የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ኦቶ ገላሳ ዲልቦ በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግስት ሲመሰረትና ቻርተሩ ሲፀድቅ ተሳታፊ ነበሩ።

አቶ ገለሳ በትግል ውስጥ ወደ 45 ዓመታት ያህል ቆይተዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታትም በውጭ አገር የቆዩ ሲሆን፣ ወደ አገር ቤት የገቡት ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን ጥሪ ተከትሎ በታህሳስ 2011 ዓ.ም ማጠናቀቂያ ላይ ነበር።

“አቶ ገላሳ ዲልቦ ማረፋቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው። ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እና እኩልነት ታግለዋል። በተለይ ሶማሌ በነበራቸው የትግል ቆይታ ብዙ መከራ እና ችግር እንዳሳለፉ አጫውተውኝ ነበር። በቅርቡ በለውጡ አመራር በተደረገላቸው ግብዣ የሰላማዊ ትግል ጉዞ መርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ መታገል ከመጀመራቸውም ባሻገር በ2013 ምርጫ በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል ለመሆንም ችለዋል። በትግል ውጣ ውረድ ውስጥ የገጠማቸውን በጎ እና ክፉ ለማሄስ እና ወጣቶች ከሁለቱም እንዲማሩ ለማድረግ ይተጉ ነበር። አቶ ገላሳ ዝምተኛ፤ አስተዋይ፤ ምክንያታዊ እና ለሰላማዊ ንግግር እጅግ የሚያመች ሰብእና የተላበሱ ግለሰብ ነበሩ። አቶ ገላሳን ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር» ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከአቶ ገለሳ ጋር በፖለቲካ ህይወታቸው ዙሪያ በታህሳስ 2011 ዓ.ም ላይ ሰፋ ያለ ቆይታን አድርጎ ነበር።

ይህንን ቆይታ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል።

Leave a Reply