በተዓምር ካልሆነ እንዴት? የነቀዘ…

ዝም በሉ። አትስሙም። አትናገሩም። ተደበቱ። ከዛ … አይናችሁን ከልቡናችሁ ጋር አንሱ። ወይም በአሮጌው ብሂል አይነ ልቡናችሁን ክፈቱ። ከዛ … አይነ ልቡናችሁ እንደ ፊልም የቀዳውን ደጋግማችሁ እዩት። ከዛ … ተዓምርን ትናፍቃላችሁ!! “ኢትዮጵያን በተዓምር ካልሆነ እንዴት” የሚለው ያልተዘፈነ ዜማ በጆሯችሁ ሽንቁር በታላቅ ነጎድጓድ ይፈሳል። አሁን ያለንበት ዘመን ሲገባችሁ እንጂ ካልገባችሁ ይህ አይሆንም። ለነቀዙም አይሆንላቸውም!!

ለማይደነግጡ የሚታይ ነገር የለም። ኪሳቸው ላሳወራቸው፣ ክፋት ለበቀለባቸው፣ ግፍ ቀለባቸው ለሆነ፣ ደም ለሚጠጡ፣ ደም ማፈሰስ ስራቸው ለሆነ፣ ለቅሶና ዋይታ ሙዚቃ ለሆነላቸው … ለነዚህ ሁሉ አይታያቸውም። ከነ ግብረ አበሮቻቸው ደርቀዋላ!! ነቅዘዋላ!! በቁም ሞተዋላ!! የሃዘኔታ ውሃልካቸው እንክትክቱ ወጥቷላ!! ሞራላቸው የመጸዳጃ ቤት ያህል ሸቷላ!! በእናቶች ሞትና ስደት፣ በህጻናት ስቃይና ዋይታ፣ በአቅመ ደካሞች ጣር፣ በአገር መውደቅ የሚያሽካኩ የቀን አውሬዎች ህሊናቸው ተዘግቷል። መጥሃፉ እንዲህ ያሉትን ” ደርቀዋል” ይላቸዋል። መንፈስ የላቸውም እንደማለት ነው። አሁን ግብግቡ ከነዚህ ጋር ነው።

ሰላም በያላችሁበት። ሰላም ለምስኪኖች፣ ላልደረቃችሁ። ያበደው በትክክል ታሟል። ቦሰናም እንዲሁ ጤና የላትም። ደጎልም የውሻ አስፕሪን ወስዷል። እየሆነ ያለው ሁሉ ጤና አይሰጥም። “እስቲ ቆይ” አለች ቦሰና ” እስቲ ሰው ሶስት ዓመት ሙሉ፣ አንድ ቀን ሳያርፍ ይሳደባል? መርዝ ይረጫል? ” ጠየቀች። የሚያዳምጡትስ አይሰለቻቸውም? መሰልቸት ብቻ አይደለም እንዴት ለመርዝ አከፋፋዮች ያዋጣሉ?

ጥያቄው የቦሰና ብቻ አይደለም። አብዛኞች ይጠያቃሉ። ማታ ማታ አገር ለሚነድሉ ደላሎች እንዴት ሰው ሳንቲም ይሰጣል? ያበደው በድንገት አንድ ነገር ታወሰው። “ጋዜጠኛ” ተደባለቀበት “አክቲቪስት” ተምታታበት ” ተንታኝ” ሃብታሙ አይሌው መተንተን ከመጀመሩ በፊት ከታች ተንትነውት ነበር። ግን በትክክል ምን እንዳደረጉት ከሃኪሙ በቀርና … ይቅር ልጆችም ሚስትም አለው!! ግን ሚስቱ ለምን አትመክረውም? ልጆቹ ሲያድጉ ብዙ ይጠይቃሉ? ሁሉም አየር ላይ ነው? የዛኔ መልስ አይኖርም። ቦሰና ” ያኛውን ተወው” ትላለች። ኤርሚያስን ነው። “መጣፍ ገላጭ” ነው የምትለው። በ97 ምስኪኖች አደባባይ ላይ ሲረሸኑ እየወጣ ፊሽካ ይነፋ ነበር። ልብ አልባው ዲያስፖራ ያንን ረስቶ ዛሬ ይቀልበዋል። … “ሃብታሙን ግን ምነው ሚስቱ ዝም አለችው?” ቦሰና ሁሌም በትዝብት ትጠይቃለች። “አልዳነ ይሆን” ትላለች። ከታች የሚነሳ ችግር ክፉ እንደሆነ መምሬ ስላስተማርዋት “ሙክት ካኮላሸው” እዲሉ … ብቻ ብዙ ምርምር የሚያሻው ጉዳይ አለ።

