ለአራተኛ ቀን ጦርነት በቀጠለባት ዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ፖላንድ ጉዞ መጀመራቸውን በጀርመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ ለቢቢሲ ገልጿል.
ኢትዮጵያውን ተማሪዎች ወደ ፓላንድ እንዲሻገሩ ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎ ጉዞ የጀመሩ መሆኑንም ቢቢሲ መረዳት ችሏል።
የሩሲያ ኃይሎች ወደ ዋና መዲናዋ ኪዬቭ መግባታቸው እየተነገረ ካለችው ዩክሬን ወደ ፖላንድ ለመውጣት በሚደረገው ሙከራ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክና የመኪና መጨናነቅ መኖሩም ተገልጿል
በተለይም ወደ ፖላንድ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ተማሪዎች እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን ሆኖም አንዳንድ በተዘጉ ስፍራዎች ላይ ያሉ ተማሪዎች መረጋጋት እስከሚፈጠር ድረስ የተወሰነ ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ ተብሏል።
.
via- @BBC New Amharic
Photo- African students at the Ukraine and Poland border