ሶማሊ ክልልና ሙስጣፌ ላይ ዘመቻ ተጀመረ፤ ክልሉን የጦር ማዕከል ለማድረግ ምክክር እየተደረገ ነው

  • በሶማሌ ክልል የታሰበው ብጥብጥ ከየአቅጣጫው ሃይል የሚሰባሰብለት ሲሆን ዋና ዓላማው የመንግስትን ሃይል ወደ ምስራቅና ወደ ምዕራብ ምስራቅ በመጎተት በወልቃይት ሰፊ ጥቃት ማድረግ ነው

የሶማሌ ክልል አንጻራዊ ሰላም ያላበት በመሆኑ ይህ እንዲቀየር እቅድ ተነድፎ እንቅስቃሴ መጀመሩና ዛሬ በናይሮቢ ሶስት ራሳቸውን “ድርጅት” አድርገው የሚጠሩ አካላት በዝግ ምክክር መጀመራቸው ተሰማ። ርዕዮትና 360 ርዕሰ መስተዳድ ሙስጣፌ ላይ ያነጣጠረ ቅስቀሳ ማካሄድ የጀመሩት በዚሁ ዕቅድ ሳቢያ መሆኑ ተሰምቷል።

ዜናውን ከናይሮቢ የላኩልን እንዳሉት በዛሬው ዕለት በዝግ እየመከሩ ያሉት የኦጋዴን ነጻ አውጪ መሪ አቶ አብዱራህማን መዴ፣ CSC ኮንግረንስ ፎር ሶማሌ ኮዝ (የሶማሌ ጉዳይ ኮንግረንስ ) አህመድ ባጃ እና የቀድሞ አልታድ አክራሪ ቡድን መሪ የነበሩት አቶ ኢብራሂም ደሬ ይመሩታል የተባለ ድርጅት ናቸው።

ስብሰባው ሌሎች አመራሮችም ያሉበት ሲሆን የትህነግ ሰዎች እንደሚመሩት የዜናው ሰዎች አመልክተዋል። ከትህነግ የተወከሉት ማን እንደሆኑ ባይገለጽም ስብሰባውን የሚመሩት የትህነግ ተወካዮች እንደሆኑ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል።

የስብሰባው ዋና ዓላማ የሶማሌ ክልል ላይ የትጥቅ ትግል በአስቸኳይ የሚስፋፋበትንና፣ ከአፋር ክልል የሚነሳ ሃይል ወደ ሶማሌ ክልል ለመግባት እንዲችል ግጭቱን በማስፋት ሃይል እንዲበታተን ማድረግ እንደሆነ ተመልክቷል።

መንግስት ከሶማሌና ኪንያና መንግስታት ጋር በመነጋገር በድንበር አካባቢ ያለውን እንቅስቃሴ ለማምከን አስቀድሞ ዝግጅት ማድረጉን ማስታውቁና የሁለቱ አገራት የጸጥታ ሃላፊዎች አዲስ አበባ ተገኝተው ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

የዜናው ሰዎች እንዳሉት ይህንኑ ሶማሌ ክልል ላይ የታሰበውን ረብሻ ተንተርሶ የክልሉን መሪ አቶ ሙስጣፌን ስም በፈጠራና በተጋነነ መልኩ ማጠልሸት መጀመሩ ከዚሁ ውጥን ጋር ተያያዥነት እንዳለው አመልክተዋል። አቶ ሙስጣፌን ለመከላከል ሳይሆን ርዕዮት በተባለው የትህነግ ደጋፊ ሚዲያ የቀረበው የስም ማጥፋት ዘመቻ እነ ፌይሰልና ሃሰን ኬናን እንዳዘጋጁት ገልጸዋል።

ይህ የሆነው የክልሉ አስተዳደር በነዋሪው ድጋፍ እንዳያገኝ ሲሆን በዋናናት አቶ ሙስጣፌን ከአመራሩና ክህዝቡ ለመነተል ነው። ርዕዮትና 360 የሚባለው የቀድሞ የትህነግ ካድሬዎች የሚመሩት ሚዲያ በተመሳሳይ ቀን የጀመሩት የስድብ ዘመቻ የዚሁ ክልሉን ወደ ቀውስ ማዕከል የመቀየር ዓላማ ያለው እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ሙስጣፌ የዘር ፖለቲካን በመቃውቀም የሚያራምዱት ፖለቲካ በትህነግ ደጋፊዎችና አመራሮች በከፍተና ደረጃ ተቃውሞና ዛቻ የገጠመው ገና ከጅምሩ እንደሆነ ይታወቃል።

በወልቃይት አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ በወዳጆቹ የሚነገርለት ትህነግ፣ የአፋር ክልል መሪና የሶማሌ ክልል መሪን በበቀለ እንደሚፈልጋቸው ሰሞኑንን በተደጋጋሚ በድርጅቱ ወዳጆች አማካይነት እየተገለጸ ነው።

አቶ ሙስጣፌን የሚያወግዘውን መረጃ በማዘጋጀት ስማቸው የተነሳው አቶ ፌይሰል፣ በትግራይ ሚዲያ በቀጥታ ቃለ ምልልስ ያደረጉና፣ ዩ ኤም ዲ በሚባለው የዩቲዩብ አውድ ዘወትር አርብ እየቀረቡ በስማሌ ክልል ላይ ተቃውሞ እንዲነሳ ቅስቀሳ የሚያቀርቡ መሆናቸውን የዜናው ምንጮች አመልክተዋል።

ዩኤምዲ አቶ ጌታቸው የሚመሩት በኤድመንተን ካናዳ የተተከለ የትህነግ ልሳን ሚዲያ መሆኑ የነገራል። ይህን ዜና የላኩት እንዳሉት በስመ አማራ ተቆርቋሪ የሆኑ “አንቂዎች” ነን ባይ ካድሬዎች ከትህነግ ጋር ሆነው አቶ ሙስጣፌ ላይ ለምን ዘመቻ እንደክፈቱ የሚያውቋቸው ሚዲያዎች ማብራሪያ ቢጠይቁዋቸው መልካም እንደሚሆን አመልክተዋል። በዚህ የትህነግ ዕቅድ ውስጥ የአማራ ተሳታፊ መሆንንና የሶማሌ ክልል እንዲበጠበጥ መተባበር ምን ፖለቲካዊ ፋይዳ እንዳለው መረዳት ለውደፊቱ የታሪክ ዝክር ለማስቀመጥ እንደሚረዳል አመልክተዋል።

አቶ ሙስጣፌ በሶማሌ ክልል የተፈጸመውን የመብት ጥሰትና ግፍ ለዓለም በማሳወቅ በዓለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት እንደሚሰሩ፣ ሁሉም ብሄረሰቦች በነጻነት እንዲኖሩ የፈቀዱና የሶማሌ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሁሉ ፓርቲያቸውን እንዲቀላቀል በይፋ ጥሪ ማቅረባቸው በአክራሪ ፖእቲከኞች ዘንዳ የተወደደላቸው እንዳልሆነ ተጠቅሶ በርካታ ዘገባ መውታቱ ይታወስል።

You may also like...

Leave a Reply