የኩላሊት ህመም ምልክቶች

የኩላሊት ምልክቶች ሕመም አብዛኛውን ጊዜ ምልክት የለሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የህመም ምልከቶች ከታዩም ደግሞ ከህሙማን ሕሙማን ይለያያሉ፡፡ በተለይ የሕመሙ መጀመሪያ አካባቢ መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አበይት ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

• የፊት እብጠት

ብዙ ጊዜ የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት የኩላሊት ህመም መለያ ናቸው፡፡ በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋን በታች ሊከሰት ይችላል፡፡ (ይህ የፔሪኦሮቢታል እብጠት ይባላል) በተለይ በማለዳ ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን ሁሉም እብጠት የ የኩላሊት ሕመምን ያመለክታል ማለት አይደለም፡፡ በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ ይችላል፡፡

• የምግብ ፍላጎት ማጣት

ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ምልክቶች ናቸው::

• ከፍተኛ የደም ግፊት

አብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል።

• የደም ማነስ እና ድክመት

የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት ዋንኛ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አነዚህ ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል። ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -መለስተኛ ደረጃ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በልጆች ላይ ደግሞ በሚገባ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የእግር አጥንት ቀጥ አለማለት የህመሙ መኖር ማሳያ ነው፡፡

ብዙ ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች

1. የሽንት መጠን መቀነስ የኩላሊት ህመሞ በጣም የተለመደ ነው።

See also  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተወሰኑ የሠራዊቱ አባሎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ

2. በመሽናት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት እና የሽንት ቧንቧ ህመም በሽታውን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።

3. የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማውጣት ችግር ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሐኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

[ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ]

ጤናመረጃMedicalInformation

Leave a Reply