የሱዳኑ ኮርማ ፍፃሜ – ከካርቱም እስከ ካይሮእስሌማን ዓባይ

የካርቱም መለዮ ለባሾች መካከል የተፈጠረው እባጭ እና ስብራት የሰነባበተ ነው። ምንም እንኳን ዛሬ ሀቁ ከአደባባይ ሲወጣ ቢታይም። [እሱ] የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች መሪ፣ ሙሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ፣ በትላንትናው እለት ወደ ሞስኮ መጓዛቸውን ተከትሎ በዚህ ቀውጢ ሰአት ምን አጣዳፊ ነገር ቢኖር ነው? ሲባል ነበር። ዛሬ ከካይሮ እና ከአልቡርሃን የውስጥ ሰዎች በኩል የተሰማው ነገር የካይሮን ቤተመንግስትና አልቡርሃንን ከጥቁር ቀን የጨመረ ስለመሆኑ ተገልጿል።
በሞስኮ ከሰርጌይ ላቭሮቭ ያደረጉትን ምክክራቸው በኋላ ሙሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ሄሜድቲ፣ ቪላዲሚር ቪላድሚሮቪች ፑቲን ወደ ዩክሬን ያደረጉን ዘመቻ በይፋ ደግፎ መግለጫ አውጥቷል። ወዲህ በካርቱም፣ አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን በስጋት ይንገፈገፍ ቀጥሏል።

ምንጮች እንገለፁት ሄሜድቲ መፈንቅለ-መንግስት ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው።” በማለት አልቡርሃን ፍራቻቸውን ለካይሮ አጋሮቻቸው ጠቁመዋል። እንደ ምንጮቹ፣ “ሄሜቲ በተቻለው ሁሉ ከሚዲያው ራሱን አርቆ ከሱ ጎን የሚቆሙ የጦር አመራሮችን ሲያደራጅ ቆይቷል።”
አል-ቡርሃን ሙሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ያደርሱብኛል ሲሉ የገለፁተሰ ስጋት ግብፅንም ያስደነገጠ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ የሄሜድቲ አቋም ከግብፅ ይልቅ ከሌሎች የአረብ ሀገራት ጥቅም ያደላ መሆኑ ጭምር ነው በአስደንጋጭነቱ የተነገረው። አሁን ላይ በሱዳን ወታደራዊ አመራሮች ዘንድ እንዲሁም በአብዮቱ መሪዎች ዘንድ ስለ ካይሮ ያለው አመለካከት በከፋ ሁኔታ አሉታዊ ሆኗልም ነው የተባለው።
በሱዳን ወታደራዊ አመራር በኩል በአልቡርሃን ላይ ያነጣጠረ የመፈንቅለ መንግስት ዝግጅት አይነት አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎች በተበራከቱበት ሰሞን ሄሜድቲ እና የቅርብ አጋሮቹ በውጭ ሀገራት እያደረጉ የሚገኘው ጉብኝት ስጋቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎታል።
ሄሜድቲ ታማኝ ወታደራዊ ባለስልጣናት ጋር በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ደጋግመው ተገኝተዋል።
በሌላ በኩል የግብፁ ደህንነት ሹም አባስ ካሜል በሱዳን ሊያደርጉ የነበረው ጉብኝት በራሱ በአልቡርሃን ጥሪ መሰረት የታቀደ ቢሆንም ኋላ ላይ እንዲራዘም ሆኗል። የግብፁ ስለላ ተቋም መሪ ወደ ካርቱም እንዳይመጡ ያደረገውም ራሱ አልቡርሃን ሲሆን በሱዳን ያለው አሁናዊ ሁኔታ አስፈሪ መሆኑን ለግብፃዊ ወገኖች አረጋግጠዋል ተብሏል። ይኸውም በሱዳን አብዮተኞችም ሆነ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ግብፅ በሱዳን ምንም አይነት ሚና እንዳይኖራት የፀና አቋም ተይዟል ነው የተባለው። እየጨመረ ባለበት በዚህ ወቅት። አልቡርሃን ለግብፅ ባለስልጣናት ካረጋገጡት ውስጥ በጣም አደገኛ የተባለው “ግብፅን በሱዳን ወታደራዊ አመራሮች ውስጥ ሚና እንዳይኖራት ስምምነት ተደርሷል።” የሚለው ነው በሚል ተዘግቧል። የሱዳን አብዮታዊ ሃይሎች ተወካዮች ከሳምንት በፊት ካርቱምን የጎበኘው የግብፅ ደህንነት ሹም ጋር እንዲገናኝ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸውም ነው የተሰማው።

በነገራችን ላይ በሱዳን አብዮተኞችም ሆነ ከአልቡርሃን ውጪ ባሉ መለዮ ለባሽ አመራሮች ዘንድ ስለ ግብፅ ያለው አመለካከት በከፍተኛ ጥላቻ መሞላቱን ተከትሎ ካይሮ በወታደራዊ ሹማምንቱና የሱዳን ጎዳናዎችን የዘጉ አብዮተኞችን እቀባ ለማላላት 120 ቶን የህክምናና ርዳታ ቁሳቁስ በወታደራዊ አውሮፕላኖች ጭና በካርቱም ያራገፈችው ከቀናት በፊት ነበር።

የሄሜድቲ ወንድም ሌተና ጄኔራል አብደልራሂም ዳጋሎ ሀሙስ የካቲት 24 ከአምስት የቤተሰባቸው አባላት ጋር በኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ ኢምሬትስ አቅንተዋል። ይኸው የሄሜዲ ታላቅ ወንድም ከአንድ ወር በፊትም ጥር 24 ላይ በሱዳን ሰአት አቆጣጠር እኩለ ቀን ላይ በኤምሬትስ አየር መንገድ አይሮፕላን ከካርቱም ተሳፍረው ወደ ኤምሬትስ ማቅናታቸው የሚታወስ ነው። በዱባይ በነበረው ድንገተኛ ጉብኝት ያደረገው የሄሜድቲ ወንድም በኤምሬትስ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ተኩል ሲሆን የአቡዳቢው አልጋ ወራሽ ባደረጉለት አቀባበል ወቅት እስኪታይ ድረስ በሚስጥር ስለመጓዙ ነው የተነገረው።
የአልቡርሃን አሁናዊ ስሜት በካርቱም ቤተመንግስት ቲክ ቲክ ከሚለው የግድግዳ ሰአት ጋር አስፈሪውን መፃኢ ጨለማ እየተጠባበቁ ስለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል።
አንቺም ክፉ ነበርሽ፣
ክፉን አዘዘብሽ፣
በላይም በታችም እሳት ለቀቀብሽ።

የዓባይልጅ

Leave a Reply