See also  የጠፈር ሽርሽር በረራ ሊጀመር ነው

“ጋዜጠኛ” ምንድ ነው? “አረ ኤዲያ” ትላለች ቦሰና። መርምረው፣ ፈልፍለው፣ ፍልገው፣ አውጣጥተው፣ በርብረው፣ ሰርስረው አያመጡ ዝም ብለው ወሬ እየቃረሙ ” ገንዘብ አምጡ” ዘመናዊ ልመና!! ጎፈንድ፣ ሱፐር ቻት… ዲጂታል ልመና። ሰሞኑንን ” የሰማሁ መሰለኝ” ብሎ አንዱ ራሱን “ጀግና” ያደረግ ተንታኝ ሲናገር ደጎል ዘሎ ወጣ። ቦሰና ቀበል አድርጋ ” ውሻ አሉህ? አንተ ነበርክ ሰው” አለችና አሽሟጠጠች። የፌስ ቡክ ሟርትና የሴረኞችን አጀንዳ እንደ ቅጠል ማታ ማታ እየጋረቡ ሳንቲም መልቀም …

ጥርሷን ተነቅላ ረሽም ማርል ቦሮ የምትምግ ነጭ ያበደው ፊት ቆማለች። ትምባሆው ረጅም ነው። ትምገዋለች። ያበደው ቀስ ብሎ ተጠጋት። ወሬ ጀመሩ። ልቧ ገራገር ነው። ጥምባሆ እንድታቆም፣ ጥምባሆ ጥምብ እንደሆነ ከመከራት በሁዋላ ሊሰናበታት ሲል ጥያቄዋን አጎረፈች።

ከየት ነህ ግን ይቅርታ

ከኢትዮጵያ ነው የመጣሁት

ጦርነት አለ አይደል? ያሳዝናል? ብላ የትግራይ ሕዝብ እያለቀ እንደሆነ፣ ዓለም ሊደርስለት እንደሚገባ አወጋች። አስከትላ “ስለፈራሁ ቀኑን ሙሉ አጤሳለሁ” ብላ ዩከሬን … ስትል ጀመረች።

በትግራዩ ዜና ላይ ያበደው መጠነኛ ማስተካከያ ካደረገና ለመረጃ ማመጣጠኛ እንዲሆናት የተለያዩ የወሬ ማስፈንጠሪያዎችን ከሰጠ በሁዋላ በአብዛኛው ችግሩ ላይ፣ የሰው ልጆች ስቃይ ላይ ሃሳቡን ሰጥቶ ጠያቂ ሆነ።

ምነው በጣም ፈራሽ?

“ሰውየው” አለች። ፑቲንን መሆኑ ነው። ክፉ ነው። ኒኩሌር ሊተኩስ ይችላል። ሊያጠፋን ነው … እያለች አነባች። እምባዋ ይፈሳል። ጎርፍ ይመስላል። ይህን ስትል እንደ ሶማሌ ክልል፣ እንደ ትግራይ፣ አማራና አፋር ክልል፣ እንደ ወለጋና ቤኒሻንጉል ተፈናቃዮች አይነት መከራና የችጋር ስቃይ ሳታይ ነው። አለችበት አገር ኮሽ ያለ ነገር የለም። ድፍን አውሮፓና ዓለም በኑሮ ውድነት ሲያብዱ እሷ ያለችበት አለችበት አገር ምንም የተፈጠረ አይመስልም። እሷ ግን ታነባለች። ሩቅ ላለው ስጋቷን … ያበደው የዓለምን ሚዲያ ሸውራራነት እያታዘበ ” የሚመካ በአምላክ ይመካ” ብሎ ተሰናበታት።

ደርቀናል። ልቡናችን ተዘግቷል። ምን እስክንሆን እንደሚጠበቅ ግልጽ አይደለም። ትምህርቱ ከሽፏል። ሲስተሙ በክቷል። በበከተ ሲስተምና በከሸፈ ትምህርት ተረግዘው ያደጉ ድንጋይ ወርዋሪዎች ብቻ ሆነዋል። ይህ ሲስተም ለምን፣ እንዴት፣ ወዴት፣ ማን፣ ስለምን ማለት የማይችል ትውልድ አምርቶ አገሪቱን የወላድ መካን አድርጉታል። “ያያሉ ግን አያስተውሉም፤ ይሰማሉ ግን አያደምጡም” የተባለላቸውን ዓይነት ሆነናል። እዚህ ቀውስ ውስጥ በማስተዋል የሚናገሩ እንደ እብድ ይታያሉ። “ለምን አዲስ ግንባታ ይገነባል” በሚል የተሳደቡ ያማረውን ሲያዩ ይቀርታ ከመጠየቅ ተመልሰው ባለቤቱ እያለ እነሱ የይዞታ ተሟጋች እንደሆኑ ሆነው ይቀርባሉ። “ጠጠር እምነበረድ ሆነ፣ ድሮ ኩራዝ የነበረ አሁን አብረቀረቀ” ብለው ይወራጫሉ። ያልታደሉ “ሙዝ በዳቦ ብሉ” ማለታቸው ወንጀል ሆኖ ያስከሳቸዋል። አጀንዳ ሰፋሪዎች ይሰፍራሉ። ቅምጦች ያከፋፍላሉ። ወርዋሪዎቻቸው ሳያላምጡ ይውጡላቸዋል። ማን ነበር ” ከሽፈናል” ያሉት ፈላስፋ። የወደፊቱ ተመልካች? አፈር ይቅለልዎት የኔታ!! እርስዎ እይሉ መርዝ ጠማቂዎች ” ባለ ራዕይ” ተብለው ይፈከር ነበር። አስራት ወልደየስን የበላች ጭልፊት ” ባለ ራዕይ” ያበደው ነባው መጣ … አስራት በነኩት እነ እንቶኔ ሲያገለሙት … ይቀፋል!! “ቸኮል” አሉ!! ቦሰና ብልሽ ሲልባት ” ጎዋ” ትላለች። ጅላጅል ማለት ነው።

