ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማኔጅመንት ቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ – ተወልደ ገብረማርያም ለቀቁ

አየር መንገዱን ከአቶ ተወልደ በፊት ለሰባት አመታት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የማኔጅመንት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል :: አቶ ተወልደ ገብረማርያም በህመም ምክንያት በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀዋል::

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ ግሩፕ የማኔጅመንት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በህመም ምክንያት በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በህመም ምክንያት አሜሪካን ሀገር ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ሙሉ ትኩረታቸውን በህክምናቸው ላይ ለማድረግ ለቦርዱ በኢሜል ማቅረባቸውን የገለጸው አየር መንገዱ፤ ቦርዱ ዛሬ ባደረገው ስብሰባው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከኃላፊነታቸው ለቀዋል ሲል አየር መንገዱ አስታውቋል።

አየር መንገዱ በዚሁ መግለጫው የቀድሞው የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የማኔጅመንት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል ብሏል።

አቶ ግርማ አየር መንገዱን ከአቶ ተወልደ በፊት ለሰባት አመታት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መምራታቸው ይታወሳል። ENA

Leave a Reply