*የላቀ የጦርሜዳ ኒሻን ተሸላሚው

በ1969 ዓ.ም ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወርር፣ ከዘመቱት 300 ሺህ ሚሊሺያዎች አንዱ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ እንዴት ተመለመሉ? ያኔ እድሜዎ ስንት ነበር?
በወቅቱ ሶማሊያ በምስራቅ ኢትዮጵያ 700 ኪ. ሜትር፣ በምዕራብ 300 ኪ. ሜትር ወደ አገራችን ዘልቃ ገብታ ነበር፡፡ ወንድ ልጅ እንዴት አገሩን ለጠላት ሰጥቶ ይቀመጣል የሚል የቅስቀሳ ዘመቻ ነበር፡፡ በወቅቱ ልጅ ነበርኩኝ፡፡ ከአውሬ በስተቀር ሰው ላይ ተኩሼ አላውቅም፡፡ እርግጥ አውሬ በምናድንበት በኩል ሱዳኖች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሲገቡ እንመልሳቸው ነበር፡፡ እኛ ሳንተኩስ እነሱ ይሸሻሉ፡፡ እኛም የጥይቱ ውድነት ስለሚያሳሳን ቶሎ አንተኩስም ነበር፡፡ እና ያ ቅስቀሳ ሲደረግ ለመዝመት ወደ አውራጃ መጣሁ፡፡ ወቅቱ 1969 ዓ.ም ነው፡፡ “አንተ ልጅ ነህ አትሄድም” ተባልኩኝ። “ከኔ በላይ አትተኩስም፤ ስለዚህ ተወኝ” አልኩት አዛዡን፡፡ “አትሄድም” ሲለኝ ዘልዬ ኤኔትሬ ላይ ወጣሁ፤ ጎትተው አወረዱኝ፡፡ እንደገና በትግል ወጣሁና አብሬ ሄድኩኝ፡፡ ያኔ እድሜዬ 15 ዓመት ቢሆን ነው፡፡
ከዚያ ወደ ታጠቅ ጦር ማሰልጠኛ ነው የገባነው፡፡ ወቅቱ ዝናብ ስለነበር ታጠቅ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ጭቃው ያስቸግራል፤ በቂ የምግብ አቅርቦትም አልነበረም፡፡ በዚህ ምክንያት ከታጠቅ ማዶ መንደር አለ፤ እዚያ እየሄድኩ ቂጣ እየነጠቅኩ እሮጥ ነበር። ብር የለማ—ምን ልክፈል?! እንዲህ እንዲህ እያልን፣ ሶስት ወር ሰልጥነን ቀጥታ ወደ ጦር ግንባር ተላክን፡፡ ግንባሩ ሀረር ቢል ሲዲሞ ይባላል፡፡ በመጨረሻ ውጊያው ተጀመረ፤ ሰው ዝም ብሎ ይተኩሳል፤ እኔ ግን አልተኩስም ነበር፡፡
ለምን ነበር የማይተኩሱት?
ምን አይቼ ነው የምተኩሰው? ሌሎች አለቆቼም ለምን አትተኩስም ይሉኛል፡፡ በእኔ እምነትና ልምድ፣ያለ ኢላማ አንድም ጥይት መተኮስ ኪሳራ ነው፡፡ “ዝም ብለህ ተኩስ አትበሉኝ፤ ስተኩስ ግን የእኔ ጥይት መሬት ካረፈ ወደ አገሬ መልሱኝ፣ ያለ ኢላማ ግን አልተኩስም” አልኩኝ፡፡ ከዚያ ቢል ሲዲሞ ስንገባ፣ ሶማሊያ የአካባቢውን ት/ቤት አቃጥላ፣ በታንክና በመድፍ ታጅባ እየገፋች መጣች። ውጊያ ላይ የሆነች ጥይት ወደኔ ጩ…ጩ…ጩ… እያለች ትመጣለች፡፡ እኛ ተኝተናል፡፡ “የታለች? እንዴትስ ልተኩስ?” አልኩኝ፡፡ አለቃዬ ኮ/ል ገበየሁ አበበ ይባላሉ፡፡ በቀደምም በኔ ህይወት ላይ በተፃፈው መፅሐፍ ምርቃት ላይ ተገኝተው ስለኔ ምስክርነት ሰጥተዋል፡፡ “እንዴት ዛሬም አልተኮስክም” ብለው ተቆጡኝ፡፡ “እኔ አላየሁም፤ ጠላት ወደ ሰማይም ወደ ምድርም ይተኩስ፣ሳላይ ጥይት አላባክንም” ብዬ እምቢ አልኩኝ፡፡ በነጋታው ጠዋት ሁለት ሰዓት ላይ፣አንድ የእኛን ወታደር እጁን በምስማር ግራና ቀኝ ቸንክረው፣ በቁመናው ስጋውን ዘልዝለውታል። ቦታው ላይ ስደርስ፤ “ወገኔ ነህ፤ እንዲህ ከምሰቃይ ጨርሰኝ” አለኝ፡፡ “አልጨርስህም” አልኩት፡፡
ለምን?
“እኔ አንተን አልጨርስህም፤ አንተን እንዲህ ያደረገህን ጠላት ግን እጨርስልሃለሁ” ብዬ ቃል ገብቼለት አልፌው ሄድኩኝ፡፡ ከዚያ መቶ አለቃ ሙለታ ደልሳ የሚባል አለ፡፡ “ያውልህ ጠላት፤ እንጨቱ ስር” አለኝ፡፡ “አይቼዋለሁ ዝም በል” አልኩትና ሳልንበረከክ፣ ቁጭ ብዬ ግንባሩን አፈረስኩት፡፡ በነገራችን ላይ እኔ አንድም ቀን አውሬም ይሁን ሰው ከአንገት በታች መትቼ አላውቅም። በፊት ስናድን ቆቅ ለመብላት ስጋዋ እንዳይበላሽ አልመን የምንመታት ራሷን ነው፡፡ ከአንገት በታች የተመታ ጠላት ካለ፣የእኔ አይደለም፡፡ እናም ያንን መትረየስ ተኳሽ ግንባሩን ካልኩት በኋላ “ያው ሰውየው ወድቋል” አልኩት ለመቶ አለቃ፡፡ ይህን እያልኩ እያለ የሟቹ ረዳት መጥቶ …
ከ Benju ገጽ

Leave a Reply