See also  [አብይና ትግሬ ታረቁ - አብረው አማራን ሊያጠቁ] የአንገት በላይ ቁምጥና

ብልጽግና ስሙ ቅዱስ፣ መልኩ ሽንጉርጉር፣ ባለ ሁለት መልክ ሾፌሮች የበዙበት ሆኖ የሚሰቃይ ድርጅት ነው። የጎበዝ አለቃ ያላቸው አሉበት። አብዛኞቹ የተመረቱ ስለነበሩ ያራሳቸው ባለቤት የሆኑ የማይመስላቸው አሉ። እነሱ ካልነቁወይም ከልተነቀነቁ መከራው አይጥርም። እነሱን አንቅቶ ወይም ነቅሎ ለማስተካከል እንዳይቻል ቅምጦች ፋታ ነስተዋል። የሚፈልገው በግርገር አገሪቱ ማዛል ነው። ነታሪካዊ መርዘኞች ጋር አድሞ ትርምስን ማከፋፈል ነው። ብልጽግና ውስጥ ያሉትን “የከሸፉ ምርቶች” መጠቀም …

ነገሩ ግራ ነው። ሰው ሰራሹ ግፍ፣ መከራ፣ ስቃይ፣ ከዚህም ከዚያ ጭፍጨፋ፣ ድርቅ፣ መፈናቀል፣ የውጭ ጫና አንድ ላይ ተዳምሮ ኢትዮጵያን እያነኮራት ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ በከርስና በስልጣን ጥማት አሁንም ለተጨማሪ ውድቀት ሩጫው ቀጥሏል። የመንግስት እኩል ሃይል የገነቡ አደባባይ ወጥተው የመሪ ያህል እየተፉ ነው። ምክር ቤት ገብተው “አንቱ” የተባሉ አቅጣጫና አጀንዳ አቀባይ ሆነዋል። ሳያላምጡ የሚውጡ ላይክና ሼር፣ እንዲሁም ብር እየለገሱ እሳቱን እየቆሰቆሱ ነው። መጨረሻውን መተንበይ ያዳግታል። ግን ተዓምር ካልመጣ በቀር በቀላሉ የሚሆን ነገር ያለ አይመስልም። ቦሰና ” ተለዩ” ትላለች።

አሁን መሽቷል። ክረምቱ ለጸደይ አስረክቦ ላለመሄድ ፍትጊያ የያዘ ይመስላል። እንደ ብረት የሚነዝር ብርድ ይጋረፋል። አይን ወሃ ያደርቃል። የዚህኔ ቦሰና ጋር መብረር የያበደው ብቸኛ አማራጭ ነው። ቦሰና!! ትሞቃለች። ሲሞቃት ” አከሲ” ማለት ትወዳለች። በርዱንም ብቸኝነቱንም ሆነ የኢትዮጵያን መላ ቅጡ የጠፋበት ፖለቲካ መማለጥ የሚቻለው ከቦሰና ጋር በመሆን ነው።

ቦሰና ፏ ብላለች። አንዳንዴ ነገር አላት። እንደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ብታበራም ተቃዋሚ የለባትም። ለምን አማርሽ ብሎ የሚነካካት ተኩሳታም የለባትም። ያበደው ገና በሩን ከፈት አድርጎ ሲገባ አይን ለዓይን ተያዩ። ተግባብቷል። ያበደው ፈገገ። ቦሰና የደንቡን ካቁደሰች በሁዋላ በመላ የጣለችውን ጠጅ ቀዳች። ወሬና ጠጅ ይስማማሉ። ያበደውም ቦሰናም እያወጉ አብረው ጋሉ። መሸ። ደጎልም ተሰናበታቸው። “አሲዮ ቤሌማ” ተጨፈረ። ዓመት ዓውደ ዓመት …. ተባለ። ቦሰና ትጣፍጣለች!! ሰላም ለኢትዮጵያ!! ልብ ለደረቁ!! ማስተዋል ለከሸፈ ዘመን ምርቶች!! የብልጽግና ሰዎች አንድ ልብ ሁኑ!! ጥቃቅን መንግስታት ይክሰሙ!! ተዓምሩ አሁን ይሁን!!

See also  [የሽግግር መንግስት] ሊቋቋም ነው !!

Leave a Reply