የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ዋና የጦሩ መሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ

በጋምቤላ ክልል ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ድርጅት ዋና የጦሩ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው ግለሰብ አቶ ዛን ዱዌር በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለመንግስት እጁን ሰጠ።

ግለሰቡ ቀደም ሲል የክልሉ መንግስት ያደረገውን ሰላማዊ ጥሪ ተከትሎ በአከባቢው ጎሳ መሪዎች አማካኝነት ወደ ህዝቡ መመለስ መቻሉ ተጠቅሷል።

የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ( ጋነግ) ድርጅት የጦሩ መሪ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አቶ ዛን ዱዌር በተሳሳተ መንገድ ወደ ጫካ በመግባት የትጥቅ ትግል ሲያደርግ እንደነበር ገልጿል።

መንግስት ያደረገውን የሠላም ጥሪ ተከትሎ ወደ አካባቢው የተመለሰው ግለሠብ ከመንግስት ጋር በመሆን ተገቢው ክትትል እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዘገባ ያሳያል።

Leave a Reply