የአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ሹመቶችን ሰጠ

የአማራ ክልል መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ተቋማትን ለሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጠ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ ዞን የተለያዩ ተቋማትን ለሚመሩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመቶችን ሰጥቷል፡፡

በዚህ ሹመት ከ60 በመቶ በላይ አዲስ እንዲሁም ከ25 በመቶ በላይ ሴት አመራሮች እንዲኾኑ መደረጉን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፦

 1. ወ/ሪት አታላ አያሌው: የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
 2. አቶ ተገኘ አባተ : የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ
 3. አቶ መንገሻ አሸብር: የሰሜን ወሎ ዞን ውሃ መምሪያ ኃላፊ
 4. አቶ ግርማ ብርሃኔ: የሰሜን ወሎ ዞን መንገድ መምሪያ ኃላፊ
 5. አቶ ሲሳይ ፍስሃ: የሰሜን ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ
 6. አቶ ታደሰ ከተማው: የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
 7. አቶ ፀሐይነው ሲሳይ: የሰሜን ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ
 8. ወ/ሮ ደስታ አራጋው: የሰሜን ወሎ ዞን ሴቶች፣ ህፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
 9. አቶ ሰጠ ታደሰ: የሰሜን ወሎ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ
 10. አቶ ሀብተማርያም አሰፋ: የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ
 11. አቶ ባንቴ ምስጋናው: የሰሜን ወሎ ዞን ወጣትና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ
 12. ወ/ሮ ጀነቲ አያሌው ብሩ : የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ ኃላፊ
 13. አቶ ንብረት አባተ: የሰሜን ወሎ ዞን ሥራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ
 14. ወ/ሮ ሰርኬ በላይ: የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቢስ መምሪያ ኃላፊ
 15. አቶ መለሰ ተሻለ: የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ
 16. ኮሎኔል ኃ/ማርያም አምባዬ : የሰሜን ወሎ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ
 17. አቶ አዲሱ ሲሳይ: የሰሜን ወሎ ዞን መሬት መምሪያ ኃላፊ
 18. ወ/ሮ ፈለቁ መኮንን: የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ
 19. አቶ ፋሲል አረጋ: የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
 20. አቶ ተስፋሚካኤል ልባይ: የሰሜን ወሎ ዞን ሕብረት ሥራ ማኅበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
 21. አቶ አብርሃም አያሌው: የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ም/ኃላፊ
 22. አቶ ቦጋለ ሰጠ: የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊ
 23. አቶ በሪሁን ተረፈ: የሰሜን ወሎ ዞን እንስሳት ሃብት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
 24. አቶ አለሙ ይመር: የሰሜን ወሎ ዞን ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ
 25. አቶ ከፍያለው አበበ: የሰሜን ወሎ ዞን ሰላምና ጸጥታ ም/ኃላፊ
 26. አቶ ጋሻው ተገኘ: የሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /መምሪያ ም/ኃላፊ
 27. ወ/ሮ አዚዛ ኢብራሂም: የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የስልጠና ሱፐርቫይዘር ም/ኃላፊ
 28. ወ/ሮ እህትየ ታረቀኝ: የሰሜን ወሎ ዞን ሥራና ስልጠና መምሪያ ምክትል ኃላፊ
 29. ወ/ሮ ባንቻለም ሁነኛው: የምዘና ማእከል ኃላፊ
 30. አቶ ብርሃን ኃይሉ: የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ
 31. አቶ ማንደፍሮ ታደሰ ገላየ: የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ም/ኃላፊ
 32. አቶ ዓለማየሁ ጋዲሳ: የሰሜን ወሎ ዞን ሕዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኾነው ተሹመዋል።

የአመራር ሥምሪቱ የትምህርት ዝግጅትና ሥራ ልምድ፣ የአመራር የመፈጸም ብቃት፣ አዳዲስ አመራሮችን ወደ ኃላፊነት ማምጣት፣ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ የሚሉትን መስፈርቶች ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የካቲት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

You may also like...

Leave a Reply