ፑቲን ዶላር የሚታመን መገበያያ አይደለም አሉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸው ከዚህ በኋላ ጋዝ የምትሸጠው በራሷ የመገበያያ ገንዘብ “ሩብል” እንዲሆን መወሰናቸውን RTን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ፕሬዝዳንቱ ወደ አውሮፓ የሚደረገው የጋዝ ሽያጭ በሩሲያ ገንዘብ እንዲሆን ውሳኔ ማስተላለፋቸው ታውቋል። የዚህ ውሳኔ ተግባራዊነትም በፍጥነት እንደሚከናወን ሩስያ አስታውቃለች።

RT እንደዘገበው ሞስኮ ከዚህ በኋላ ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ጋር ” በዩሮም ሆነ በዶላር የመገበያየት ስሜት የላትም “ብሏል። ቭላድሚር ፑቲን ዶላር የሚታመን የመገበያያ ገንዘብ እንዳልሆነ መናገራቸውን RT ዘግቧል።

የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ እና የካቢኔ አባላት ከአውሮፓ ጋር በሩብል የሚካሄደውን ግብይት በተመለከተ በአንድ ሳምንት ውስጥ ውሳኔ እንዲያስቀምጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ምንም እንኳን የተለያዩ ሀገራት የሩሲያን ሀብት ቢያግዱም ሀገራቸው ግን በገባችው ውል መሰረት ነዳጅ ማቅረቧን እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

ምንጭ፦ RT/አል ዓይን ኒውስ

See also  ዲጂታል ሚዲያዎች የጋዜጠኝነት ሙያዊ ሥነ ምግባርን ተከትለው መስራት ይጠበቅባቸዋል

Leave a Reply