ጌራሲሞቭ የፑቲን ቀኝ እጅና የጦርነት ዶክትሪን ባለቤት

የሩሲያ ጦር ኢታማዦር ሹም ነው፡፡ ምስጢራዊ እና ውስብስብ፤ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ ጦረኛ ነው፡፡ በዓለም ስሙን ያገነነለት የራሱ የሆነ የጦርነት ዶክትሪን አለው፣ ጌራሲሞቭ ዶክትሪን ይባላል፡፡ መከላከያውን የማደራጀት ብቃቱ እና ለአገሩ ሩሲያ ያለው ፍቅር በወዳጆቹም በጠላቶቹም ይመሰከርለታል፡፡ “Hero of the Russian Federation” የሚል ማዕረግ ተሰጥቷል፡፡ ይህን የጦር አርክቴክት ጄነራል ቫለሪ ጌራሲሞቭን ተዋወቁት

  • ጄኔራል ቫለሪ ቫሲሊዬቪች ጌራሲሞቭ እ.ኤ.አ በ1955 በቮልጋ ወንዝ ዳርቻ በካዛን ከተማ የተወለደ ሲሆን በ1977 ገና በወጣትነት ዕድሜው የሶቪየት ሕብረትን ጦር ተቀላቅሏል፡፡ በክፍል ስልጠናና በተግባር ልምምዶች እጅግ ውጤታማ በመሆኑ ደረጃዎችን በፍጥነት በመዝለል የ58ኛው ክፍለጦር ዋና አዛዥ ሆነ፡፡
  • የእርሱ ክፍለጦር ያለበት አካባቢ የቺቺንያ አማጺያን ለሩሲያ ፈተና የሆኑበት የጋረጡበት በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ሁለተኛው የሩሲያ እና ቺቺንያ ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ በመጀመሪያ ጦርነት የሽንፈት ካባ የተከናነበችው ሩሲያ በዚህኛው ዙር ስትራቴጂ ለመበቀል የመጣች በመሆኑ ለጌራሲሞቭ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፡፡ የቺቺንያን አማጺያን ወደ ሩሲያ በመገልበጥና የተቀናጀ ጥቃት በመፈጸም ሩሲያ ዘመቻዋን በስኬት ስታጠናቅቅ የጌራሲሞቭም ስም በሩሲያውያን ዘንድ እየታወቀ መጥቷል፡፡
  • በመሆኑም ጌራሲሞቭ የሩሲያ ሩቅ ምስራቅ ዲስትሪክት ጦር ዋና አዛዥ ሆነ፡፡ በመቀጠልም የሩሲያና ሴንት ፒተርስበርግ ጦር ዲስትሪክት ዋና አዛዥ ለመሆን በቃ፡፡ ኋላ ላይ ከወቅት ኢታማዠር ሹም ኒኮላይ ማካሮቭ ጋር በተፈጠረ መቃቃር የማዕከላዊ ዲስትሪክ አዛዥ ተደርጎ ነበር፡፡ ኋላም የሩሲያን የድል ቀን በሚዘከርበት ዕለት የሚቀርቡ ወታደራዊ ትርዒቶችን እንዲያዘጋጅ ተደረገ፡፡ በመጨረሻም በ2012 ስል አዕምሮውንና የማደራጀት አቅሙን የሚያውቀው ፑቲን ማካሮቭን በማንሳት አዲሱ የሩሲያ ኢታ ማዦር ሹም አድርጎ ሾመው፡፡

ጌራሲሞቭ ዶክትሪን ምንድነው?

  • ጌራሲሞቭ በመላው ሩሲያ ዝነኛ ቢሆንም በዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ስለ ጦር ፍልስፍናው የታወቀ ነገር አልነበረውም፡፡ ነገር ግን በ2013 ዓ.ም ካደረገው ንግግር በመነሳት የምዕራባውያን ሚዲያዎች ጌራሲሞቭ ዶክትሪን ብለው የሚጠሩት የጦርነት ፍልስፍና በስፋት ዘገቡለት፡፡ ዶክትሪኑ በአጭሩ የድብልቅ ጦርነት (Hybrid warfare) የሚባል ሲሆን ለአንድ ወታደራዊ ዘመቻ ስኬት ከመደበኛ የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ የውሸት መረጃዎችንና የሳይብር ጥቃቶን አደባልቆ መጠቀም የሚለው ነው፡፡
  • በመሆኑም ሩሲያ አንድ ውጊያን ስታቅድ አብራ የቴክኖሎጂ፣ የመረጃ፣ የዲፕሎማሲያዊ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና ሌሎችም በርካታ መሳሪያዎችን በአግባቡ እንድትጠቀም ያበረታታል፡፡ በቀጥታ በወታደራዊ ዘመቻው የሚሳተፉ ወታደሮችም በቅድሚያ የጠላትን የኢኮኖሚ መሰረተ ልማቶች እንዲያወድሙ ትዕዛዝ ይሰጣቸዋል፡፡
  • ዓለምን ባስደመመ ሁኔታ ጄነራሉ እያንዳንዱን ስትራቴጂውን ሩሲያ ክሬሚያን ስትወርር ተገበረው፡፡ የሩሲያ መንግስት ከወረራው አስቀድሞ በሶሻል ሚዲያዎች የአካባቢው ህዝብ መንግስት ላይ እንዲያምጽ ማበረታት ጀመረ፡፡ ስውር ኦፕሬሽን በመጠቀም በአካባቢው ውጥረት የሚፍጥሩና የዩክሬይን መንግስት አካባቢውን ለመቆጣጠር እንዲቸገር የሚያደርጉ ረብሻዎችና አለመረጋጋቶች እንዲፈጠሩ አደረጉ፡፡
See also  በአዲሱ የአብርሆት የህዝብ ቤተመፃሕፍት ደጃፍ የቆመው ኪነ ሀውልት ትርጉም ምንድን ነው?

Via fast info tube

Leave a Reply