በትናንትናው እለት በሿሿ ዘረፋ የከተማውን ነዋሪ ሲዘርፉ የነበሩት መጨረሻቸው ሞት እና ከባድ ጉዳት ሆኗል::

5L ሚኒባስ ኮድ 3 75549 በትናንትናው እለት መነሻቸውን ሰሜን ሆቴል አድርገው አዲሱ ገበያ፣ አስኮ፣ ጦር ኃይሎች፣ ገላን፣ ቱሉ ዲምቱ… ከተማውን እያካለሉ ሿሿ የሚሰሩ ዘራፊዎች ነበሩ። ቱሉ ዲምቱ አደባባይ ጋር ተረኛ ተዘራፊ ቆማ ታክሲ እየጠበቀች የት ነሽ ሲሏት “መገናኛ” ነኝ ትላለች። ከዛ 3ኛ ወንበር ላይ 3ኛ ሆና ተደርባ ተቀመጠች።

አጠገባ የነበረችው ረዳቱን “እንዴት እርጉዝ ሆኜ ሶስተኛ ትደርብብኛለህ” ስትል በቃ እህቴ እኔ እነሳለሁ ብላ ተደርባ የገባችው ተነሳች ይሄኔ ወዲያ “ትራፊክ ትራፊክ፣ ዝቅ በይ” ብለው አዋከቡኝ በዛ መሃል ዘመናዊ ስልኬን ከቦርሳው ወስደው ነበር። በቃ ትራፊክ አለ ውረጂ አሉኝ እና አስወረዱኝ። ከወረድኩ በኋላ ነበር ስልኬን መሰረቄ ያወኩት

እሷን ካወረዱ በኋላ ወደ ሌላ ተዘራፊ ፍለጋ ይሄዳሉ ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሲደርሱ 5:00 ሰዓት አካባቢ መኪናቸው ከሲኖ ትራክ ጋር ተጋጭቶ ሹፌሩን ጨምሮ 3 ሰዎች ህይወታቸው ያልፋል 8 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ይወሰዳሉ።

ፖሊሶች ነብረቶቹን ሰብስቦ ይዞ ነበር በዚህ መሃል አንድ ስልክ ይደወላል ይሄኔ ፖሊሶቹ የተጎጂዎቹን ቤተሰቦች ልናገኝ እንችላለን በሚል ስልኩን ያነሳሉ ይሄኔ “እባካችሁ የምትፈልጉትን ብር እንስጣችሁ ስልኩ ውስጥ ብዙ ዶክመንት አለ ስልኩን መልሱልኝ” የሚል ተማፅኖ ፖሊሶቹ ይሰማሉ።

ፖሊሶቹ ደንግጠው የማን ዘመድ ናችሁ ይላሉ “ዘመዴ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ስልኳን ታክሲ ውስጥ ተሰርቃ ነው እሱን እንደከመልሱ ነው” ትላለች። ይህ ጉዳይ የፖሊሶቹን ቀልብ ስቦ ተጨማሪ ክትትል ያደርጋሉ። ይሄኔ አደጋው የደረሰባቸው በከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታ እየተዟዟሩ በስርቆት ወንጀል የተሰማሩ ዘራፊዎች ሆኖ ይገኛሉ።

#drivinginethiozia

Leave a Reply