ከሃይል ሽኩቻው በተጨማሪ የዩክሬይን! ቁልፍ ጉዳዮች

እንግሊዝና አሜሪካ ሞስኮ ላይ ስለጣሉት ማዕቀብ ተፅዕኖ ከማውራታችን በፊት ይህን እንመልከት። “ዩክሬይን ወደ ሩሲያ ተጠቃለለች ማለት ምዕራባዊያን ሩሲያ የሚኖራትን ዓለም ዓቀፍ ተፅዕኖ በአይናቸው እያዩ አምነው ይቀበላሉ።” የሚለው በበርካታ ምዕራባዊ ምሁራን የተለያዩ ጥናቶችና መፃህፍት ውስጥ የተሰጠ ድምዳሜ ነው። ዩክሬይን በምዕራባዊያን ስር መቆየቷ ደግሞ አለማቀፍ የተፅዕኖ ሚዛኑን በምዕራቦቹ ስር እንዲቆይ እንደሚያችል በመግለፅ ጭምር። ከአውሮፓ አካባቢ በቆዳ ስፋቷ ሁለተኛዋ ዩክሬይን 43 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ናት፤ እንግዲህ ከሃይል ሽኩቻው በዘለለ ስለ ዩክሬን ከርስ ቁልፍ ጉዳዮቹ

የዩክሬን ቁልፍ ደረጃዎች

  • በአውሮፓ ቁጥር አንዱ ከፍተኛ ዩራኒየም ክምችት አላት
  • ቲታኒየም ማዕድን ክምችት ከአውሮፓ 2ኛ ከዓለም 10ኛ
  • በማንጋኒዝ ማዕድን ክምችት ከአለም ሁለተኛ፤ መጠኑም የአለማችንን 12% ክምችት ድርሻ ይሸፍናል።
  • በብረት ማዕድን ክምችት ከዓለም 2ኛ ስትሆን መጠኑም 30 ቢሊዮን ቶን፤
  • በሜርኩሪ ማዕድን ሀብት ክምችት ከአውሮፓ 2ኛ፤
  • የሼል-ጋዝ ክምችት መጠን ከአውሮፓ 3ኛ ከአለም 13ኛ
  • [በአጠቃላይ] በተፈጥሮ ሀብቶች ጅምላ ዋጋ ከአለም አራተኛ፤

በግብርና

▪️ዩክሬን ያላት ለም የእርሻ መሬት መጠን ከአውሮፓ 1ኛ ነው።

▪️የጥቁር-አፈር መሬት ሀብቷ ከአለም ሶስተኛው ሲሆን የአለምን 25% ድርሻ ይወስዳል።

▪️የሱፍ ዘይትና ራሱን ሱፍን ወደ ውጭ በመላክ ከዓለም ቁጥር አንዷ ዩክሬይን ናት።

▪️በማሽላ corn አምራችና ላኪነት ከአለም ሶስተኛ፤

▪️ዩክሬይን በድንች ምርት ከዓለም 4ኛዋ ደገኛ ሀገር ናት።

▪️በአጃ ምርት ከዓለም 5ኛ፤

▪️በንብ ማነብ ከዓለም 5ኛ ናት። አመታዊ ምርቷ 75,000 ቶን

▪️የጫጩት እንቁላል በማምረት ከዓለም 9ኛ

▪️ዩክሬን የእርሻ ምርት ለ600 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ፍላጎት ያሟላል፤

ዩክሬን በኢንዱስትሪ

▪️ከአውሮፓ 2ኛውና ከአለም 4ኛው ግዙፍ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ መሰረተ-ልማት በዩክሬን የሚገኝ ነው።

▪️በኒዩክሌር ማብላያዎቿ Installed capacity ከአውሮፓ 3ኛ ከዓለም 8ኛ

▪️ዩክሬን ያላት የባቡር ኔትወርክ ከአውሮፓ 3ኛ ሲሆን ከአለም 11ኛው ነው። ርዝመቱ 21,700 ኪ.ሜ፤

▪️የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ከአሜሪካና ፈረንሳይ በመቀጠል ከአለም ሶስተኛዋ፤

▪️በብረት ማዕድን እክስፖርት ከዓለም 3ኛ ትልቋ ላኪ ናት፤

▪️ለኑክሌር ኃይል ማመንጫዎች የሚሆነውን ተርባይን ኤክስፖርት በማድረግ ከአለም 4ኛዋ፤

▪️የሮኬት መተኮሻ አምርታ በመላክ ከአለም 4ኛዋ፤

▪️በሸክላ ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ፤

▪️በቲታኒየም ኤክስፖርት ከአለም 4ኛ

▪️የመከላከያ ኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ በዓለም 9ኛ ደረጃ

▪️በብረት ምርት ከአለም 10ኛዋ ስትሆን መጠኑም 32.4ሚሊየን ቶን ነው።

Esleman Abay የዓባይልጅ ✍️

Related posts:

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ጥብቅ ገደብ ጣለ
የ18 ዓመቱ ጎረምሳ በኒውዮርክ የገበያ አዳራሽ በጥይት እሩምታ አስር ሰው አጠፋ
ሕንድ ስንዴ ወደ ውጪ መላክ አቆመች
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ
የሶማሊያ ምርጫ ፣የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በአፍሪቃ
አቢሲኒያ ባንክ 60 ወለል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ሊያስገነባ ነው
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተሳሳተ መረጃ ስሜ ጠፍቷል ሲል ማብራሪያ እንዲሰጠው ቢቢሲን ጠየቀ
«የትግራይ ሕዝብ ያተረፈው መከራና ስቃይ ነው»
ከሶማሊ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ የአቋም መግለጫ
በድሬዳዋ ከተማ በነበረው ሁከት ተሳታፊ የነበሩ 89 ተጠርጣሪዎች ተያዙ
በሃይማኖትን ሽፋን የሚፈጸሙ የወንጀል ተግባራትን መንግሥት እንዲያስቆም የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ
“ሕገወጦች በድንጋይ ከሰል አመላላሽ አሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው”
"የሽብር ድርጊት በሚፈጠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን"
"ሃይማኖት የሰላም እንጂ በምንም ምክንያት የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም"
የፑቲን ቀጣይ ዒላማ - ኦዴሳ የወደብ ከተማ

Leave a Reply