አፋርና አማራ ክልል መዘንጋታቸውንና የአምነስቲና ሂውማን ዎች የጋራ ሪፖርት ፖለቲካዊ መሆኑንን ጋዜኛኛዋ አስታወቀች

ዓለም ዐቀፍ ተቋማትና የረድኤት ድርጅቶች በአፋርና በአማራ ክልል ያለውን ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ሊገነዘቡና አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ አን ጋሪሰን ተናገረች። የቀረበውን የሰብአዊ መብት ሪፖርት ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው አመለከተች።

አን ጋሪሰን

በኢትዮጵያ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ያደረገችውን ጉብኝት አስመልክቶ ከኢዜአ ጋር በነበራት ቆይታ ጦርነቱ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ማስከተሉን ገልጻለች።

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በሕዝቡ ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅግ አሰቃቂ መሆኑን ተዘዋውራ በተመለከተቻቸው ሥፍራዎች ባደረገችው ምልከታ ማረጋገጧን ጠቁማለች።

ሂዩማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በቅርቡ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ተከስቷል ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያወጡት የጋራ ሪፖርትም ፖለቲካዊ ይዘት አለው ብላለች።

ሪፖርቱ የወጣው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ላይ ያጠናውን ሪፖርት ከመለቀቁ ከቀናት በፊት መሆኑን አንስታ ይህም አንድ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በማለም የተደረገ መሆኑን ገልጻለች።

ከዚህም በላይ ሪፖርቱ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ማዕቀብ እንዲጥሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ማዕቀብ ካልተጣለ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል እምነት በሰዎች ውስጥ እንዲያድር ያለመ መሆኑንም ነው ያነሳችው።

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል የሆኑት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ስለ ትግራይ የሰብዓዊ ቀውስ ብቻ በተደጋጋሚ የሚያደርጉት ውግንና የፖለቲካ አቋማቸውን አመላካች ነው፤ ይህም ገለልተኛ በመሆን ድርጅቱን ለመምራት ከገቡት ቃል ጋር የሚጻረር ነው ብላለች።

See also  ከፌደራል ወደ ክልል የተከለሰው ሴራ - ሶማሌ ክልል እርምጃ ወሰደ

Leave a Reply