አደገኛው ህግ ወደ መዝገብ ቤት በተላከ ማግስት፣ ዓለም ባንክ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ የመልሶ ግንባታው አካላት መሆናቸው ተገልጿል

 “ኤችአር6600” የተሰኘውና “የኢትዮጵያን ሰላም፣ ዲሞክራሲና መረጋጋት መደገፍ” በሚል ሽፋን በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ጥቅም ላይ ጥቁር ጥላ የሚያጠላል የተባለው ህግ በይደር እንዲቆይ በተደረገ ማግስት ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁ ታላቅ የዲፖሎማሲ ድል ተደርጎ እንደሚወሰድ ተሰማ።

Advertisements

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ለተዘጋጀ ፕሮጀክት የሚውል የ300 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማጽደቁ ነው የተሰማው።

ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ይህ ዓለም አቀፍ የልማት ድጋፍ በኢትዮጵያ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች የተጎዱ ሰዎችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እንደሚውል አስታውቋል።

በተለይም ድጋፉ የመሰረታዊ አገልግሎት አቅርቦትን ለማሻሸል እና ለዓየር ንብረት ለውጥ የማይበገር መሰረተ ልማት ለመገንባት እንደሚውል በመጠቆም፥ በግጭት የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንደሚያስቀድም ነው ባንኩ ያመለከተው። በዚህም መሰረት አፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አስታውቋል።

በአጠቃላይ ድጋፉ ከ5 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ነው ባንኩ በመግለጫው ያስታወቀው።

ውጤታማ እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠትም በማሰብ የገንዘብ ድጋፉ በፌደራል መንግስት፣ በክልል መንግስታት እና በአካባቢዎቹ በሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በኩል እንደሚቀርብም ገልጿል።

የአለም ባንክ 300 ሚሊዮን ዶላር ልገሳ ምን ይነግረናል ? ሲሉ አቶ ሳምሶን ሚካሎቪች ይህን አሳብ በማህበራዊ አውዳቸው አስፍረዋለ።

የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋሚያ ዛሬ ለገስኩት ያለው ገንዘብ ከነዋያዊ ፋይዳው ይልቅ ፖለቲካዊ አንድምታው ያመዝናል።

፩. ይህ ልገሳ HR6000 ሳይወለድ መጨንገፉን ያሳያል። የዚህ የህግ ማዕቀፍ አርቃቂዎች ኢትዮጵያ ከባንኩና IMF የገንዘብ ድጎማ እና ብድር እንዳታገኝ ወትውተዋል። ከጅምሩ ምልጃቸው የተሳካ አይመስልም።

፪. አሜሪካ የአለም ባንክ ዋንኛ የገንዘብ ምንጭ ናት። ባንኩ ልገሳም ይሁን ብድር ሲሰጥ የአሜሪካ ይሁንታ ግድ ነው። እናም አሜሪካ ከልምጭ ይልቅ ኢትዮጵያን በካሮት ለማባበል ስትራቴጂ ይዛለች ማለት ነው። የአሜሪካ የስራ አስፈጻሚው ክፍል ከህግ አውጪው በተቃራኒ ሄዶ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ልዩነት በዲፕሎማሲ ለማስታረቅ የመወሰኑ ምልክትም አድርገን ልንወስደው እንችላለን።

፫ .የገንዘብ ድጎማው የሰሜኑ ጦርነት ወደ መቆሙና ኢትዮጵያ ወደ መልሶ ማልማት እየተመለሰች እንደሆነም ያሳያል። አንዳንድ ሰዎች መንግስት ጦርነቱን ማቆሙን ይተቻሉ መለስ ብለውም የኑሮ ውድነቱን ያማርራሉ። ጦርነት የሀገር ሀብት ይበላል ፣ ኢንቨስትመንት ይገድላል ፣ ኢኮኖሚ ይደቁሳል የውጭ እርዳታና ልገሳን ያዳክማል። መንግስት ጦርነቱን ለማቆም መወሰኑ እጅግ ብልህነት የተሞላበት ውሳኔ ነው ፖለቲካዊ ኪሳራ ቢኖረውም። ፖለቲካ ደግሞ ሁሌም calculated risk የምትወስድበት ሂደት ነው።

Related posts:

በሳዑዲና ኢራን በሞት የሚቀጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯልMay 26, 2022
የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022

Leave a Reply