወቅት ፀጥታን መቆጣጠር የጀነራሉ ኃላፊነት መሆኑ ተገልጿል።

የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ቢሮ ቃል አቀባይ የሆኑት ኑር መሐመድ ሼህ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት “በጣም ብቁ እና የውትድርና እውቀት ያለው በመላው ዓለም የተከበሩ ባለሙያ ናቸው” ሲሉ ስለ ጀነራል አስራት ዴኒሮ መፃፋቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም እንዲሰፍን ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንዲሁም በሁለት ጎራ የተከፈለውን የሀገሪቱንወታደራዊ ኃይል ወደ አንድ ወታደራዊ አመራር ማምጣት በጀነራል አስራት ላይ ከተጣሉ ኃላፊነቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።ሌተናንት ጀነራል አስራት የተተኩት በኢጋድ የደቡብ ሱዳንን ተልዕኮ ለሁለት ዓመታት በመሩት ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ ቦታ ነው።

Leave a Reply