አሳዛኙ የዩክሬን ለቅሶና መከዳት- ” የዓለም ጉልበተኞች ከሩቅ ሆነው እያዩን ነው”

ከእኛ ጋር ሆኖ የሚዋጋ ማንንም አላየንም። ብቻችንን ነው እየተዋደቅን ያለነው። ብቻችንን ነን። ብቻችንን ከወራሪው ጋር ተጋፍጠናል። የዓለም ጉልበተኞች ከሩቅ ሆነው እያዩን ነው” ይህ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቃል ነው። ፕሬዚዳንቱ ስለ ዩክሬን መከዳት ያስታወቁት ዛሬ ነው። ዩክሬን ሲዘንብላት የነበረው “አለንልሽ” ከሩሲያ ፈጣን፣ የተጠናና በቂ ዝግጅት ከተደረገበት ዘመቻ አላተረፋትም።

Zelenskyy also declared that he is still in Ukraine, despite Russia wanting to “destroy Ukraine politically by taking down the head of state. I am staying in the government quarter together with others. The enemy has designated me as the target number one, and my family as the target number two.”

በሁሉም አቅጣጫ ሰብሮ እየገሰገሰ ዋና ከተማዋን በማሽተት ላይ ያለው የሩሲያ ጦር ሰራዊት በታላላቆቹ አገራት የተገነባውን የአየር መከላከያ እንዳይሆን አድርገው እንዳሽቸው ሲጋልቡ ሊያስቆማቸው የቻለ ሃይል አለመኖሩን ኬቭ የሚገኙ የምዕራብና የአሜሪካ ሚዲያ ዘጋቢዎች ሳይውዱ በግዳቸው መስክረዋል።

እንደውም ፊታቸውን አዙረው ዜናውን ወደ ሰብአዊ ቀውስ በማተኮር እርዳታና ድጋፍ፣ እንዲሁም የጦር ወንጀል መፈጸሙን ልክ የኢትዮጵያ መከላከያ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን ሲመታ እንደሚያደርጉት የማስፈራራት አይነት እያደረጉ ነው።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ” ሩሲያ የማዕከላዊ መንግስቱን ለማፍረስ ፍላጎት ቢኖራትም። እዛው ኪዬቭ በመንግስት ማዕከል ከባልደረቦቼ ጋር እገኛለሁ። ጠላት እኔን በቅድሚያ፣ በሁለተኛ ደረጃ ቤሰቦቼ ላይ አነጣጥሯል” በማለት በአገራቸው ሚዲያ መናገራቸውን የዘገበው አልጃዜራ ነው።

በጥቅሉ “ተሸውደናል” ያሉት የዩክሬን መሪ ቃል ተንተርሶ አልጀዚራ አውሮፕና አሜሪካ ማዕቀብ ለማጥበቅ ሲዳክሩ የሩሲያ ጦር ቁልፍ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑ በምጸት ዘግቧል።

“የእጁና ታገናለች” ሲሉ የሩሲያን ኦፕሬሽን ያወገዙት የአሜሪካው አንጋፋ መሪ ጆ ባይደን ከግማሽ ቀን በሁዋላ ” ዓለም በጸሎቱ ከዩክሬን ጋር ነው” ማለታቸውን የሰሙ ይህን ባሉበት አውድ ስር የስድብና የውገዘት ምላሽ ተበርክቶላቸዋል። “አሜርካንን ያመነ፣ ጉም የዘገነ” እንዲሉ የሚለውን የኢትዮጵያዊያን ብሂል በተለያየ መልኩ አንጸባርቀዋል። “ለምርጫ ጥሩ የመወዳደሪያ አጀንዳ እያዘጋጃችሁ ነው። በርቱ” ይሉዋቸውም አሉ። አፍጋኒስታን ላይ የተፈጸመውን ክህደትም በስፋት ተነስቶ ባይደን ላይ መዛበቻ ሆኗል።

“We’re defending our country alone. The most powerful forces in the world are watching this from a distance,” አገራችንን ብቻችንን እየተከላከልን ነው። ከዓለም ታላቅ አቅም ያላቸው [በዩክሬን] የሚሆነውን በርቀት እያዩ ነው” ሲሉ አሜሪካን የተቹት የዩክሬን ፕሬዚዳንት፣ የትናንቱ ማዕቀብ ምንም እንዳላመጣ በመጠየቅ፣ በማዕቀብ ማጥበቅ ብቻ የሚሆን ነገር ባለመኖሩ የተግባር ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተማጽነዋል።

የፕሬዚዳንቱ እምባ ቀረሽ ወቀሳ ዩክሬን መከዳቷን በአደባባይ ያሳየ ነው። ልክ ትህነግ ሲሸነፍና በሁለት ሳምንት ከሰማይና ከምድር ተነርቶ የያዘውን ይዞ ወደ ትግራይ ሲያቀና ” አሜሪካ ነበረች አዲስ አበባ ግቡ ብላን የነበረችው” በሚል ክስ እንደተሰማው፣ ከቅርብ ጎረቤታቸው ጋር ሰላም ከማስፈን ይልቅ አላስፈላጊ የሴራ መረብ ውስጥ የወደቁት መሪ አሁን ላይ ከሩሲያ ጋር መደራደር እንደሚፈልጉ ቢያስታውቁም፣ ሩሲያ ወታደራዊ ሃይሉ ስልጣኑን እንዲረከብ ጥሪ አቅርባለች። ከወታደር ሃይሉ ጋር መነጋገር እንደሚቻልም አመልክታለች።

ትናንት ለዛሬ ከባድ ውሳኔ እንደሚወስን ቀጠሮ ይዞ የነበረው ኔቶም ያሰለፈውን መሳሪያ በዘረዘረበት ሙቀቱ ስለመቀጠሉ እስካሁን አመላካች ነገር የለም። ፑቲን ግን ከዩክሬን ስለቀረበው የ”እንደራደር” ጥያቄ ለፕሬዚዳንቱ በቀጥታ መልስ እንኳን ሊመልሱላቸው አልወደዱም። እንዲያውም ወታደሩ ስልጣኑንን እንዲረከብ፣ በሌላ አነጋገር ኩዴታ እንዲካሂድ ጥሪ አቅርበዋል። ምክንያቱም ሕዝብን መመሸጊያ አድርገው የሚቆምሩ የኔዮ ናዚ ስብስብ ለዩክሬን አጠቅምም ባይ ናቸው።

የዩክሬናዊያንን “ልጆቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን እና የሚወዷቸውን ሰዎች እንደ ሰው ጋሻ የያዙትን ክፍሎች ሊፈቅድላቸው አይገባም” ያሉት ፑቲን ወታደሩ ስልጣን ቢረከብ ለመነጋገርና ለመደራደር እንደሚቅል አመልክተዋል።

Leave a Reply