አይ ኤም ኤፍ በዩክሬንና ሩሲያ ግጭት ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ለተጎዳ የአፍሪካ ሀገራት 50 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ለተጎዱ የአፍሪካ ሀገራት 50 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ ተገለፀ።

ቀደም ሲል በኮቪድ -19 ከተፈጠረው የኢኮኖሚ ድቀት ለማገገም የሚታገለው የአፍሪካ ኢኮኖሚ በዩክሬን ጦርነት ሌላ ጫና ላይ መውደቁ የአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ዳይሬክተርዋ ከአፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ ከማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተወካዮች ጋር በዩክሬን ያለውን ቀውስ ሊያደርስ ስለሚችለው ተፅእኖ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም በጦርነቱ ምክንያት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የምግብ ዋጋ መናር፣ የዕዳ አገልግሎት ግዴታዎች እንዲሁም ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ማጣት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።

ከአፍሪካ አገራት 12 የሚሆኑት ብቻ የተጣራ ኢነርጂ ላኪዎች ሲሆኑ ቀሪዎች 42ቱ አገራት ደግሞ ኢነርጂ አስመጪዎች መሆናቸውን ጠቅሰው “ያላቸው የበጀት ቦታ ውስን በመሆኑ ይህ በጣም አስደንጋጭ ነው” ይላሉ።

“በርካታ የአፍሪካ አገራት የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ አለመቻላቸውን አንስተው ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያሉት ተጠቃሽ መሆናቸው ገልፀዋል።

ከሩሲያ እና ዩክሬን የሚመጡ የስንዴ ምርት ተያይዞ በአንዳንድ ሀገሮች ላይ ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት መስተዋሉንም ጠቁመዋል።

ከስቴለንቦሽ ዩኒቨርሲቲ ቫንዲል ሲህሎቦ ባደረገው ትንተና “የአፍሪካ አገሮች በ2020 4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የግብርና ምርቶችን ከሩሲያ ማስገባታቸው አንስቷል።

“ከዚህ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ስንዴ ሲሆን 6 በመቶ ደግሞ የሱፍ አበባ ዘይት እንደነበረ ጠቁሟል።

ግብፅ ግማሽ የሚጠጋ ድርሻ የነበራት ሲሆን ሱዳን፣ ናይጄሪያ ታንዛኒያ፣ አልጄሪያ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ድርሻ እንደነበራቸው አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ውይይቱን ተከትሎ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን አገሮች የመቋቋም አቅምን ከፍ ለማድረግ በዘላቂነት እንዲያገግሙ ለማበረታታት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም 50 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል። EBC

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply