ከባሕር ዳር – ዳንግላ በሚሄደው 66KV የኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ላይ የታወር ብረት ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ መሆኑን የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር 8ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የቴክኒክ ምርመራ ተወካይ ሳጅን ስጦታው ንጉሴ ገልጸዋል፡፡

ሳጅን ስጦታው እንደገለፁት ሁለት ተጠርጣሪዎች በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አዲስ ዓለም ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በአካባቢው አስተዳደርና የፀጥታ አካላት ቅንጅት መያዛቸውንና ያልተያዙ ተርጣሪዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠርጣሪዎችን ለያዙና ቀሪዎችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ላሉ የፀጥታ አካላት ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል፡፡

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት በአገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። በየደረጃው የሚገኝ የፀጥታ አካል በአካባቢው ለተዘረጉ የኤሌክትሪክ አውታሮች ጥበቃ እንዲያደርግና ሕብረተሰቡም አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲመለከት ለሚመለከታቸው ጥቆማ እንዲሰጥ የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጠይቋል።

ከባሕር ዳር – ዳንግላ የሚሄደው ኤሌክትሪክ አስተላለፊ መስመር ተጠግኖ አግልግሎት መሥጠት መጀመሩ ይታወሳል።

(አሚኮ)

Leave a Reply