የአለማችን ግዙፉ የሩሲያ ኒዩክለር ተሸካሚ ሚሳኤል ምን ተአምር የማሳየት አቅም ያለው ይመስላችኋል ?

ሩሲያዊያኑ RS-28 #ሳርማት (RS-28 #Sarmat) ይሉታል: የአለማችን ግዙፉ ኒዩክለር ተሸካሚ ተምዘግዛጊ ባሊስቲክ ሚሳኤል ነው:: ምዕራባዊያኑ (አሜሪካና ሀያላኑ የኔቶ አባል ሀገራት) ደግሞ ‘#ሰይጣን 2’ ብለው ይጠሩታል:: ይህ በፈሳሽ ነዳጅ የሚንቀሳቀሰው (Liquid-fueled) የኒዩክለር ተሸካሚ ተምዘግዛጊ ባለስቲክ ሚሳኤል (#ICBM) በፕላኔታችን (በመሬት) ላይ መምታት የማይችለው ቦታ የለም:: በሰዓት 25,560 ኪ.ሜ. (25,560Km/h) ከፍተኛ ፍጥነት በመምዘግዘግ እስከ 18,000km ርቀት ላይ ያለን የትኛውንም ኢላማ መምታት የሚችለው ይህ ሚሳኤል ከሩሲያ የምድር ውስጥ ማስወንጨፊያ የሚሳኤል ሳይሎ (missile silo) አንዴ ከተተኮሰ በኋላ በአለማችን የትኛውም ጫፍ ላይ ያለን ቦታ ከአንድ ሰአት በታች በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደ አመድነት መቀየር ይችላል::

ይህ የአለማችን ግዙፉ የኒዩክለር አረር ተሸካሚ ICBM (intercontinental ballistic missile) የሚጓዘው ከድምፅ ፍጥነት በ21 እጥፍ አከባቢ (Mach 20.7) ሲሆን አንዱ ብቻውን የአሜሪካንን ቴክሳስ ግዛት አሊያም ሙሉ ፈረንሳይን በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አመድ ክምርነት መቀየር ይችላል:: ኔቶ (#NATO) “ሰይጣን-2” ብሎ የሚጠራውና በምዕራባዊያኑ በእጅጉ የሚፈራው ይህ የሩሲያ ኒዩክለር ተሸካሚ ሚሳኤል በአንድ ግዜ 10 ከባባድ ወይንም 16 መካከለኛ የኒዩክለር አረሮችን የሚታጠቅ ሲሆን የራሱ multiple independently targetable reentry vehicle (#MIRV) ስርአት አለው::

ይኸ ማለት ደግሞ ለምሳሌ ሩሲያ አንድ “ሰይጣን-2” ኒዩክለር ተሸካሚ ሚሳኤል አሜሪካ ላይ ብታስወነጭፍ ሚሳኤሉ ወደ ህዋ ተተኩሶ ፕሮግራም ወደተደረገለት የምድር ላይ ኢላማዎች ሲመለስ የታጠቃቸውን 16ቱንም የኒዩክለር አረሮች በአሜሪካ ከጫፍ እስከጫፍ በሚገኙ 16 ከተሞች ላይ እያንዳንዱን አረር ለየብቻ በእያንዳንዱ ከተማ ላይ ኢላማ በማድረግ በአንዴ 16ቱንም የአሜሪካ ከተሞች ወደ አመድነት በመቀየር ወደ ድንጋይ ዘመን ሊመልሳቸው ይችላል::

ሌላው በጣም የሚገርመው የዚህ ሚሳኤል ብቃት ደግሞ ከጠላት ሊተኮሱ የሚችሉ ፀረ-ሚሳኤል ሚሳኤሎችን መከላከል የሚያችለውን የራሱን ነፃ የፀረ-ሚሳኤል መቃወሚያ ስርአት (independent missile defence system) የታጠቀ የመሆኑ ነገር ነው:: በዋናነት ይኼን ሚሳኤል ለአሜሪካ ፀረ-ሚሳኤል መቃወሚያ ስርአቶች አይነኬ (immune) የሚያደርገው ግን ከፍተኛ ፍጥነቱ ነው:: ሩሲያዊያኑ ይህን ሚሳኤል አሁን ላይ በአለማችን ላይ ስራ ላይ ላለ የትኛውም የፀረ-ባሊስቲክ ሚሳኤል መከላከያ ስርአት ተጋላጭነት የሌለው (“#invulnerable”) ነው ይሉታል:: የሩሲያ የባሊስቲክ ሚሳኤል ኤክስፐርቶች ይኸንኑ ሲገልፁ “አንድ በሩሲያ ምድር ላይ ካለ የሚሳኤል silo ወደ አሜሪካ ምድር የተወነጨፈ “ሰይጣን-2″ ሚሳኤልን ለማክሸፍ አሜሪካ በትንሹ 500 ፀረ-ሚሳኤል ሚሳኤሎችን መተኮስ ይጠበቅባታል” ይላሉ::

ቀጣይ ክፍል ይቀጥላል

Via – #triangle of Afar

Leave a Reply