ሩሲያ ከስፔስ ጥቃት ፈጸመች !!

የሳተላይት መረጃዎችን የተደገፉና ከሩሲያ ወታደራዊ ክፍል ጋር መረጃ የተለዋወጡ ሚዲያዎች በአንድ ድምጽ እደዘገቡት (ከስር ያለውን ምስሉን በመለጠፍ ) ሩሲያ ከስፔስ የዩክሬንን ተጨማሪ የወታደራዊና የደህንነት ቀጠናዎችን አውድማለች።

ከየብስ ፣ ከባሕርና ከአየር የተወነጨፉትም ቢሆኑ የቆዩ የሶቪየት ዊፐኖች እንጂ ሀይፐርሶኒኮች አይደሉም።

ሩሲያ አንድን ግዙፍ ከተማ የሚማግድ ርኬቶችና የትኛውንም የአለም ነጥብ መምታት የሚያስችላት ዜርኮን ሚሳኤሎችን የታጠቀች ናት።

ሩሲያ ከ44 ሺ ቶን በላይ የባዬሎጂካልና በጋዝ መልክ ተተኩሰው አካልን በጀምላ አቃጥለው የሚያተኑ የኬሚካል ዊፐኖች የታጠቀች ናት። የአለማችን የአቶሚክ ቦምብ ትልቁን FAOB የታጠቀች ናት። በአለም ለይ ከሚገኙ አቶሚክ ቦምቦች 50% 14,000 የሚገኘው በእጇ ነው።

ያም ሆን አለም የየብሱን ሲመለከት ከስፔስ እሳት ዘንቦበታል። ሩሲያ የምትዋጋው ከአየር ፣ ከየብስ ፣ ከባሕር ፣ ከስፔስና ከሳይበር የጦር ግንባሯ ነው።

የእንግሊዝ ጠ/ሚር ጆንሰን ትልቁ ስጋቱ ከሩሲያ የሚሰነዘር የስፔስ ጥቃት እንደሆነ የገለጸው ከሁለት ወራት በፊት ነበር።

ሰውየው ከተገቢው በላይ ይደነፋል። አሁን ከደቂቆች በፊት እንኳ ሩሲያን እንደሚደፍቃት አይነት ነገር ተናግሯል። የፈራው የስፔስ ጥቃት……..

ትናንት ማለዳው ለይ በሩሲያ እያንዳንዷ ግዛት ለይ ዘግናኝ ማእቀብ ሲጥል የነበረው EU እንዲህ የሚል የሚያለቅስ መግለጫን አውጥቷል :-

” ይኸ አውሮፓ ሳይታሰብ የተጋፈጠው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የከፋ የጨለማው ቀናት ጅማሮ ነው ” ሲል ነው ቀናቱን የገለጸው

የእንግሊዙ ጠሚር ቦሪስ ጆንሰን በውጥረቱ ሁሉ ሚዲያቸውን ይዘው ሲፎክሩ ነበር። አሁን ከሩሲያ ጥቃት በኋላ ለሩሲያ ተገቢውን ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጧት ዝተዋል።

እንደሚነገረው የሩሲያ የምንግዜም ወታደራዊ ዝግጅት ኢላማውን እንግሊዝና አሜሪካን ታሳቢ ያደረገ ነው። የሩሲያ ዜርኖይክ የኒውክለር ሚሳኤል ኢላማቸውን የደቀኑት እንግሊዝ ለይ ነው። ለሩሲያ ጦር ከእንግሊዝ ይልቅ ዩክሬን ትከብደዋለች የሚሉ አሉ።


በዩክሬን የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ አገሩን አድኑን ሲል የልዩ በረራ ጥያቄን ለሕንድ መንግስት አቅርቧል

ሊቱንያ ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል ነበር። ጥቃቱ የተጀመረው የጀርመን የየብስና የአየር ሀይል በሉትንያ ከሰፈረ ገና ጥቂት ሰአታት እንኳ ሳይቆጠር ነበር ። አሁን የሚነደው እሳት ነበልባሉ ሲገርፋት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጃለች ።


በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ሂትለር በቀላሉ የተቆጣጠራት ፓላንድ ደግሞ የተለመደ ፍርሀቷ ተነስቶባት ጭንቅ ውስጥ ገብታለች።

ፓላንድና ሩማንያ ወትሮም ከሩሲያ ጋር ሆድና ጀርባ ነበሩ። አሁን የኔቶ ጦርና አሜሪካ ደግሞ እንደ ኔቶም እንደ አለም አለቃም ሆና ከዩክሬን እየወጡ ጦራቸውን ያሰፈሩት ሩማንያና በተለይ ፓላንድ ለይ ነው።

የአሜሪካ ጦርም ትናንት ከእነዚህ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ወደ ሩሲያ ድንበር መጠጋት መጀመሩ የሩሲያን የአሁኑን እርምጃ ከማእቀቦቹ ቀጥሎ ያፋጠነው መሆኑ ይነገራል።

አሁን ከጥቃቱ በኋላ የጀርመን ተጨማሪ ሀይል ወደ ፓላንድ ተንቀሳቅሷል። ምናልባት ጆንሰን እንደፎከሩት ወደ ወታደራዊ እርምጃ ከገቡ የሚነሱት ከሩማንያ ይልቅ ከፓላንድ ነው ማለት ነው።

ይኸ ማለትም የኒውክለር ጦርነት ማለት ሲሆን አስፈሪዎች የጨለማ ቀናት ቁልፍ የሚፈቱባት አገር ከለንደን በፊት ፓላንድ ነች ማለት ነው።

እስካሁን በቀጠለው ጥቃት በርካታ የዩክሬን ወታደሮች ሞተዋል። የዩክሬንን አጠቃላይ ወታደራዊ አቅም ለመማገድ 50 ደቂቆች ይበቃዋል የተባለው የሩሲያ ሀይል እሳቱ የዩክሬንን አቅም ማግዶታል።

ከባድ ነው። ከቤላሩስ የተነሳው ጥምሩ የሩሲያና የቤላሩስ ሀይል አስፈሪ ነው። የሩሲያ የሪፓብሊካን ጦር አስፈሪ ሞገድ ሆኖ እየተመመ ነው

Suleman Abdela

You may also like...

Leave a Reply