“ዓላማችን ዶንባስን ነጻ ማውጣት ነው” ሩሲያ አልተሳክቶም?

አሁን አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ሩሲያ በጦርነቱ ያሰበችውን ያህል እንዳልተሳካላት የሚያመላክቱ ሆነዋል። ዘመቻው የተለመደው የምዕራቡ አለማት የወሬ ክተት እንጂ በተግባር ሩሲያ ዩክሬንን በምትፈልገው ደረጃ ደቁሳለች የሚሉም አሉ።

“ኮሎኔል ጀኔራል ሰርጌ ሩድስኮይ አሁን የዩክሬን ወታደራዊ ኃይል ለሩሲያ ስጋት ሊሆን በሚችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ሙሉ ትኩረታችን ዶንባስን ነጻ ለማውጣት አድርገናል” ማለታቸው የሽንፈት ምልክት እንደሆነ ተሰምቷል። እንደውም የሩሲያ ጀነራሎች ሞት ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ማለቱና በአንዳንድ አካባቢ የዩክሬን ጦር ማጥቃት ማጀመሩን ተከትሎ የተሰጠ መግለጫም ሆኖ ተወስዷል።

የሁለቱ ሀገራት ጦርነት መጨረሻው ወዴት እንደሚያመራ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ የሚገልጹ ተንታኞች ሩሲያ ዶንባስን ነጻ ለማውጣት በሚል ያቀረበችው የአሁኑ እቅድ የቀደመ ሽንፈቷን ለመሸፈንና ኃይሏን በድጋሚ ለማደራጀት ማቀዷን አመልካች መሆኑንን እየገለጹ ነው። ነገሮች አሁን ካሉበት አልፈው ከተባባሱና ጣላቅ ገብነት ካለ ሩሲያ ኒኩሌር ለመተቀም መዛቷ ከዚሁ ያሰበቸው ካለመሳካቱ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ የሚናገሩም አሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ የሚያውሉ ከኾነ ኔቶ «ምላሽ» ይሰጣል ብለዋል። ፕሬዚደንቱ ይህን ያሉት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ከአውሮጳ ኅብረት እና ቡድን ሰባት ሃገራት ጋር ቤልጂየም ብራስልስ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደኅንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ደግሞ ሩስያ «ከባድ ዋጋ» ትከፍላለች ብለዋል። ሆኖም ግን «ዩናይትድ ስቴትስ የኬሚካል ጦር መሣሪያ የመጠቀም አንዳችም ፍላጎት የላትም» ሲሉ አክለዋል።

የአሜሪካና የሌሎች ሀገራት የጦር መሳሪያዎች እና ወታደራዊ ቁሳቁስ ወደ ዩክሬን እየገቡ መሆናቸውን ተከትሎ የሩሲያ ወታደራዊ ኃይል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባቱ የምዕራቡ አገራት ሚዲያዎች በስፋት እየወተወቱ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች የዩክሬን ወታደራዊ ኃይል ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሸጋገሩን የሚያሳይ ማስረጃ እንዳለም የአሜሪካ ባለሥልጣናት መናገራቸውን እየጠቆሙ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይም የዩክሬን ወታደራዊ ኃይል በጥቁር ባህር ዳርቻ አካባቢ ትልቅ የሩሲያ መርከብ መምታታቸው ተነግሯል።

ይህ ብቻ አይደለም በደቡብብ ዩክሬን ኬርሶን ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ያኮቭ ሬዛንትሴቭ የተባሉት የሩሲያ ትልቅ ጄነራል ህይወታቸው ማለፉን የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ጄነራል ሬዛንትሴቭ የሩሲያ 49ኛው ጥምር ሠራዊት አዛዥ እንደነበሩ ጥቅሶ ሞታቸውን ያስታወቀው ቢቢሲ ነው። ሌሎች ሚዲያዎችም ተቀባብለውታል። በዚህም የሩሲያ ጀነራሎች ሞት ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ማለቱ እየተሰማ ነው። ሩሲያ ግን ያመነችው የአንድ ጀነራል ህልፈትን ብቻ ነው።

የኔቶ አባል አገራት እየጋዙ ያለው የጦር መሳሪያ፣ እያጓጓዙ ያሉት የወታደር ሃይልና ሩሲያ ላይ ያሳረፉት ማዕቀብ አንድ ላይ ተዳምሮ የፑቲንን ክንድ እንደሚያዝለው ቢጠበቅም የኢኮኖሚ ጣጣው ወደ ሌሎች አገሮች እየተራባ ነው። በነዳጅ፣ በስንዴ፣ በዝየትና አጠቅላይ የግብአት እጥረት ሳቢያ ጦርነቱ ጥቁር አሻራ እያሳረፈ፣ ደሃ አገሮችንና ሰላማዊ ዜጎችን እየደቆሰ መሆኑ ሌላ ራስ ምታት ሆኗል። በጣሊያን በገሃድ ኔቶን ያወገዘ ተቃውሞ ሰልፍ እስከመካሄድ ደርሷል። ሌሎች አገራትም በግብዓት እጥረት ሰላባ በመሆናቸው እያጉረመረሙ ነው።

Leave a Reply