የኦፌኮ ጉብኤ መረራን መሪ አድርጎ ሰየመ፤ ኦነግና ዳውድ እንዴት እንደሚቀጥሉ እየተጠበቀ ነው

ኢፌኮ መሪዎቹን መረጠ። ኦነግ ለሁለት በመከፈሉ ገና መደበና ጉባኤውን እንዴት አካሂዶ ሪፖርት እንደሚያቀርብ እስካሁን የታወቀና የተሰማ ነገር የለም። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ ሲሰየም፣ አቶ በቀለ ገርባን ደግሞ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር ፣ አቶ ጁሐር መሀመድን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ይፋ አድርጓል።

ፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄድ ባለበትና የደረሰበትን ሪፖርት ሲያድርግ እንዳስታወቀው 17 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል። በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፥ ህብረ ብሄራዊ ወይም ፌዴራሊዝም ማለት ሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊ የሚሆኑበት ስርዓት ነው ማለታቸውን ፋና ዘግቧል። አክለውም ለሰላምና እና ለሀቀኛ ዲሞክራሲ ለሚደረገው ትግል፣ ሀገሪቱን ለመለወጥ እና ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ትግል ፓርቲያችን የራሱን አስተዋፅኦ ያርጋል ማለታቸውን አስታውቋል።

በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ጫናና የቢሮ መዘጋት ከምርጫ መውጣቱን ፕሮፌሰር መረራ በጉባኤው መክፈቻ ላይ አመልክተዋል። ለሁለት ቀናት እየተካሄደ ባለው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤው ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ጉባኤው ሲጠናቀቅ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች መደበኛ ጉባኤያቸውን በወር ጊዜ ውስጥ እንዲያካሂዱ መመሪያ ማስተላለፉ ይታወቃል። በዚሁም የኦነግ መሪ የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳም ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ምርጫ ቦርድ ባዘዘው መሰረት ጉባኤ ለማካሄድ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑ ተሰምቷል። ኦነግ ለሁለት በመከፈሉ የስብሰባው አካሄድ እንደኤት እንደሚከናወን እስካሁን ከሁለቱም ወገን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ዳውድ በነሳነት መንቀሳቀስ መጀመራቸው ከመገለጹ ውጪ በእነ አራርሳ ከሚመራውና እሳቸውን በድምጽ ብልጫ በዲሲፒሊን ግድፈት አማባረሩን ከሚገልጸው አካል ጋር እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል፣ ማን ምርጫ ቦርድ ላይ በቀጣይ የኦነግ ባለቤት እንደሚሆን ደጋፊዎችና አባላቱ በጉጉት የሚከታተሉት ጉዳይ መሆኑ ተሰምቷል።

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply